23/07/2023
#ፔድረስ ደርመታይቲስ( Paederous Dermatitis )
በቅድምያ በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ በማድረስ ከበሽታው ይታደጓቸዉ!
?
#መንስኤ
ፔድረስ ደርመታይቲስ ህመም መንስኤዋ ነፍሳት ክረምትና ቀዝቃዛ አየርን ተከትላ በምትራባ ነፍሳት ምክንኛት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው። በተለምዶው ናይሮቢ ፍላይ በመባል የምትታወቀው ነፍሳት ብርሐን አቅራቢያ ብዙውን ጊዜ የጣራ ኮርኒስ ላይ ትገኛለች። በሀረጋችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ይህ የቆዳ ህመም ሪፖርት ተደርጓል።
?
ናይሮቢ ፍላይ አትናከስም አትናደፍም። በውስጧም ፔድሪን የሚባል ለቆዳ መርዛማ የሆነ ኬሚካል ይዛለች። ቆዳችን ላይ እያለች በእጃችን ጣቶች፣ በልብሳችን ወይም በማንኛውም ነገር መጨፍለቅ ሲገጥማት ከሰውነቷ ሚያመልጠው ፔድሪን የተሰኘው ኬሚካል ነው የቆዳ ህመሙን ሚያስከትለው።
የቆዳ መቅላት፣ የተለያዩ የቆዳ ሽፍታ አይነቶች፣ እብጠት፣ የማሳከክ ስሜት እንዲሁም ካልታከመና የግለሰቡ የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ ከሆነ የተለያዩ የቆዳ ህመሞችን ልታስከትል ትችላለች። እነዚህ ምልክቶች ያሉት ሰው በሚያድርበት አካባቢ ይህችን ነፍሳት መኖርዋን ማረጋገጥና ማራቅ ለቆዳ ህመሙ ሐኪም ማማከር ይኖርብናል።
?
ናይሮቢ ፍላይ በመባል ምትታወቀው ነፍሳት ቁመቷ ከ7_10 ሚሊሜትር ሲደርስ በቅደም ተከተል የተደረደሩት ቀይና ጥቁር ቀለማት በቀላሉ ከሌሎች ነፍሳት መለየት ያስችሉናል
Paederus sabaeus(Nairobi or narrow bee fly . aka. rove beetles)
ከጣሊያኑ እግር ኳስ ክለብ ባንዲራ ቀለማት ጋር ካላት መመሳሰል የተነሳ አንድ አንድ አካባቢዎች ኤስ ሚላን በመባል ትታወቃለች::
ይህች ነፍሳት በተደጋጋሚ በምኖርነት አሶሳ አካባቢ ትስተዋላለች ቁጥራቸውን መናገር ባይቻልም ብዙ ሰዎችንም አጥቅታለች። ህመሙ ከ5 _ 10 ቀናት በሚቆይ የቆዳ ቁስል ሊወሰን ቢችልም ለበርካታ የቆዳ ህመሞች ስለሚያጋልጥ ችላ ሊባል አይገባም
ይህንን ህምም ያለ ምንም ወጪ መከላከል እንችላለን። ቁልፍ ከላይ ያለውን ምስል በመመልከት ነፍሳቷን መለየትና የምንተኛበትን፣ የምንቀመጥበትን ቦታዎች በማራቃ ነፍሳቷንም ከስፍራው ቆዳችንን ሳትነካን ማሶገድ ያስፈልጋል። ያልጋ አጎበር መጠቀምም ጠቃሚ ይሆናል። ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ ሰዎችንም ያስገንዝቡ።
1. የህመሙ መንስኤ የሆነችውን ነፍሳት መለየት መቻል።
2. ወደ ማረፊያ ቦታዎቻችን እንዳትገባ በርና መስኮት መዝጋት።
3. የአልጋ አጎበር መጠቀም።
4. ሰውነታችን ላይ ካየናት በርጋታ ቀስ ብሎ ማንሳት።
5. የቤት ውስጥ ብርሀን ነፍሳቶቹን ስለሚስብ ከመተኛታችን በፊት አላስፈላጊ የሆኑ መብራቶቻችን ማጥፋትና በየሱቁ የሚገኙ ፀረ ተባይ ስፕሬይ መጠቀም ያስፈልጋል::
በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ በማድረስ ከበሽታው ይታደጓቸዉ!