Gimbo Kaffa Ethiopia

Gimbo Kaffa Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gimbo Kaffa Ethiopia, College & University, Gimbo, Bonga.

23/03/2025
11/03/2025

በለምለሚቱ ካፋ... ለም መሬት፣ ምቹ ሥነ-ምህዳር፣ በቂ ዝናብና አምራች የሰው ኃይል ይዘን በኑሮ ውድነት የምንደቆሰው መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ከመድረክ ፍጆታ ያለፈ ትኩረት ባለመስጠቱ ነው።

የግብርና አመራሮችና ባለሙያዎች ሥራ ምን እንደሆነ አይታወቅም። በኢህአዴግ ዘመን በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ የተትረፈረፈ ምርትና ምርታማነት እንደነበር ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። የሴክተሩ ስብሰባ በተካኸደ ቁጥር እየገዛችሁ የመድረክ ማሞቂያ እንደምታደርጉም አላጣንም። በዚህ ልክ ከመውረድ በላይ ምን ዝቅጠት አለ🤭⁉️ ዝምታ አለማወቅ ከመሰላችሁ ተሳስታችኃል።

ሆይ ውሸታችሁ፣ ቅጥፈታችሁ፣ አስመሳይነታችሁ፣ ሙስናችሁ፣ ማጭበርበራችሁ፣ የምትፈጥሩት የመልካም አስተዳደር ችግር ሁሉ ተደማምሮ ሰልችቶናል፣ ቋቅም🤮 ብሎናል። በግድ ማስተዳደር ብሎ ነገር የለም። እንደተገደበ ወንዝ የችግሩ ጽዋ ሞልቶ በተረፈ ጊዜ እናንተን አያርገን❗️

05/03/2025

ምስጋና ለጊምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ
ሚዲያችን የወከላቸውን ህዝብ በታማኝነትና በቅንነት የሚያገለግሉ በገጠርና በከተማ ተግባራት ውጤታማ የሆኑ ከመንግሥት የሚትመደበውን ጥቂት በጀት እንደ እርሾ በመያዝ ህዝብን በማሳተፍና በማነቃቃት ተጨማሪ ሀብት በመሰብሰብ ከሌብነት ፅዱ ሆኖ የምጨበጥ ልማት በማረጋገጥ ለሚሠሩ ታታሪ አመራሮች ተገቢውን እውቅና ይሰጣል ፤ስማቸውንም በክብርና በመልካም ሁሌም ያወሳል። በተቃራኒዉ በሌብነት የተጨማለቁ በማህበረሰቡ ዘንድ ክብረ ነክ ግብር የሚፈፅሙትን እየተከታተለ ያጋልጣል:: ለህዝብም አይንና ጆሮ በመሆን ያገለግላል፤ በማገልገል ላይም ይገኛል።

የጊምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ ወረዳውን ማስተዳደር ከጀመረበት ቀን አንስቶ በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ ጠንካራ መሪ ሲሆን በሌብነት አድገው፧ሌብነትን ተምረውና አስተምሮ በPhD የተመረቁና ብዙ ተከታይ ያፈሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ወደ ጊምቦ ወረዳ አመራር መዋቅርና ፐብሊክ ሰርቪስ ተቋም ለመቀላቀል በራሳቸውና አማላጅ በመላክ ያደረጉትን እልህ አስጨራሽ ትግል ማክሸፍ በመቻልህ ላንተ ያለን አክብሮት ላቅ ያለ ነው።

በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ፊቱን ያዞረ የጊምቦ ወረዳ አመራር፣ሠራተኛና ህዝብ ለማባላትና ለመከፋፈል ስውር ተልዕኮ አንግቦ የነበረው ቀድሞ ከጊምቦ ወረዳ ኢንተርፕራይዞች ልማት ም/ሀላፊነት በስርቆት የተባረረው በአሁኑ ሰዓት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ የሚሠራ መዋሽት ፥ሌብነት፣ማቃጠርና ማጋጨት መለያው የሆነ ያሬድ ከበደ ከብዙ ግብግብ በኃላ የኋሊት ተመልሷል።

ነገሩ እንዲህ ነው አሁን ባለበት ቦታ አመራርን ከሠራተኛ፤ ሠራተኛን እርስበርስ እና አመራርን ከአመራር የሚያጋጭ የውሸት መረጃ መስጠትና ማቃጠር ካልሆነ በስተቀር ምንም መሥራት ባለመቻሉና በቢሮው የሚወጡ የዕቃ ግዢ ጨረታዎችን ከተጫራች ጋር በውጭ በመደራደር እናንተ እንድታሸንፉ አደርጋለሁ በሚል ሲሰራ በጽ/ቤቱ ኃላፊ ብርቱ ክትትልና በጠቋሚዎች መረጃ ተደርሶበት እርምጃ ከተወሰደ በኃላ አንድ ዘዴ መዘየድ ጀመረ።

ከዚህ በኃላ ማምለጫ የለኝም ሰውዬው አይለቀኝም ስለዚህ የቀድሞ ስራዬን ለማቀላጠፍ ወደ ጊምቦ ወረዳ መመለስ አለብኝ አሁን ያለው የወረዳ አስተዳዳሪ በፊት ከኔ ጋር አብሮ ሰርቷል ይቀበለኛል ብሎ አማላጅ መላኪና በራሱም ተፍጨረጨረ።

በጣም የሚገርመው መጀመሪያ የጠየቀውና አማላጅ የላከው የወረዳ አመራር አድርጋችሁ ውሰዱኝ የር/መስ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተረፈ ልያጠፋኝ ነው የሚል ልመናና ዕንባ በመርጨትም ጭምር ነበር።

የዚህን መሰሪ ባህሪ ጠንቅቆ የሚያውቅ አቶ ትብብሩና አስተባባሪው በሹመት ቀርቶ በሙያ አንተን ወደዚህ መመለስ ወረዳውን ወደማይወጣበት አዘቅት ውስጥ መክተት እና ወደኃላ መመለስ ስለሆነ አንቀበልህም ብለው መለሱት።

ይሁን እንጂ እንደ እስስት መልኩን በመቀያየር የሃይማኖት አባቶችን በስተመጨረሻ ልኮ በአመራርነት ካልተቀበሉኝ ባለሙያ ሆኘ እንዲሠራ ይመቻች ብሎ ስያስጠይቅ ለአባቶች ክብር ሲንል ከዚህ በፊት በወረዳው በነበረበት ጊዜ ወጣቶችን በእንተርፕራይዝ ሲያደራጅ ከእያንዳንዱ ወጣት የተቀበለው ገንዘብ ፥ ለወጣቶች የመጣ የገንዘብ ብድር ለራሱ የተጠቀመውን እና በገጠር በወጣቱ ስም የቸበቸበውን መሬትና ሌሎች አንድ ሺህ አንድ ጥፋቶችን በማስረገጥ ከእነዚህና እዛ ክልል ሄደህ ተጨማሪ የሌብነትና ነገር የማመላለስ ኮርስ የወሰድከውን አራግፈህ ሰው መሆን ከፈለክ የወረዳው ሲቪል ሰርቪስ በአሠራር መሠረት ጥያቄውን እንድመልስ አቅጣጫ ተሰጠ።

የሲቢል ሰርቪሱ ሀላፊ ያለው መደብ ደረጃ 12 ነው ሙያ መስመርና አገልግሎት የሚጋብዝ ከሆነ በመ/ቤቱ ማኔጅመንት ይታይ የሚል አቋም ይዞ ሲቀርብ ማኔጅመንቱ አይመጣም አይቻልም ሰውዬው ድሮም ሆነ ዛሬ ስራው ይታወቃል ሠላም አይሰጥም፤ ለምንድነው ክልል ደረጃ 15 ላይ የተመደበ ግለሰብ ደረጃ 12 ወርዶ መምጣት የፈለገው በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ መመለሳቸው የጠንካራ አመራርና ማኔጅመንት Quality ስለሆነ ልናመሰግናችሁ ወደድን።

ነገር ግን አሁንም ቢሆን አቶ ትብብሩ እኔ እንዳልሾምና ወደ ወረዳው እንዳልመጣ እንቅፋት ሆኖብኝ እየተንከራተትኩ ነው የሚል ዘመቻ ላይ ስለሆነ ሌባ ምንም እንደማያመጣ ጠንቅቃችሁ ስለምታውቁ የነበረውን የአመራር አስተሳሰብ አንድነት በማፅናት በራችሁን እንደ እኔ ያሬድ ከበደ አይነቱ ሙልጭልጭ ሌቦች ሾልከው እንዳይገቡ በራችሁን ዘግታችሁ በጀመራችሁት ተነሳሽነትና ወኔ የብልፅግና ጉዟአችሁን እንድትቀጥሉ መልዕክታችን ነው።
ከሌብነት የፀዳች ካፋ-ደቡብ ምዕራብ ክልልን በትግላችን እውን እናደርጋለን +++

Address

Gimbo
Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gimbo Kaffa Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share