Dandii Boru College Dessie Campus

Dandii Boru College Dessie Campus Dandii Boru College is of privately-owned by higher learning institutions in the country.
(1)

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተ...
12/08/2026

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከነሀሴ 13 እስከ 15/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦
1.የፈተናው መርሃ-ግብርም፦
-በ13/12/2018 ዓ.ም…… Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Environmental Health, Human Nutrition, Emergency and Critical Care Nursing, Dental Medicine እና Optometry
-በ14/12/2018 ዓ.ም…………, Medical Laboratory Science, Public Health, Midwifery, Medical Radiology Technology, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing, Physiotherapy እና Surgical Nursing
-በ15/12/2018 ዓ.ም…… Nursing
ሁሉም ተፈታኝ ነሀሴ 12/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::
2.በፈተናው ወቅት የብሄራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print out ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
3.ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎችን፣ እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
4.በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
5.በተጨማሪም ከስር የተያያዘውን የፈተና ሂደቱን የሚያሳይ ቪዲዎ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
6.ተመዛኞች ወደ ጣቢያ ከመምጣታችሁ በፊት ከዚህ ማስታወቂያ በታች የተያያዘውን ዚፕፋይል በመክፈት የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያ መመልከት ይኖርባችኋል።
ማሳሰቢያ፦
ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

የፈተና ጣቢያ መረጣ ዛሬ ይጠናቀቃል!ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና፣ የተመዛኞች የፈተና ጣቢያ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ ዛሬ ሐምሌ 30/2018...
06/08/2026

የፈተና ጣቢያ መረጣ ዛሬ ይጠናቀቃል!

ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና፣ የተመዛኞች የፈተና ጣቢያ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ ዛሬ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በመሆኑም ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዛችሁ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂ ተመዛኞች https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት Fayda and Password በማስገባት በቀሩት ሰዓታት የፈተና ጣቢያ ምርጫ አድርጉ፡፡

ምንጭ፦tikvahuniversity

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

05/08/2026

ኤአይ (AI)ን እንዴት እንጠቀም ?

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለረጅም ጊዜ እና ያለገደብ መጠቀም የሰዎችን የፈጠራ ብቃት እና ነገሮችን በጥልቀት የመመርመና የማሰብ ክህሎትን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በቅርቡ የወጡ ተከታታይ ጥናቶች አመልክተዋል።

​በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች መረጃዎችን እና ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በኤአይ (AI) ላይ ጥገኞች ሆነው ማከናወን ሲጀምሩ " ኮግኒቲቭ ሰረንደር " ወይም የአእምሮን የማሰብ ስራ ለቴክኖሎጂ አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ ይታይባቸዋል።

ይህም አእምሮ በራሱ ጥረት መረጃዎችን የማቀናበር፣ የመተንተን እና አዳዲስ ሀሳቦችን የማመንጨት የተፈጥሮ ብቃቱ እንዲደክም ያደርገዋል።

በተለይ #ወጣቶች እና #ተማሪዎች ለተወሳሰቡ ጥያቄዎች እና ስራዎች ፈጣን ምላሽ ከኤአይ ማግኘት መልመዳቸው የራሳቸውን የአእምሮ አቅም የመጠቀም ተነሳሽነታቸውን እንደሚቀንሰው ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ።

ነገር ግን ቴክኖሎጂውን እየተጠቀሙ አእምሮን ሁል ጊዜ ንቁ፣ ብቁ እና ጤናማ አድርጎ ለማቆየት የሚረዱ በርካታ ሳይንሳዊ መንገዶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።

የአእምሮን የአስተሳሰብ ብቃት ላለማጣት ምን አይነት ልምዶች ማዳበር ይቻላል ?

- ከኤአይ (AI) የተገኙ ምላሾችን ወይም መረጃዎችን በቀጥታ ወስዶ ከመገልበጥ ይልቅ " ይህ መረጃ ትክክል ነው ? ምን ጎደለው ? አመክንዮአዊ ነው ? " በማለት በራስ አእምሮ መርምሮ፣ መዝኖ መጠቀም።

- ማንኛውንም ስራ፣ ጽሑፍ ወይም ፕሮጀክት ከመጀመርዎ በፊት መነሻ ሀሳቦችን እና እቅዶችን በራስ አእምሮ ማመንጨት እና ማስታወሻ መያዝ። ኤአይ ስራውን ለማስጀመር ሳይሆን የተጀመረውን ስራ ለማደራጀት ወይም ለመፈተሽ ብቻ መጠቀም።

- የፈጠራ እና የጥልቅ አስተሳሰብን የሚያነቃቁ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስልታዊ ጨዋታዎችን መጫወት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ ለመማር መሞከር።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች/ስራዎችን ለኤአይ ሰጥቶ ያለ ምንም ምርመራ፣ ማስተካከያና ደጋግሞ የማንበብ ጥረት በቀጥታ #በመገልበጥ አንዳንዴም እንደራስ ስራ ማስመሰል እየተለመደ መጥቷል። ይህ በጥልቀት ሳያስቡና ሳይመራመሩ በቴክኖሎጂ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን አእምሮን የማሰብ ስራውን እንዲተው በማድረግ፣ እውነታን የመተንተን እና የጥልቅ አስተሳሰብ ብቃትን በከፍተኛ ደረጃ እየገደለው ይገኛል ፤ ሰዎች ትንሽ ስራ እንኳን ለመስራት የማይፈልጉ ስልቹና ሰነፍ እያደረጋቸውም ነው።

ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ኤአይ (AI) የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን እንደ ረዳት መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው ነው። ጥቅም የሚኖረውም የሰው ልጅ የራሱን የአስተሳሰብ ልዕልና ጠብቆ ሲቀጥል ብቻ ነው።

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ የ2018ዓ.ም 2ኛዉ ሴሚስተር እና የዓመቱ የማጠቃለያ ሱፐርቪዥን እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሃምሌ 28/2018 ዓ.ም. ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ ዳንዲ ቦሩ ኮሌ...
04/08/2026

የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ የ2018ዓ.ም 2ኛዉ ሴሚስተር እና የዓመቱ የማጠቃለያ ሱፐርቪዥን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ሃምሌ 28/2018 ዓ.ም. ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ

ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ ላለፉት 8 አመታት በተቋሙ ዉስጥ የዉስጥ ጥራትን ለማምጣትና የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር የተለያዩ ስታንዳርዶችን ዘርግቶ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ያለ እና ዘመኑን የሚመጥን ዲጂታላይዝድ አገልግሎት ለመስጠት እራሱን እያበቃ ያለ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡ይሄንን ጉዞዉን ለማሳለጥና የተሸለ ዉጤት ለማምጣት የስራ ክፍሎች በተዘረጋላቸዉ አሰራር እየሰሩ መሆኑን ለመከታተል፣ ለመደገፍና ለማረም ያስችል ዘንድ በኳሊቲ አሹራንሰ ሃላፊ የሚመራ የሱፐርቪዝን ቡድን አዋቅሮ በአመት ሁለት ጊዜ አጠቃላይ ሱፐርቪዥን በማካሄድ የመማር ማስተማሩን ሂደቱን በመገምገም ያጋጠሙ ክፍተቶችን በግብረ መልስ ለስራ ክፍሎች እንዲደርሱ በማድረግና በአሰራር እና በተዘረጋዉ ስታንዳርድ እንዲያስተካክሉ በማድረግ ተቋሙ ከአመት አመት መሻሻል እና ለዉጥ እንዲያሳይ አድርጓል፡፡ በሳላፍናችዉ 7 አመታት የስራ ክፍሎች ጠንካራ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የሱፐርቪዝን ዉጤታቸዉን በመተንተን እና ደረጃ በማዉጣት በስራ ክፍሎች መካከል ጤናማ ፉክክር እንዲፈጠር ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰአት በተቋማችን ዉስጥ ለ12 የስራ እና የትምህርት ክፍሎች የሱፐርቪዝን ቸክሊስት ተዘጋጅቶ የሱፐርቪዝን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የ2018ዓ.ም ሱፐርቪዥን እስካሁን ከሰራናቸዉ ሱፐርቪዢኖች ጠንከር ያለና የኦዲት መንገድን የተከተለ ሲሆን በቀጣይ ለምንሰራዉ ISO Certification እንደ መነሻ ግበአት እንዲሆን በማሰብ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌላዉ የአሁኑን ሱፐርቪዥን ለየት እሚያደርገዉ የሱፐርቪዥን ሂደቱን የሚከታተሉ ታዛቢ ሱፐርቫይዘር መጨመሩ ነዉ፤ ይህም ለታዛቢዎቹ በቅርበት ከሌሎች የስራ እና የት/ት ክፍሎች ምርጥ ተሞክሮ የሚወስዱበት፣ ነገ በሃላፊነት ቢቀመጡ ተቋሙ ሱፐርቪዥን በምን መልኩ እያከናወነ እንደሆነ ልምድ እንዲያገኙ፣ እንዲሁም በየትምህርት እና በየስራ ክፍሎቹ የሚካሄደው ሱፐርቪዥን መጨረሻላይ ውጤቱ ተተንትኖ ደረጃ የሚወጣለት በመሆኑ ሲካሄድ የነበረው ሱፐርቪዥን ወጥነት እና ፍትሃዊነት እንዳለው እንዲያዩ በማሰብ የተደረገ አሰራር ነው፡፡ በዚህም የሱፐርቪዥን ቡድኑ ወጥ በሆነ መንገድ የስራ ክፍሎችን እየገመገመ መሆኑን መረዳት ችለናል እሰካሁን በወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት የ4 የስራ ክፍሎች ሱፐርቪዥን የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ 8 የስራ ክፍሎች በተመሳሳይ መልኩ ሱፐርቫይዝ ይደረጋሉ፡፡ የኳሊቲ ማኔጅመንት ቲሙ ለኳሊቲ አሹራንስ ቡድኑ የሱፐርቪዥን ማድረጊያ ስታንዳርድ እና ቼ ሊስት ላልተዘጋጀላቸው 6 የስራ ክፍሎች ወደፊት ሊለካቸው የሚችል ስታንዳርድ እና ቼክ ሊስት አዘጋጅቶ ይካሄዳል፡፡
ሱፐርቪዥኑ ካለቀ ብኋላ ዉጤት ተተንትኖ የየስራ ክፍሎቹ ውጤት እና ደረጃ የሚገልጽ እና አጠቃላይ ውይይቶች ይካሄዳል በማለት የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ የኳሊቲ አሹራንስ ሃላፊ የሆኑት ሲ/ር ሰላማዊት ገብሬ ገልፀዋል፡፡


የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ የኳሊቲ አሹራንስ ክፍል

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ___የጤና ሚኒስቴር ነሀሴ 13-15 /2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዛችሁ በመጠባ...
03/08/2026

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___

የጤና ሚኒስቴር ነሀሴ 13-15 /2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዛችሁ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች በሙሉ፤ ተመዛኞች ከሀምሌ 27- 30/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን FAYDA and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦
▪ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

▪ በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

ለዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ ምሩቃን እና በመማር ላይ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉከዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ከኮሌጁ ማህበራዊ ሚዲያ ጋር ያላችሁን ትስስር ይመለከታልሃምሌ 24/2018 ዓ.ም. ዳንዲ...
01/08/2026

ለዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ ምሩቃን እና በመማር ላይ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ከዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ከኮሌጁ ማህበራዊ ሚዲያ ጋር ያላችሁን ትስስር ይመለከታል
ሃምሌ 24/2018 ዓ.ም. ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
ደሴ
እንደሚታወቀዉ የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ በምዘገባ ወቀት፣ በትምህርት ላይ እያላችሁ እና በምረቃ ጊዜ በርካታ ጥልቅ የሆኑ ዳታዎችን ከተማሪዎች በመሰብሰብ በኮሌጁ የተማሪዎች ሪከርድስ እና ሪጅስተራር ዳታ ቤዝ ሲስተም ዉስጥ በማስቀመጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች በተለያዩ ጊዜ ሲያስፈልግ አገልግሎት ላይ እየዋለ ትንተና እየተሰራለት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም ዘመኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ኮሌጁ ሌሎች ከላይ ከተጠቀሰዉ ሲስተም በተጨማሪ የኮምፒዉተር ለርኒንግ ማኔጅመንት ስርአት ዘረግቶ በግቢዉ ዉስጥ ማንኛዉም አይነት ፈተናና ምዘና ለሁሉም ተማሪዎቻችን ለእያንዳንዳቸሁ ወደ ሲስተሙ መግቢያ የሚሆን ዩዘር ኔም አካዉንት ተከፍቶላችሁ እና በፈተናዉ ወቀት በየጊዜዉ ዳይናሚክ የሆነ ፓስወርድ እየተሰጣችሁ እንደመትፈተኑም ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተማሪዎች ወርሃዊ ክፍያ ክፍያችሁ ለእያንዳንዳችሁ የአዋሽ ባንክ መክፈያ ስም ዝርዝር ወይም አይዲ ወይም ኮድ ተሰጥቷአችሁ እየከፈላችሁ እንዳለም ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ልዩ ልዩ ወቅታዊ እና ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሷችሁ በሁሉም የኮሌጁ ማህበራዊ ትስስር (ሶሻል ሚዲያ) ሰብስክራይብ እና ፎሎዉ እንድታደረጉ በተደጋጋሚ ማስገንዘባችን ይታወሳል፡፡ አልፎም የስልክ ቁጥር በተቻላችሁ መጠን እንዳትቀይሩ ከቀየራችሁ ደግሞ ሬጅስተራር እየቀረባችሁ update እንድታደርጉ ማሳሰባችንም የሚታወቅ ነዉ፡፡ በመሆኑም ለአስቸኳይ ጉዳይ ስትፈለጉ እነዚህን ሶሻል ሚዲያ መከታተላችሁ በአንደኛዉ ሚዲያ በቀጥታ ስናጣችሁ በሌላኛዉ ሚዲያ በመፈለግ ባላችሁበት አስፈላጊዉን ወቅታዊ፣ ግለሰባዊ ማስረጃ እና አገልግሎት ለማድረስ መሆኑም ጭምር ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ አንዳንድ ተማሪዎች አሁንም ከላይ የተገለጹትን ሁሉ በአግባቡ በቀላሉ ባለመፈጸማቸዉ ለተለያዩ ችግር እየተዳረጋችሁ ትገኛላችሁ ለአብነት ያክል በ17/11/2018ዓ.ም በሚየበቃዉ የጤና ሚኒስቴር የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ በተለምዶ(የሲኦሲ) ምዘና የአንዳንድ ተመራቂዎች የጋጠማቸዉን ችግር ለመፍታት ከጤና ሚኒስተር ጋር በመነጋገር በተለይም የOTP ሜሴጅ ያልደረሳቸዉን ፣ ስማቸዉ ወደ ጤና ሚኒስትር መጫን የተቸገሩትን፣ ከ2015 ዓ.ም. በፊት የጤና ሚኒስቴር በወረቀት ምዘና ይሰጥ በነበረበት ወቅት ሁሉ የጤና ሚኒስቴርን የሙያ ፈቃድ ምዘና በተለያየ ምክኒያት ሳትፈተኑ የቀራችሁ እና አሁን ለመፈተን ስትሞክሩ ዳታችሁ በጤና ሚኒስቴር የመረጃ ቋት ውስጥ ያልተገኛችሁ ወዘተ… ኮሌጁ እናንተን ለማገዝ በሚፈለግበት ወቅት ልናግዛችሁ አልተቻለም፡፡ ለምሳሌ ያክል ከነርስ የ2014ዓ.ም ተመራቂዎች ዉስጥ አለምነሽ አዲሴ እና ሷሊህ መሀመድ ፋይዳ ቀይራችሁ ባለመያዛችሁ፣ ከፋርማሲ የት/ት ክፍል ተመራቂ ወይንሸት ባየ እና እስማኤል መኮነን ስልክ ቀይራችሁ ባለመስራቱ የሚያስፈልጋችሁን መረጃ በጊዜዉ እና በወቅቱ ቢደወልላችሁም እንዲሁም ከኮሌጁ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ፈልገን ልናገናችሁ ብንሞክርም አልተሳካም ነበር፤ በሌላ በኩል የነርስ ት/ት ክፍል የተመራቂ ተማሪ ሷሊህ መሀመድ አወል የሜዲካል ላበራቶሪ ት/ት ክፍል እና የተመራቂ ተማሪ ሉባባ ሰይድ የስልክ ቁጥር በመሳሳቱ ከጤና ሚኒስቴር ሊደርሳቸዉ ያልቻለዉን ኦቲፒ () ቴክስት ከኮሌጁ እንዲደርሳቸዉ ለማደረግ ተችሏል፡፡ በዚህም ለመመዝገብ በቅተዋል፡፡ በሌላ በኩል ከ2014 ዓ.ም. የነርስ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ደስታ አዲስ ደርብ በወቅቱ 1 ጊዜ ብቻ በወረቀት ተመዝና ከዛ በኋላ ባለመመዘኗ ስሟን በጤና ሚኒስቴር የመረጃ ቋት ውስጥ ማግኘት አልተቻለም በመሆኑም ኮሌጁ በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ በየትኛውም ቦታ ሆናችሁ የሚፈለገውን አገልግሎት በሚፈለገው ጊዜ፣ ጥራት እና መጠን እንዲሰጣችሁ
1ኛ) ሁሉም በመማር ላይ ያለችሁም ተማሪዎች ሆናችሁ የተመረቃችሁ ተማሪዎች ሁሉንም የኮሌጁን ሶሻል ሚዲያዎች እንድትከታተሉ እና አባል እንድትሆኑ
2ኛ) ሁሉም በመማር ላይ ያላችሁም ሆናችሁ ለተለያየ አገልግሎት ወደ ኮሌጁ የምትመጡ የቀድሞ ምሩቃን የፋይዳ እና የስልክ ቁጥራችሁን መረጃ ለኮሌጁ ሬጅስተራር ጽ/ቤት እንድታስመዘግቡ፡፡
3ኛ) ስትመዘገቡ ያስመዘገባችሁትን ስልክ ቁጥር የቀይራችሁ ሰልክ ቁጥራችሁን እንድታስመዘግቡ
4ኛ) ሁሉም በመማር ላይ ያላችሁ ተማሪዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅማችሁን ባላችሁበት እንድታሳድጉ በተለይም የኢትዮ ኮደርስ ፣ የአማራ ዲጂታል ኢኒሺየቲቭ ተብለው የተጀመሩትን ፈጽማችሁ ሰርተፍቲኬቱን ያሊሲያዛችሁ ተማሪዎች በ2019ዓ.ም ምዝገባ ወቅት ይዛችሁ እንድትመጡ በማለት በጥብቅ እያሳሰብን ማንኛዉም ጥያቄአችሁን በኮሌጁ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ የሚጠየቁ ጥያቄዎችንም ደግሞ እንደ የት/ት ክፍላችሁ እና እንደ የስራ ክፍላችሁ የኮሌጁ የተለያዩ ክፍሎች ሃላፊዎች ፈጣን መልስ እንድትሰጡ በማልት እናስታዉቃልን፡፡

‹‹ትክክለኛ መረጃ በትክክለኛ ጊዜ ከትክክለኛ ክፍል ለትክክለኛ ተገልጋይ››!!

ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ!!

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

Dandii Boru College is of privately-owned by higher learning institutions in the country.

የጤና ሚኒስቴር ፈተና  /COC/ ለምትወስድ የጤና ተማሪዎች በሙሉ "Your registration has been rejected, Please upload a clear and valid copy of ...
30/07/2026

የጤና ሚኒስቴር ፈተና /COC/ ለምትወስድ የጤና ተማሪዎች በሙሉ
"Your registration has been rejected, Please upload a clear and valid copy of your Temporary Degree Certificate.---Ethiopian Health Professionals Licensing Examination!"
የሚል ሜሴጅ ሲመጣባችሁ ቴምፖ የማይታይ እና መስተካከል ስላለበት ስለሆነ በድጋሚ አስተካክላችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡
Students whose document were rejected because they uploaded unclear or unreadable temporary degree
So upload a clear, readable, and visible temporary degree certificate when resubmitting their document.
ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

Dandii Boru College is of privately-owned by higher learning institutions in the country.

ለሪሰርች የተመረጡ ርዕሶችን ስለማሳወቅሀምሌ 20/2018 ዓ.ምዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹በቴሌግራም_አድራሻችን👇'=> https://t.me/dandiibo...
27/07/2026

ለሪሰርች የተመረጡ ርዕሶችን ስለማሳወቅ
ሀምሌ 20/2018 ዓ.ም
ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

  የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡የመመዝገቢያ ሊንክ 👇...
25/07/2026



የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

የመመዝገቢያ ሊንክ 👇
https://ngat.ethernet.edu.et

ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር ሲሆን፤ በምዝገባ ወቅት በቴሌብር በኩል መክፈል ይጠበቅባችኋል።

ምዝገባው በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወን መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ፤ የፈተና ጣቢያዎች ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ የሚወሰን መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦tikvahuniversity

ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

የስራ ክፍሎችን ሱፐርቪዥን ፕሮግራም ስለማሳወቅ
24/07/2026

የስራ ክፍሎችን ሱፐርቪዥን ፕሮግራም ስለማሳወቅ

Address

Dandii Boru
Dessie

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00

Telephone

+251331122753

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dandii Boru College Dessie Campus posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Dandii Boru College Dessie Campus:

Shortcuts

Share