27/12/2022
ሰርጂዮ ራሞስ: "ከአለም ዋንጫ አሸናፊው ጋር ለማውራት መጠበቅ አልቻልኩም።"
"ለአለም ዋንጫው ጉልበቱን ሲቆጥብ ቆይቷል። እናም ተመልክተነዋል። አሁን PSG ቁጭ ብሎ ወደኋላ በመመለስ ሊዮኔል ሜሲ ያሳለፈውን ታሪክ መመልከት አለበት። አሁን ክለቡ PSG የቻምፒየንስ ሊግ ህልሙን እንዲያሳካ ለመርዳት ብቻ ነው እንጂ ለምንም አይነት ሽልማት ብሎ አይጫወትም። የአርጀንቲናን የረጅም ጊዜ ህልም አሳክቷል አሁን የፒኤስጂን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የማሸነፍ ህልም ለማሳካት ያለውን አቅም ሁሉ ይሰጣል። ከዚያም በኋላ ጫማውን ለመስቀል አያስብም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከፍተኛ ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ከአውሮፓ ሊጎች የመውጣት ፍላጎት ያለው አይመስለኝም። ወደ ሌላ ሀገር ከመሄድ ይልቅ በቻምፒዮንስ ሊግ እየተጫወተ የእግርኳስ ህይወቱን ቢያጠናቅቅ ደስ እንደሚለው ተናግሯል።"