Golden Gech

Golden Gech Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Golden Gech, College & University, Kombolcha—Gindewoin, Borena.

ይህን ያውቁ ኖሯል ?በአለማችን ካሉ ፍጡራን እጅግ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ፈስ በማንዛረጥ ዜብራ ቀዳሚው ነው። የፈሳቸው ድምፅ ከአንድ ኪሎሜትር በላይ ባለ ርቀት ይሰማል። ግማቱ ደግሞ አፍንጫ ይ...
13/11/2025

ይህን ያውቁ ኖሯል ?

በአለማችን ካሉ ፍጡራን እጅግ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ፈስ በማንዛረጥ ዜብራ ቀዳሚው ነው። የፈሳቸው ድምፅ ከአንድ ኪሎሜትር በላይ ባለ ርቀት ይሰማል። ግማቱ ደግሞ አፍንጫ ይቆርጣል !

ጥቁር ጉንዳኖች ሁለት ሆድ አላቸው። አንዱ ለግል ጥቅማቸው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከራሳቸው ቆርሰው ለሌሎች   ለማካፈል የሚጠቀሙበት ነው ተካፍሎ መብላት 🙌
27/10/2025

ጥቁር ጉንዳኖች ሁለት ሆድ አላቸው። አንዱ ለግል ጥቅማቸው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከራሳቸው ቆርሰው ለሌሎች ለማካፈል የሚጠቀሙበት ነው

ተካፍሎ መብላት 🙌

ቼጉቬራ በሆነ የበግ እረኛ አቃጣሪነት ከተደበቀበት ቦታ ተያዘ። አንድ ሰውዬ የተፈጠረው ነገር ግርምት ጭሮበት እረኛውን ጠየቀው፦“እድሜ ልኩን ላንተ መብት ጠበቃ ሆኖ ሲዋጋ የኖረን ሰው ለምን ...
19/10/2025

ቼጉቬራ በሆነ የበግ እረኛ አቃጣሪነት ከተደበቀበት ቦታ ተያዘ። አንድ ሰውዬ የተፈጠረው ነገር ግርምት ጭሮበት እረኛውን ጠየቀው፦“እድሜ ልኩን ላንተ መብት ጠበቃ ሆኖ ሲዋጋ የኖረን ሰው ለምን አቃጠርክበት?”

እረኛውም እንዲህ ሲል መለሰ፦“ይህ ነፃ አውጪ ነኝ የሚለን ሰውዬ እደበቃለሁ ሲል በጎቼን አስንደንብሮ ከበረት ሰደደብኝ”

ከአመታት በኋላ በግብፅ ታላቁ አዛዥ ሙሀመድ ከሪም በስሩ መቶ ሺህዎችን ያሰለፈ የፈረሳዩን መሪ ናፖልዮን በመቃወም ደረጃ ብቻውን የቆመ ብቸኛ ሰው ነበር። ቢሆንም በመጨረሻም ሙሀመድ ከሪም በናፖሊዮ እጅ ወደቀና የሞት ፍርድ ተፈረደበት። ናፖሊዮ ግን ሙሀመድን ጠርቶ እንዲህ አለው፦“እንደ አንተ ዓይነት ሰው ከስንት አንድ ቢገኝ እንጂ የለም። ለእኔ ደግሞ አገሩን ብሎ የተዋጋን ጀግና መግደል በታሪክ የማይረሳ ጠበሳ ነው የሚሆንብኝ። ስለዚህ አላስገድልህም። ነገር ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አለ፤ እንደ መካሻ ይሆን ዘንድ መቶ ዐሥር ሺህ የወርቅ ሳንቲም ክፍያ ታቀርባለህ። እኔም እርህራሄዬን እሰጥሃለሁ።”

ሙሐመድ ከሪምም ፈገግ አለና እንዲህም አለ፦“ለጊዜው የዛን ያህል የሚበቃ የወርቅ ሳንቲም በእጄ የለኝም፤ ነገር ግን ለነጋዴዎች ከመቶ ሺህ በላይ የወርቅ ሳንቲም አበድርያለሁ።”

ናፖሊዮ ይህን ሲሰማ ጥቂት እንዲቆይ ፈቀደለት። እናም ሙሀመድ ከሪም በወታደሮች ተከቦ ገበያ ወጣ። መስዋት የከፈለላቸው የአገሩ ነጋዴዎች ተስፋን ከሰጡት ብሎ ያበደረውን የወርቅ ሳንቲም ጠየቀ። አንድ ነጋዴ ግን ሊሰማው አልፈቀደም፤ እንደውም የታላቁ እስክንድር መጥፋት እና የኢኮኖሚ መውደቅ መንስኤ ነው ሲል ከሰሰው።

መሐመድ ከሪም ወደ ናፖሊዮን በተሰበረ ልብ ተመለሰ። ናፖሊዮም እንዲህ አለው፦“ተስፋ አላስቆርጥህም አላስገድልህምም ጭምር። ምክንያቱም ከእኛ ጋር ጦርነት መግጠምህ ብቻ ሳይሆን፤ ሕይወትህን ለሕዝብ ስትል አሳልፍህ መስጠትህ ትልቅ ክብር ነው። እነሱ ግን ነፍሳቸውን በሸቀጥ የለወጡ ግብዞች ናቸውና ነፃነት ከንግድ እንደሚበልጥ ፈጽሞ አልተገነዘቡትም።”

የአረቡ ታላቅ ባለቅኔ ሙሀመድ ራሺድ ረዛ እንዲህ ይላሉ፦“ደናቁርት ማኀበረሰብን ለማሳወቅ የተነሳ አዋቂ፤ ለዕውር መንገድ ያበራለት ዘንድ እራሱን በእሳት ያቃጠለን ሰው ይመስላል።”

17/10/2025
15/10/2025

🛜አሁን ምን አይነት ዜና አየሁ በሩሲያ የወሊድ ምጣኔ መቀነሱን ተከትሎ ሀገሪቱ ቤተሰቦች ልጆች እንዲወልዱ እያበረታታች ሲሆን፤ ለዚህም ሦስት ወይም ከዚያ በላይ ልጆች ለሚወልዱ ቤተሰቦች ብዙ ጥቅማጥቅሞችን አቅርባለች፡፡ ጥቅማጥቅሞቹ የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

✅• እስከ 1 ሚሊዮን ሩብልስ የሚደርስ የገንዘብ ጉርሻ

✅• መኖሪያ ቤት መገንቢያ መሬት

✅• ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎትና የት/ቤት ምገባ ለልጆች

✅• ነጻ የሕክምና አገልግሎቶች

✅• የመብራትና የነዳጅ ክፍያዎች ከቀረጥ ነፃና ቅናሽ

✅• ዓመታዊ የቤተሰብ ጉዞዎችና የእረፍት ጊዜያት

ይሄ የሩሲያ ህግ እኛ ሀገር ቢመጣ አስበኸዋል 😁

30/09/2025

የንግድ ባንክ ደንበኞች ከፍተኛ የአገልግሎት
ክፍያ ቅሬታ አሰሙ! 🛑

የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ደንበኞች፣ ባንኩ መስከረም 19 ተግባራዊ ባደረገው የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ሳቢያ፣ እጅግ ያልተለመደ እና ከፍተኛ የሆነ የኮሚሽን ቅነሳ እየገጠማቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይ ገንዘብ ከአንድ ባንክ ወደ ሌላ ባንክ ሲተላለፍ ባንኩ በኮሚሽንና በ15% ቫት ስም የሚቆርጠው መጠን ከሚላከው ገንዘብ በላይ ሆኖባቸዋል ብለው በርካታ ደንበኞች በማህበራዊ ሚዲያዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ከደንበኞች የተሰጡ ምሳሌዎች፡-

* አንድ ደንበኛ 100 ብር ከንግድ ባንክ ወደ ሌላ ባንክ ሲልክ፣ 57.7 ብር ተቆርጦበታል።

* ሌላኛው ደንበኛ ደግሞ 20 ብር ብቻ ልኮ በጠቅላላ 57 ብር ተቆርጦበት እንደነበር አስታውቋል።

ለመላው የCBE ደንበኞች፡

እርስዎስ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞዎታል?
ምን ያህል ተቆርጦብዎታል?

አስተያየቶን ያጋሩን!

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

12/09/2025

" ሲያልቅልን ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ትክክለኛ ቀን እናሳውቃችኋለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች " የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ነው ይፋ የሚደረገው ? ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጳጉሜን 4/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋል ብለው ነበር ሳይደረግ አለፈ ውጤት ይፋ የሚደረገው መቼ ነው ? " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች እና ወላጆችን ጥያቄ ይዞ አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን አነጋግሯል።

እኚህ አመራር " ውጤት ሲያልቅ እንገልፃለን በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ይለቀቃል፤ ትክክለኛው ቀን ሲወሰንም በይፋ ሚዲያ ጠርተን እናሳውቃለን " ብለዋል።

" የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ተማሪዎችን እያወናበዱ ነው " ያሉት አመራሩ ተማሪዎች ውጤቱ ይፋ የሚደረግበትን ቀን ከተቋሙ እስኪሰሙ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች (በፌስቡክ ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ) " ስለ ውጤት መረጃ አገኘን በዚህ ቀን ይወጣል " እያሉ የሚያሰራጩት መረጃዎችም ሀሰተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል።

" እኛ በሚያልቅ ጊዜ እናንተን ጨምሮ ሚድያዎችን ጠርተን እናሳውቃለን " ያሉም ሲሆን " ' በዚህ ቀን ይወጣል ተብሎ ነበር ' የሚለው ሳይሆን ጥርት ብሎ ሲያልቅልን በፍጥነት እናሳውቃለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ580 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር ✅

08/09/2025

ለወንዶች የዘር ፍሬን (s***m) ቁጥር ለመጨመር እነዚህን አድርግ፥

✅የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቢያንስ በሳምንት ለ 150 ደቂቃ ስራ

✅ክብደትህን ከቁመትህ ጋር የተስተካከለ ይሁን (ማለትም body mass index = weight in kg ሲካፈል height in meter = ከ 18.5 እስከ 24.9 kg/m2 ይሁን)

✅በምግቦችህ ውስጥ
☑️ዚንክ (ቀይ ስጋ ፣ ባቄላ ፣ አተር ፣ የዱባ ፍሬ)
☑️ኦሜጋ 3 (አሳ)
☑️ፎሊክ አሲድ (ጎመን ፣ ባቄላ)
☑️ቪታሚን ሲ (ፍራፈሬ ፣ የወተት ተዋፅኦ ፣ እንቁላል)
☑️ቪታሚን ዲ (የጧት ፀሀይ ፣ የወተት ተዋፅኦ ፣ እንቁላል) የያዙ ምግቦችን ተመገብ።

የዘር ፍሬን (s***m) ቁጥር ለመጨመር እነዚህን ግን አስወግድ፥

✅ሲጋራ ማጨስ
✅አልኮሆል መጠጣት
✅ብልት አካባቢ ሞቃት ነገሮችን ማስወገድ
✅ጠባብ የውስጥ ፓንት መልበስን አስወግድ

ሳይንቲስቶች እንደተናገሩት ከሆነ በሚፈነዳ እሳተ ጎመራ ውስጥ የሚኖሩ ሻርኮች እና የተለያዩ የአሳ ዝርያት እንደሚኖሩ አረጋግጠናል ብለዋል።
08/09/2025

ሳይንቲስቶች እንደተናገሩት ከሆነ በሚፈነዳ እሳተ ጎመራ ውስጥ የሚኖሩ ሻርኮች እና የተለያዩ የአሳ ዝርያት እንደሚኖሩ አረጋግጠናል ብለዋል።

በደቡብ ሱዳን በሚደረግ ብዙ ወተት የመጠጣት ውድድር ባክ ማጎክዲት የተባለ ሱዳናዊ ውድድሩን ቢያሸንፍም ሽልማቱን ሳይቀበል ህይወቱ ወዲያውኑ አልፏል።ለህይወቱ ማለፍ ምክንያት በጣም ብዙ ወተት ...
06/09/2025

በደቡብ ሱዳን በሚደረግ ብዙ ወተት የመጠጣት ውድድር ባክ ማጎክዲት የተባለ ሱዳናዊ ውድድሩን ቢያሸንፍም ሽልማቱን ሳይቀበል ህይወቱ ወዲያውኑ አልፏል።

ለህይወቱ ማለፍ ምክንያት በጣም ብዙ ወተት መጠጣቱ ነው ተብሏል ።

06/09/2025

የ2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ፤ትምህርት ሚኒስቴር

ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሞባይል ስልክ ፣ ታብሌትና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዞ ትምህርት ቤት መምጣት ተከልክሏል፡፡

----------------------------------------

(ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች አከፋፈት አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር ባደረገበት ወቅት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 5/ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል።

በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት ዓርብ መስከረም 2 / 2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበትና መስከረም 5/2018 ዓ.ም ደግሞ በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑንም ክብርት ወ/ሮ አየለች አስታውቀዋል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የተማሪዎችን ሥነ ምግባር በተመለከተም ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በየትኛውም ክልልና የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ ታብሌትና ማናቸውንም የትምህርት ስራ ላይ ተጽእኖ ሚያሳድሩና አዋኪ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስገንዝበዋል፡፡

በበይነ መረብ በተካሄደው ምክክር የትምህርት ጥራትና ፕሮግራሞች መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ (ዶ/ ር) የ2018 የትምህረትት ዘመን የትምህርት ቤቶችን አከፋፈት ጋር ተያይዞ የባለድርሻ አካላት ሚና ፣የትምህርት ቤቶች ዝግጅት፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት አካባቢ በመፍጠር፣ በትምህርት ለትውልድና በሌሎችም ዙሪያ ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለ2018 የትምህርት ዘመን አከፋፈት ፣በተማሪዎች ምዝገባ ፣ በትምህርት አጀማመር፣ በመማር ማስተማር ስራውና በተማሪዎች ስነ ምገባር ዙሪያ አፈጻጸሞቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

Address

Kombolcha—Gindewoin
Borena

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Golden Gech posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Golden Gech:

Shortcuts

Share