Dilla University

Dilla University Dilla University, often referred as 'University of the Greenland' due to the greenery in and around.

06/09/2026

ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው ብዝሃ መር የኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው

ዲላ፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው ብዝሃ መር የኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።

ቀደም ሲል በግብርና መር ኢኮኖሚ ልማት ላይ ተወስና የቆየችው ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት ወደ ብዝሃመር የኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ ተሸጋግራለች።

የኢትዮጵያን እምቅ የመልማት አቅሞች በመገንዘብ የግብርና ልማትን ጨምሮ በኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ አይሲቲና የማዕድን ዘርፍ ዋነኛ የልማት ምሰሶዎች ሆነው እየተሰራባቸው ይገኛሉ።

በእነዚህ ዘርፎችም ላይ በተሰሩ ስራዎች ሀገሪቱ እመርታዊ እድገትና ማንሰራራት ላይ ለመሆኗ በርካታ ተጨባጭ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንትና የተፈጥሮ ሃብት ተመራማሪ ሐብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፤ የልማት ስትራቴጂው ብዝሃ መሆኑ እና ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መደረጉ ለተመዘገበው ስኬት የላቀ ትርጉም አለው ብለዋል።

የብዝሃ ኢኮኖሚ እድገት አማራጭን ከመከተል ባለፈ በተለይም በግብርናው ዘርፍ አዳዲስ ኢንሼቲቮችን በመተግበርና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ እመርታ መታየቱን አስረድተዋል።

በስንዴ ልማት፣ በቡና ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች የግብርና ዘርፎች ውጤቱና ስኬቱ አስደናቂ መሆኑን ነው ያነሱት።

የተፈጥሮ ሃብትና መሬት አስተዳደር ተመራማሪና የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት ፤ እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶችን በመጠቀም እየተሄደበት ያለው የልማት ዕቅድ በአጭር ጊዜ ውጤት አምጥቷል።

በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተጀመረው የተቀናጀ የልማት ጥረት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነትና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት መሆኑን አንስተዋል።

ከመደበኛ የምርት ወቅት በተጨማሪ የመስኖ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸው፣ የዘርፉ እመርታ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የታየው እመርታ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት ለመውጣትና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሰረት የሚጥል መሆኑን ምሁራኑ ገልጸዋል።
Ethiopian News Agency #ኢዜአ

05/09/2026

Dear Grade 12 Students!

Warm congratulations and best wishes as you begin the new 2019 E.C. academic year!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

As you take an important step toward shaping your future, we proudly invite you to choose Dilla University as the place where your dreams can become reality.

Dilla University stands out as a preferred destination for higher education for many compelling reasons:

🌼 A Peaceful and Conducive Environment:
The university is located in a safe, welcoming, and student-friendly setting that promotes academic success and personal growth.

🌼 Proven Academic Excellence:
Renowned for its outstanding teaching and learning practices, Dilla University has earned widespread recognition for delivering quality education.

🌼 Modern ICT Infrastructure:
Students benefit from well-developed and up-to-date information and communication technology facilities that support effective learning and innovation.

🌼 Smart and Technology-Enhanced Classrooms:
Our modern classrooms are equipped with advanced educational technologies designed to provide an interactive and enriching learning experience.

🌼 Highly Qualified and Experienced Faculty:
The university is staffed by competent, experienced, and dedicated scholars committed to helping students achieve academic excellence.

🌼 Well-Equipped Laboratories:
A wide range of modern laboratories provides students with valuable practical and research-oriented learning opportunities.

🌼 Market-Relevant Academic Programs:
Dilla University offers numerous fields of study that are highly demanded in today’s job market, preparing graduates for successful careers and future leadership.

✅ A City That Feels Like Home!

Dilla, the home of Dilla University, is one of Ethiopia’s most attractive and livable cities. Known for its pleasant climate, welcoming community, and vibrant atmosphere, the city provides an ideal environment for students to live, learn, and thrive.

Students who choose Dilla University are not only investing in quality education but also becoming part of a supportive and dynamic community.

The university leadership, together with the local community, warmly welcomes you to our prestigious institution, often described as a "Mini Ethiopia" because of its rich diversity and inclusive culture.

We are committed to providing you with the support, guidance, and opportunities you need to succeed throughout your academic journey.

🎯 Choose Dilla University. Invest in your future. Achieve your dreams.

Join us and become part of a vibrant academic community dedicated to excellence, innovation, and success.

🎯 Dilla University: Where Dreams Become Achievements.

Choose Dilla University today and take the first step toward a bright and successful future.

=== # # #===




Regular Research Proposal Defense Held at Dilla University============*************============  DU: Nehase 30, 2018 E.C...
05/09/2026

Regular Research Proposal Defense Held at Dilla University
============*************============

DU: Nehase 30, 2018 E.C. (PIR)

Dilla University has conducted its 2019 Regular Research Proposal Defense Session, with presentations held under the institution’s five core research themes.

Over the two-day program, scholars presented proposals designed to address pressing challenges and offer practical solutions, undergoing rigorous review and evaluation across multiple stages.

Habtamu Temesgen (PhD), Vice President for Research and Technology Transfer, emphasized the university’s commitment to supporting researchers with the resources they need.

He noted the growing participation of faculty members in research activities and highlighted the importance of strengthening problem-solving projects that can inform science, policy, and society.

He further pointed out that the university is advancing digital systems to modernize research processes, including proposal calls, evaluations, and related procedures, reducing reliance on paper based methods.

Misganu Legesse (PhD), Director of Research, Publication, Ethics, and Dissemination, remarked that this year’s program was conducted earlier than usual, ensuring researchers have sufficient time and support to refine their work.

He confirmed that 113 proposals were presented and evaluated under the five thematic areas, reflecting the university’s focused research agenda.

The sessions brought together college and department leaders, research coordinators, and evaluators, underscoring Dilla University’s growing research culture and institutional commitment to academic excellence.

=== # # #===



በዩኒቨርሲቲው የሰለጠኑ ከ300 በላይ የስቴም ማዕከል ሰልጣኞች ተመረቁ===========***********===========ዲ.ዩ: ነሐሴ 30/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2018...
05/09/2026

በዩኒቨርሲቲው የሰለጠኑ ከ300 በላይ የስቴም ማዕከል ሰልጣኞች ተመረቁ
===========***********===========

ዲ.ዩ: ነሐሴ 30/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2018ዓ.ም በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች በስቴም ማዕከል የሰለጠኑ ከ300 በላይ ሰልጣኞች ተመርቀዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር አዲሱ ፍርንጆ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ማዕከሉ ባጠቃላይ ከ3500 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን እና የማዕከሉ ምሩቃንም ባሁኑ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አክለውም በዛሬው ዕለት የተመረቁ ከ300 በላይ ተማሪዎች በክረምት፣ በሳምንቱ መጨረሻ እንዲሁም በጂኦስፖሻል ስልጠናና በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናውን ተከታትለው ለምረቃ መብቃታቸውን ጠቁመዋል።

ማዕከሉ ጥራት ያለው ስልጠናዎችን ስለሚሰጥ፣ ባሳለፍነው ዓመት በEmerging technology በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ጠቁመው፣ ተማሪዎች የሳይንስ ፈጠራ እውቀታቸው እንዲጎለብት ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ አውስተዋል።

ሰልጣኞች እዚህ ያገኙትን እውቀት ወደየ ትምህርት ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለሌሎችም እንዲያካፍሉ እና የሳይንስ ፈጣሪ ዜጎችን እንዲፈጥሩም አደራ ብለዋል። በቀጣይ ዓመት ወደ ማዕከሉ ሲመጡም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ይዘው እንዲመጡ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጳውሎስ በበኩላቸው፣ የጅኦስፓሻል ስልጠና በሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለመፍጠር ባለድርሻ አካላት ተባብረው ያዘጋጁት እንዲሁም የሚደግፉት ስልጠና መሆኑን አውስተዋል። ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ረገድ ተጽህኖ ፈጣሪ ዜጎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፀው፣ ዩኒቨርሲቲው በትውልድ ላይ እየሰራ ላለውና እየተመዘገበ ላለው የሚጨበጥ ለውጥ በክልሉ ስም አመስግነዋል።

በተለይ በክረምቱ የተሰጠው የጂኦስፓሻል ስልጠናን በየዓመቱ ለመስጠት እቅድ ስለመኖሩ የገለፁት ኃላፊው፣ የሰለጠኑ ተማሪዎች እድሉን ላላገኙ ወንድሞቻቸው ያገኙትን እውቀት እንዲያገሩ አደራ ብለዋል።

የጌዴኦ ዞን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደረጄ ሾንጣ ተመራቂ ተማሪዎችን እንኳን ለምረቃ ቀናችሁ አደረሳችሁ ብለዋቸዋል። ኃላፊው አክለውም በዚህ ጊዜ ላይ ዓለም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ውድድር ላይ እንደምትገኝ ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ላይ በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን በልዩ ትኩረት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ጊዜያት ላይ እንደ ሀገር የተያዘው እቅድ ከግብ እንዲደርስ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አውስተዋል።

ወቅቱ ቴክኖሎጂ የየለት ስራዎቻችን ጋር የበለጠ የተቆራኘበት በመሆኑ፣ ተማሪዎች ከዚህ ሲመለሱ ማህበረሰቡ ጋር ያሉ ችግሮችን በቅርበት በመከታተል ንድፈ ሀሳብ በማዘጋጀት ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን እንዲያስቡ ጥሪ ያቀረቡት ኃላፊው ዞኑ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ አካላት ድጋፍ እንደሚያደርጉ አውስተዋል።

በመድረኩ ለ45 ቀናት በስፔስ እና ጂኦስፓሽያል ዘርፍ ላይ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ተማሪዎችም ተመርቀዋል። በስልጠናው ወቅት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

=== # # #===



Wonago-HDSS Represents Dilla University at Landmark National Health Surveillance MoU============**********===========DU:...
05/09/2026

Wonago-HDSS Represents Dilla University at Landmark National Health Surveillance MoU
============**********===========

DU: Nehase 30/2018 E.C (PIR)

Dilla University’s Wonago Health and Demographic Surveillance System (Wonago-HDSS) has marked a historic milestone in national health research by signing a Memorandum of Understanding (MoU) with leading health institutions and academic partners in Addis Ababa.

The event, organized under the Impact HDSS Ethiopia Project, brought together senior officials from the Ministry of Health, the Ethiopian Public Health Institute (EPHI), and representatives from 14 public universities, one college, and 15 surveillance sites. Collectively, the network monitors health and demographic data for nearly 1.4 million people across more than 256,000 households, strengthening Ethiopia’s evidence base for public health policy.

In his opening remarks, Dr. Mesay Hailu, Director General of EPHI, underscored the importance of integrating surveillance centers through standardized digital platforms to improve cause-of-death reporting, disease surveillance, and outbreak response. He acknowledged the pivotal support of the Bill & Melinda Gates Foundation and Vital Strategies in advancing this initiative.

Dr. Muluken Argaw, Strategic Lead Executive Office Director at the Ministry of Health, emphasized that the new network creates a direct bridge between community-generated population data and national health strategies, ensuring that local realities inform policy decisions.

Representing Dilla University, Dr. Habtamu Temesgen, Vice President for Research and Technology Transfer, signed the MoU on behalf of Wonago-HDSS and contributed to high-level panel discussions.

He highlighted the strategic importance of building a national network for evidence-based policymaking, stressing that data quality must remain a top priority. Dr. Habtamu further urged leaders to address capacity gaps by ensuring all HDSS sites, particularly new centers, have dedicated data managers to safeguard integrity and reliability.

Through this landmark partnership, Dilla University reaffirms its commitment to impactful population health research and institutional excellence, positioning Wonago-HDSS as a vital contributor to Ethiopia’s national health surveillance system.

=== # # #===




መላው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንኳን ለ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!የወደፊት ህልምዎን እውን ለማድረግ ዲላ ዩኒቨርሲቲን መርጠው እንዲማሩ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን!...
04/09/2026

መላው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንኳን ለ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!

የወደፊት ህልምዎን እውን ለማድረግ ዲላ ዩኒቨርሲቲን መርጠው እንዲማሩ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

ዩኒቨርሲቲያችን በአራቱም የትምህርት መስኮቹ ማለትም:

✅ በጤና ሳይንስ፣
✅ በግብርና፣
✅ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንዲሁም
✅ በመምህራን ትምህርት ዘርፍ ተፈላጊ የሆኑ ፕሮግራሞችን በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በርካታ አዳዲስ ስርዓተ ትምህርቶችን እየቀረፀ እንዲሁም ነባሮቹን በመከለስ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲን ተመራጭ የሚያደርጉ አንኳር ምክንያቶች

📍ሰላማዊ እና ምቹ አከባቢ ላይ መገኘቱ
📍በመማር ማስተማር ስነ ዘዴው በብዙዎች የተመሰከረለት የትምህርት ጥራት አምባሳደር መሆኑ
📍 በቂ እና ዘመኑን የዋጀ የICT መሠረተ ልማት የተሟሉለት መሆኑ
📍ጥራት ባላቸው እና በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች የተደራጁ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ባለቤት መሆኑ
📍በቂ እና ልምድ ባላቸው ምሁራን ትምህርት እየሰጠ መሆኑ
📍ዘመናዊ የመማሪያ ቤተሙከራዎች የተደራጁለት መሆኑ
📍በገበያው ላይ ተፈላጊ የሆኑ በርካታ የትምህርት ዓይነቶችን የሚያስተምር መሆኑ እውነትም ተመራጭ ያደርገዋል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት ዲላ ከተማም ለኑሮ ተስማሚ፣ እጅግ ተመራጭ እና ተወዳጅ መሆኗ፣ ተቋማችንን መርጠው የሚመጡ ተማሪዎችን እውነትም እድለኛ ያደርጋቸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የአከባቢው ማህበረሰብም 'ትንሿ ኢትዮጵያ' ወደሆነው አንጋፋው ተቋማችን ስትመጡ፣ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ዝግጁ ናቸው።

🎯 ኑ ህልምዎን እውን ያድርጉ፣ ያተርፉበታል።
🎯 መረጃውን ለጓደኞችዎ ያጋሩ!

ዲላ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ!

=== # # #===


!


Research Proposal Defense Underway at Dilla University============**********============  DU: Nehase 28, 2018 E.C. (PIR)...
03/09/2026

Research Proposal Defense Underway at Dilla University
============**********============

DU: Nehase 28, 2018 E.C. (PIR)

Dilla University has opened its Regular Research Proposal Defense Session for 2019 E.C, a flagship academic event where 113 proposals will be presented and reviewed under the institution’s five core research themes.

University officials emphasized that this year’s defense is proceeding on schedule, a timely move that ensures research projects begin without delay and that grants are released as planned.

The first day of the session featured defenses under Theme 3: Health and Well‑Being, and Theme 4: Quality Education, reflecting the university’s commitment to advancing public health and educational excellence.

Defenses will continue with proposals under Theme 1: Agricultural Productivity and Sustainability, Theme 2: Natural Resources and Environment, and Theme 5: Transdisciplinary Research.

The program is scheduled to run through Saturday, offering scholars a platform to receive constructive feedback, strengthen their proposals, and contribute to the university’s growing research culture.

=== # # #===



Proposal presentation!
02/09/2026

Proposal presentation!


📢አዲስ ማስታወቂያ🔔====********====በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን ላይ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም (Postgraduate Program)በመደበኛ እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ መር...
02/09/2026

📢አዲስ ማስታወቂያ🔔
====********====

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን ላይ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም (Postgraduate Program)በመደበኛ እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ መርሀ ግብር ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ ተማሪዎች ከነሐሴ 28/2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 06/2019ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ አለያም በዚህ ማስፈንጠሪያ https://portal.du.edu.et ገብታችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።

የምንሰጣቸውን የትምህርት ዓይነቶችን ይመልከቱ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ።

መረጃውን ለጓደኞችዎ ያጋሩ!

=== # # #===


!

📢ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ🔔========*******========ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የአካዳሚክ ቅጥር ማስታወቂያ ላይ ለመመዝገብ...
02/09/2026

📢ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ🔔
========*******========

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የአካዳሚክ ቅጥር ማስታወቂያ ላይ ለመመዝገብ የምትፈልጉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሰው የመመዝገቢያ ማስፈንጠሪያ https://srms.du.edu.et/duthvacancy እየገባችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

መረጃውን ለጓደኞችዎ ያጋሩ!

=== # # #===


!

Address

South Ethiopia Region
Dilla
419

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30
Saturday 08:00 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Dilla University:

Shortcuts

Share