አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ /Amhara Region Police University College/

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Mark'os
  • አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ /Amhara Region Police University College/

አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ /Amhara Region Police University  College/ The Amhara Regional State Police Training Institute has been providing various skills and police training's since 1985.
(2)

The training institute has been upgraded to the ARPC in accordance with Reg. No. 53/1999 and is being formed by three deputy directors

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ያዘጋጀውን በወንጀል መከላከል የመጀመሪያ ደግሪ እና የድህረ ምረቃ ዲፕሎማ ስርዓተ-ትምህርቶች ወርክሾፕ አካሄደ፡፡ሀምሌ 14 2018 ዓ ም ደብረ ማርቆስየ...
22/07/2026

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ያዘጋጀውን በወንጀል መከላከል የመጀመሪያ ደግሪ እና የድህረ ምረቃ ዲፕሎማ ስርዓተ-ትምህርቶች ወርክሾፕ አካሄደ፡፡

ሀምሌ 14 2018 ዓ ም ደብረ ማርቆስ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀዉን በወንጀል መከላከል የመጀመሪያ ዲግሪና የድህረ ምረቃ ዲፕሎማ ስርዓተ-ትምህርቶች ላይ ከዩኒቨርስቲ ኮሌጁ አመራርና መምህራን ጋር ቫሊዴሽን ወርክሾፕ አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት ም/ ኮሚሽነር አበበ ደለለ እንዳሉት ተቋማችን ከኮሌጅነት ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ማደጉን ተከትሎ አዳዲስና ያደጉ የስልጠና ፕሮግራሞችን መጀመር ይጠበቅብናል ብለዋል። በ2019 በጀት ዓመት ስልጠና ለመስጠት በዕቅድ ከተያዙት ውስጥ በወንጀል መከላከል የመጀመሪያ ዲግሪ እና የድህረ ምረቃ ድፕሎማ ስልጠና ፕሮግራሞች ዋነኞቹ በመሆናቸው በነዚህ የስልጠና ፕሮግራሞች ላይ የተዘጋጀ ስርዓተ-ትምህርቶች ላይ ከመምህራን ጋር መወያየትና አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት የክልላችንን ፖሊስ የመፈፀም አቅም የሚያሳድግ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል ።

በመሆኑም የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ መምህራን አዳዲስና ገንቢ ሀሳቦችን በማፍለቅ ስርዓተ-ትምህርቱን ማዳበር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ዋና መምሪያ ሀላፊና የአካዳሚክስ ጉዳዬች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ሲሳይ እደገለፁት በአዲሱ በጀት ዓመት በርካታ ስልጠናዎችን መስጠት የሚጠበቅብን ስለሆነ መምህራን ራሳቸዉን ከወዲሁ መዘጋጀት ያለባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የዛሬዉ የስርዓተ-ትምህርት ቫሊዴሽን ወርክሾፕ የ2019 በጀት ዓመት ዋና ተግባሮች ውስጥ በመሆናቸው የተዘጋጀውን ስርዓተ-ትምህርት ማዳበር የሚጠበቅብን ስለሆነ መምህራን ከፍተኛ ተሳትፎ እዲያደርጉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የተዘጋጁትን ረቂቅ ስርዓተ- ትምህርቶችን ዋና ኢንስፔክተር (እጬ ዶክተር ) ከፍያለው የኔየት አቅርበው በዩኒቨርስቲ ኮሌጁ አመራሮችና መምህራን ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ወርክሾፑ ተጠናቋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰባዊነት ማገልገል።

13/07/2026
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የ2018 በጅት ኣመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ደብረማርቆስ፡፡የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሉጅ አመራሮችና ሁሉም...
07/07/2026

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የ2018 በጅት ኣመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡
ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ደብረማርቆስ፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሉጅ አመራሮችና ሁሉም ሰራተኞች በተገኙበት በ2018 በጀት ዓመት የተከናዎኑ ተግባራትን ግምገማ አካሂዷል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ዕቅድና በጀት ዋና ክፍል ተወካይ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጥላሁን ቢድግልኝ በሪፖርቱ እንዳመላከቱት በዚህ በጀት ዓመት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብሏል፡፡ በተለይም በክልላችን ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የቀረቡ የስልጠና ፕሮግራሞችን በመቀበል ሁሉንም በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን ገልጾ ሪፖርቱን በዝርዝር አቅርቧል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ኮሉጁ ፕሬዝዳንት ም/ኮሚሽነር አበበ ደለለ የስራ አፈጻጸም ግምገማውን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ በ2018 በጀት ዓመት በረካታ ተግባራትን ያከናዎንበት ጊዜ መሆኑን በተለይም በመሰረታዊ ፖሊስ እና ልዩ ልዩ የፖሊስ ሙያዎች ሰልጣኞችን ተቀብሎ ከማሰልጠን በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ የማዕረግ ሽግግር ስልጠና ስርዓተ ትምህርት በመቅረጽና ሞጁል በመናዘጋጀት ሰልጣኞችን ተቀብለን ማሰልጠን መቻላችን በጉልህ የሚጠቀስ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል የ4ኛ ዙር ክልል አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤን በስኬት ማዘጋጀታችን፣ በጥሩ ብርሃን በርካታ ቁጥር ያለው የሰላም አስከባሪ ስልጠናዎችን መስጠታችን፣ የህንጻ እደሳትን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ስርዓተ ትምህርት እና ሞጁል ማዘጋጀታችን፣ የሚመጡ ድንገተኛ የስልጠና ፕሮግራሞችን ተቀብሎ በማሰልጠንና በማስመረቅ የተከናዎኑ ተግባራት የዩኒቨርሲቲ ኮሌጃችንን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ውጤት መመዝገብ ደግሞ ሎጅስቲክስና ሌሎች አስፈላጊ የስልጠና ግብዓቶችን ከማሟላት ጀምሮ የነበሩ ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራርና የአመራሩን የፈጻሚ አካላት ተናቦ መስራት ውጤት በመሆኑ ሁሉም ፈጻሚ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በዚህ በጀት ዓመት የታዩ ጥንካሬዎች እንደ ግብዓት በመውሰድና ከድክመቶቻችን በመማር በቀጣዩ በጀት ዓመት የሚኖሩንን በርካታ ተግባሮቻችንን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ከወዲሁ ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን ብለዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አመራርና ሰራተኞች በቀረበው ሪፖርት ላይ በታዩ ጥንካሬዎችና በቀጣይ መስተካከል በሚገባቸው የአሰራር ክፍተቶች ላይ በሰፊው አስተያዬት የሰጡ ሲሆን በቀጣዩ በጀት ዓመት ከዚህ በበለጠ ሁኔታ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!!

የአማራ ክልል ፖሊስ ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለመምህራን ለአካል ብቃት አሰልጣኞች ሰለ በስርዓተ ትምህርትና የሞጅል አዘገጃጀት ዙሪያ  የአቅም ግንባታ ሰልጠና ተሰጠ ። ሰ...
18/06/2026

የአማራ ክልል ፖሊስ ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለመምህራን ለአካል ብቃት አሰልጣኞች ሰለ በስርዓተ ትምህርትና የሞጅል አዘገጃጀት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሰልጠና ተሰጠ ።
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በስርዓተ ትምህርት እና ሞጁል አዘገጃጀት ዙሪያ ለ3 ተከታታይ ቀን ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ሰልጠናዉን የሰጡት ዋና ኢንስፔክተር (እጩ ዶክተር ) ከፍያለው የኔት ሲሆኑ ፖሊስ ሁሌም ተቋማት ባደጉ ቁጥር ስርዓተ ትምህርቱና ሞጁሎቻችን ዘመኑን የዋጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ተቋማችን ከኮሌጅነት ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሲያድግ በስም ብቻ ሳይሆን በተግባር ተቋሙን የሚመጥን መምህር፣ አሰልጣኝ፣ እንዲሁም ጊዜውን ያገናዘበ ስርዓተ ትምህርት እና ሞጁል ሊኖረን ይገባል፡፡ የዚህ ስልጠና ዓለማም አሁን በወንጀል መከላከል እያዘጋጀነው ላለው የአድቫንስ ዲግሪ የሞጁል ዝግጅት ላይ የተሻለ አቅም ለመፍጠር እና በመምህራን መካከል ተቀራራቢ ዕውቀት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ያለባቸውን የጊዜ ጥበት አጣጥመው ስልጠናው ለሰጡትና በዩኒቨርሲቲ ኮሌጃችን የረጀርም ጊዜ መምህርና የአሁኑ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪያችን ዋ/ኢ/ር ከፍያለው የኔየት ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም እንዲዚህ ያሉ የስራ ላይ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል፡፡
ኮሚሽነሩ እዳሉት ወቅቱ የሞጅል ዝግጅት የምናዘጋጅበት ጊዜ በመሆኑ ያለብንን ክፍተት የምንለይበት እና የተሸለ ሞጁል ለማዘጋጀት አቅም የምነጥርበት በመሆኑ ሁሉም መምህራን ስልጠናውን ትኩረት ሰጥተው መከታተል ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡
ዋና ኢንስፔክተር ( እጬ ዶክተር) ከፍያለው የኔዬት ሰልጠናው በዩኒቨርስቲ ኮሌጃችን ሰለ ስልስርኣተ ትምህርትና ሞጁል አዘገጃጀት ስልጠና በመስጠታቸዉ ደሰተኛ መሆናቸውን ካነሱ በኋላ በተለይ ስርኣተ ትምህርት ለአንድ የትምህርት ተቋም በተለይም ደግሞ ለፖሊስ ወሳኝና አስፈላጊ በመሆኑ ሁሌም ልንረዳው ልናውቀው ይገባል በማለት በስፋት ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን የተከታተሉት መምህራንና አካል ብቃት አሰልጣኞች ይህን ትምህርት የሰጡሉን ዋና ኢንስፔክተር (እጩ ዶክተር ) ከፍያለው የኔየት ለሌሎቻችን አራያ እና ስልጠናውን በቲዎሪና ተግባሩን አዋህደው ስለሰጡን እናመሰግናቸዋለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ሲሳይ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሌጅ የጥናትና ምርምር ዋና መምሪያ ሀላፊ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ መምህራን ሁሌም ከመፃፍ፣ ከማንበብና ከመማር መራቅ የለባቸውም ብለዋል፡፡ በቀጣይም እንደዚህ ያሉ አጫጭር የስራ ላይ ስልጠናዎች የሚቀጥሉ መሆኑን አስገንዝበዋል

ምርምርና ፈጠራ የታገዘ ፖሊሳዊ አገልግሎት ለዘላቂ ሰላም፤” 4ኛው የጥናትና ምርምር ጉባኤ በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተካሂዷል። አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደብረ ማርቆስ ...
28/05/2026

ምርምርና ፈጠራ የታገዘ ፖሊሳዊ አገልግሎት ለዘላቂ ሰላም፤” 4ኛው የጥናትና ምርምር ጉባኤ በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተካሂዷል።

አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደብረ ማርቆስ ግንቦት 20/2018 ዓ/ም

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ “ምርምርና ፈጠራ ለተሻለ የፖሊስ አገልግሎት እና ዘላቂ ሠላም!” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የጥናትና ምርምር ጉባኤ ተጠናቋል።
በዚህ መድረክ ላይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የፖሊስ ስትራቴጂክ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎችና የዘርፉ ምሁራን ታድመዋል።
በጉባኤዉ መክፈቻ ላይ መሪ ቃሉን መነሻ በማድረግ ቁልፍ ንግግር ያደረጉት ረዳት ኮሚሽነር ግዛቸው ከበደ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የአካዳሚክስ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እንደገለጹት ወቅቱ የሚጠይቀውን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ውጤታማ የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት የምርምርና የፈጠራ ስራዎች ወሳኝ ሚና አላቸው።
ይሄንን ሳይንሳዊ መንገድ መከተል ለአካባቢው ህዝብ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ጠንካራ መሰረት ይጥላል ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር ግዛቸው ከበደ አክለው አብራርተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የ6ኛ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በበኩላቸው፤ በምርምር የተደገፈ ፖሊሳዊ አገልግሎት መስጠት በክልሉ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን ለጎን የጥናትና ምርምር ተቋማት የሚያመነጯቸው ግኝቶች በወረቀት ላይ ብቻ መቅረት እንደሌለባቸውና በተግባር ላይ መዋል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ በበኩላቸው የወቅቱ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ ፖሊሳዊ አገልግሎቱ ካለበት ልማዳዊ አሰራር ወጥቶ ወደ ላቀ ሳይንሳዊ ምዕራፍ እንዲሸጋገር እንደሚያስገድደው በስፋት አብራርተዋል።
የክልሉ የፖሊስ ሰራዊት በንድፈ-ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ እውቀት፣ በተግባራዊ ክህሎት እና በከፍተኛ ስነ-ምግባር የታነጸ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።
“የእኛ ዋና ተልዕኮ ህዝብን በታማኝነት፣ በቅንነትና በሙያዊ ብቃት ማገልገል ነው። ይህንን ለማሳካት ደግሞ ሰራዊታችን በየደረጃው የህዝብን ደህንነት በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚያስችል የዕውቀትና የክህሎት ባለቤት መሆን አለበት” ሲሉ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ይህ 4ኛው የምርምር ጉባኤ እንዲሁ በየዓመቱ የሚደረግ ተራ ስብሰባ ሳይሆን፣ የአማራን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስጠበቅ የሚያግዙ ስልታዊ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል።
በጉኤዉ በተጨባጭ መሬት ላይ ያሉ የጸጥታ ፈተናዎችን በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር በተደገፈ አሰራር ለመፍታት እና አዳዲስ ስልቶችን ለመንደፍ የሚያስችል ዋና የዕውቀት መፍለቂያ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት የነገውን ፖሊስ የመገንባት ትልቅ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነሩ በተለይም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የበቃ፣ ከዘመኑ ጋር እኩል የተራመደ እና በቴክኒክና ታክቲክ የላቀ ዘመናዊ የፖሊስ ሰራዊት ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
የወንጀል መከላከልም ሆነ የምርመራ ስራዎች በቴክኖሎጂ ሲታገዙ የህዝቡን እምነት የሚያተርፍና አጥፊዎችን በቀላሉ ለህግ የሚያቀርብ ተቋም መፍጠር እንደሚቻልም በዝርዝር አስገንዝበዋል።
በጉባኤዉ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
• “Police operational roles and crime prevention effectiveness in volatile security context”
• “Challenges of policing in enforcing law and public order during armed conflict”
• “Unpacking predictors of police violence in Ethiopia: A post-1991 perspective”
• “Examining the effect of authentic and transformational leadership styles on police officers' motivation”
• “Police education and training as drivers of police reform in Ethiopia”
በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰበዓዊነት ማገልግል!

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ 4ኛው የምርምር ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ።አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደብረ ማርቆስ ግንቦት 20/2018 ዓ/ምየአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌ...
28/05/2026

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ 4ኛው የምርምር ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ።

አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደብረ ማርቆስ ግንቦት 20/2018 ዓ/ም

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ "ምርምርና ፈጠራ ለተሻለ የፖሊስ አገልግሎት እና ዘላቂ ሠላም!" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት የሚቆየውን 4ኛውን የምርምር ሲምፖዚየም ማካሄድ ጀምሯል።

በዚሁ ከፍተኛ የፖሊስ ምርምር መድረክ ላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የ6ኛ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ፣ በብርጋዴር ጀኔራል ሶፍያን መሀመድ 602ኛ ኮር አዛዥ፣ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ፣ አቶ ተሾመ ዋለ የደብረማርቆስ ከተማ ከንቲባ፣ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ስትራቴጂክ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለፀዉ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሲምፖዚየም ላይ በፖሊሳዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በፈጠራ ስራዎችና በዘላቂ ሰላም ግንባታ ዙሪያ ትኩረታቸውን ያደረጉ አምስት የምርምር ጽሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ይደረግባቸዋል።

ይህ የምርምር መድረክ የፖሊስ ተቋምን የአሰራር ስርዓት በሳይንሳዊ እውቀትና በምርምር ውጤቶች ለማዘመን፣ የጸጥታ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እና የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።

"የፖሊስ ተቀደሚ ተግባር ወንጀልን መከላከል ፣ ህግና ሰርዓት ማሰጠበቅና ማሰከበር ነው እንዲሁም በተቋማችን ጠንካራ ሰራዊት እየተገነባ የማድረግ አቅሙ እየጨመረ መጧል።"      ረዳት ኮሚሸነ...
24/05/2026

"የፖሊስ ተቀደሚ ተግባር ወንጀልን መከላከል ፣ ህግና ሰርዓት ማሰጠበቅና ማሰከበር ነው እንዲሁም በተቋማችን ጠንካራ ሰራዊት እየተገነባ የማድረግ አቅሙ እየጨመረ መጧል።"
ረዳት ኮሚሸነር አብዮት ሸፈራው

አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የመሰረታዊ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የአድማ መከላከል ሰልጣኝ ፖሊሶችን አሰመረቀ።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ በአማራ ክልል ፖሊሰ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሀብት አሰተዳደርና እና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ረዳት ኮሚሸነር አብዮት ሸፈራው ፣ በአማራ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የመሠረታዊ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ኮማንደር ይሰማ ተናኜ ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዪኒቨርስቲ ኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና እና ተጋባዠ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል ።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ የመሰረታዊ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ኮማንደር ይሰማ ተናኜ በሪፖርቱ እንዳመላከቱት የዕለቱ ተመራቂዎች የህግ ማሰከበር ተግባር አጠናክሮ ለማሰቀጠልና በሀገራችን ብሎም በክልላችን አሰተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያበቃቸውን ሰልጠና የወሰዱ ሲሆን በስልጠና ቆይታቸው ተገቢውን ወታደራዊ ዕውቀትና ክህሎት በማሰጨበጥ ለቀጣይ ተልዕኮ ብቁ የሚያደርጉ ፣ ወቅታዊ ሁኔታውን በሚገባ የተረዱና የነበራቸውን በዥታ በስልጠናው ሂደት በአግባቡ እንዲረዱ የተደረጉበትና በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ በሚገባ እንዲወጡ ለማድረግ የአመለካከትና የተግባር አንድነት እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸውን ሰልጠና በሚገባ ተከታትለዋል ብለዋል።

በአማራ ክልል ፖሊሰ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሃብት አሰተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሸነር አብዮት ሸፈራው ለዕለቱ ተመራቂዎች የሰራ መመሪያ ሰጥተዋል ።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ ዋና መምሪያ የሰው ሀብት አሰተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሸነር አብዮት ሽፈራው እንደገለጹት የፖሊስ ተቀደሚ ተግባር ወንጀል መከላከል ፣ ህግና ሰርዓት ማሰጠበቅና ማሰከበር ነው ብለዋል ።

እንደ ኮሚሸነሩ ገለፆ የክልላችን መንግስት ተቋሙን በቴክኖሎጅ ፣ በሰለጠነ የሰው ኃይልና በሎጀስቲክስ አቅርቦት አቅሙን ከፍ ለማድረግ እና ሰራዋቱን ምቹ የሰራ ከባቢ በመፍጠር ከመቸውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።

ተመራቂ የአድማ መከላክል ፖሊሶች ህዝብ ያገለግሎኛል ብሎ ከፍተኛ እምነት አሳድሮ መልምሎ ለሰልጠና ሲልካችሁ ትልቅ ግምትና ዋጋ ሰጧችሁ እንደሆነ ላፍታም ቢሆን መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ሲሆን እናንተም በሰልጠና ማጠቃለያ የገባችሁትን ቃል ጠብቆ ለማቆየት ብሎም የህዝብና የመንግሰትን አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት፣ በጽናት ፣ በሙያዊ መልካም ሰነ ምግባር አደራችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ መመሪያ ሰጠዋል።

በመጨረሻመ ውድ ተመራቂዎች ዛሬ ተልዕኮ የምትቀበሉበት ቀን ነው ፤ የምትመረቁበት ከዚህ ወጥታችሁ ህግና ሰርዓት የናፈቀው ህዝባችን በሰላም መንቀሳቀሰና ሰርቶ መብላት የሚቻልበት ሁኔታ ሲፈጠር ነውና ይሄን እያሰባችሁ የሚሰጣችሁን ተልዕኮ እንድትፈፅሙ እያሳሰኩ መጪው ጊዜ ውጤታማና የድል ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ ለተመራቂዎች መልዕክታቸውን አሰተላልዋል።

የዕለቱ ተመራቂ ሰልጣኞች በበኩላቸው የሚሰጠንን ማንኛውም ተልዕኮ ለመቀበልና ህዝባችን ለማገልገል ዝግጁ ነን ሲሉ ለክፍላችን አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

ዘገባው ፦ የመሰረታዊ ፖሊሰ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው
ጥሩብርሃን
በጀግንነት መጠበቅ በሰበዓዊነት ማገልገል!

የሀዘን መግለጫየቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባልደረባ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር አብርሃም ገብረህይወት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ /ደብረ ...
25/04/2026

የሀዘን መግለጫ

የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባልደረባ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር አብርሃም ገብረህይወት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ /ደብረ ማርቆስ ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም

የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባልደረባ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር አብርሃም ገብረህይወት ከዚህ ዓለም ድካም በሞት ተለይተዋል፡፡ ሟች ዋና ኢንስፔክተር አብርሃም ገብረህይወት ከመጋቢት ወር 1997 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣስ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ የአስተዳደር ክፍል ሃላፊ በመሆን ያገለገሉ እንዲሁም በክልልና በፌደራል የፖሊስ ሰራዊት ውስጥ በተለያዩ የስራ ክፍሎች ለ40 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን በአገልግሎት ዘመናቸውም ስራቸውን አጥብቀው የሚወዱ፣ ቅንና ሰው አክባሪ መኮነን ነበሩ፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በዋና ኢንስፔክተር አብርሃም ገብረህይወት ህልፈተ-ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለመላ ቤተሰቡ፣ወዳጅ ዘመድና ጓደኞቹ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

-------------------------ነፍስ ይማር---------------------------

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ

“የትንሳኤ በአል እየሱስ ክርስቶስ  ለእኛ ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ትህትናን እና ይቅርታን ያስተማረበት ታላቅ በዓል ነዉ”ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለየአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝ...
11/04/2026

“የትንሳኤ በአል እየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ትህትናን እና ይቅርታን ያስተማረበት ታላቅ በዓል ነዉ”ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ለመላው የክልላችን ፖሊስ አመራርና አባላት፣ ለአማራ ክልል ፖሊስ ለዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አመራረሮችና አባላት፣ ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የክልላችን ብቸኛው የፖሊስ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ሲሆን ባለፉት 33 ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፖሊስ አመራር፣ ባለሙያ እና አዲስ የፖሊስ አባላትን አስመርቆ ወደ ስራ አሰማርቷል እያሰማራም ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አክለዉም ይህን ተልዕኮውን በአዳዲስ ፕሮግራሞች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዉ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ያለውን ተቋማዊ ሪፎረም ተከትሎ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጃችን ማቋቋሚያ ደንብ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ/ም በአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት እንዲጸድቅ በመደረጉ ለመላው የክልሉ ፖሊስ አመራርና አባላት ለዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ በማለት እየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ለእኛ ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ትህትናን እና ይቅርታን እንዳስተማረን ሁሉ እኛም እርስ በዕርስ በመዋደድ በይቅርታና በመከባበር የጀመርነውን የተቋማችን ትንሳኤ በውጤታማነት ለማስቀጠል ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ ሲሉ አሳስበዋል፡፡በመጨረሻም በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸዉን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት
መልካም በዓል!!!

ሚያዚያ 2018 ዓ/ም ደብረ ማረቆስ
በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

Address

Debre Markos
Debre Mark'os

Telephone

+251587714223

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ /Amhara Region Police University College/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share