11/02/2026
መጥኖ የሰራሽ ጥበቡን አብዝቶ
ሁለመናሽ መሳጭ እንከን የለሽ ከቶ
የአጋጣሚ ጉዳይ የዘመን ስልጠና
የእግዚአብሔር ፍቃድ አንቺን አመጣና
የውበትሽ ሳያንስ ትህትናሽ በልጦ
ልቤ አንቺን ይላል ከኔ አንቺን መርጦ
ለበረሃው ልቤ እንደ ሰማይ መና
ለተጎዳው ጎኔ ጠጋኙ ሆንሽና
የግራዬ ጉድለት መጠኑ ሲለካ
የጎደለው አጥንት አንቺ ነበርሽ ለካ
በጣም ነው ምወድሽ የኔ ወገብ ችቦ
ዕጣ ያገናኘኝ ካለሁበት ስቦ
በሰላም በፍቅር ኑሪልኝ በደና
አጊኝቼ እስካቅፍሽ እናፍቃለሁ ገና