08/06/2026
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ሬድዮ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ።
።።።።።።።ሰኔ 1/2018 ዓ.ም።።።።።።።
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ ሬድዮ ጣቢያ FM-92.1ላይ በፈቃደኝነት እያገለገሉ ላሉ እና ፊላጎት ላላቸው መምህራን ፣ የአስተዳደር ስራተኞችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ነግግር ያደረጉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መማ/ማስ/ምር/ማህ/አገ/ቴክ/ስር/ም/ኘሬዝዳንት ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) ናቸው።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው በግልጽ እንዳሰፈሩት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ የራሱን የሬድዮ ጣቢያ መክፈቱን ገልጸዋል።
በመሆኑም የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ብቻ ሳይሆን የሰው ሀይል ልማት ላይ መስራት እንዲሁም ማፊራት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።
የዛሬውም ስልጠና የዚሁ አካል በመሆኑ ሙያው በሚፈልገው ልክ ሰራተኞችን ለማብቃት የታለመ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ሚዲያ የተቋምን ገጽታ ለመገንባት ወሳኝ በመሆኑ በሙያው የታነፀ ባለሙያ ሲኖር ደግሞ ጣቢያው የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አብራርተዋል።
ሰልጣኞችም ስልጠናውን በሀላፊነት ስሜት በመከታተል የሬድዮ ጣቢያውን ወደተሻለ ከፍታ በማሸጋገር ለተቋማዊ ለውጥ የበኩላችሁን እንድትወጡ በማለት በይፋ ስልጠናውን አስጀምረዋል።
ስልጠናውን ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ቦንጋ ቅርንጫፍ የመጡ ባለሙያዎች በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ከመሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብ ባሻገር በተግባር የተደገፈ ስልጠናም የመርሀ-ግብሩ አካል ነበር።
የዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በዋናነት ስልጠናውን አስተባብሯል።
በጋራ እንችላለን!