Yonas tesfaye

Directions

Yonas tesfaye Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yonas tesfaye, College & University, Dire Dawa.

06/09/2026

ወርኀ ጳጉሜን

መ/ር ጌታቸው በቀለ

ጳጉሜን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (ካላንደር) የዓመቱ የመጨረሻዋ እና ፲፫ኛዋ ወር ናት። “ጳጉሜን” የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” (Epagomene) ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲኾን ትርጉሙም “ትርፍ” ወይም “ጭማሪ” ማለት ነው፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(፲፱፻፵፰)፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት ሐዲስ፡፡ ገጽ 905/፡፡ደስታ ተክለ ወልድ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት በሚለው መጽሐፋቸው “ጳጉሜን የወር ስም፣ ዐሥራ ሦስተኛ ወር፣ ተረፈ ዓመት፣ በነሐሴ መጨረሻ በሦስት ዓመት አምስት አምስት፤ በዐራት ዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ ስድስት የሚሆን ሲሆን፤ ትርጓሜውም ጭማሪ ማለት ነው፡፡” /ገጽ 1223/ በማለት ይገልጹታል፡፡

ወርኀ ጳጉሜን እንደሌሎቹ ወራት ፴ ቀናት ሳይሆን በአራት ዓመት አንዴ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት ቀናት ሲኖራት፤ በዘመነ ማርቆስ፣ በዘመነ ሉቃስና በዘመነ በማቴዎስ ደግሞ አምስት ቀናት ብቻ ይኖራታል፤ ነገር ግን የዓመቱ ዐሥራ ሦስተኛ ወር ተደርጋ ትቆጠራለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የዐሥራ ሦስት ወራት ጸጋ (Thirty months of sun shine) በመባል ትታወቃች፣ ትለያለች፡፡ /Enclopedia of Aethiopica. Vol II./

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ወርኃ ጳጕሜን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ ይህም ጳጉሜ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ መሸጋገሪያ እንደኾነች ሁሉ፤ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፣ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፣ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነትና ነው፡፡ ጳጉሜ የክረምቱ ማብቂያ እንደኾነች ሁሉ፤ ምጽአትም በመጨረሻው ዘመን መከራ የሚበዛበት የዚህ ዓለም ማብቂያ ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜ አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ጻድቃን አዲሲቷን ምድር (መንግሥተ ሰማያትን) ለመውረስ ተዘጋጅተው “ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” የሚባሉባት ናት፡፡

የፈቃድ ጾም በወርኀ ጳጉሜን
በወርኀ ጳጉሜን በርካታ ሰዎች የፈቃድ ጾም ይጾማሉ፣ ጠበል ይጠመቃሉ፡፡ በወርኀ ጳጉሜን የሚጾመውን ከዮዲት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይኸውም፡- ዮዲት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በባቢሎን በከለዳውያን የነገሠው ናቡከደነፆር የተባለው ኃያል ንጉሥ በነበረበት ዘመን የተገኘችና ሕዝበ እስራኤልን በቅኝ እንዳይገዛ ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደሱንም እንዳያጠፋ ትልቅ ተጋድሎ የፈጸመች እስራኤላዊት ሴት ነች፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ መፍትሔ ይሰጣቸው ዘንድ በጾም፣ በጸሎት፣ በልቅሶም ልመናዋን አቀረበች፡፡ እግዚአብሔርም የመፍትሔውን አቅጣጫ አመለከታት፡፡ ለጦርነት የወጣውንም የናቡከደነጾር ቢትወደድ የሆነውን ሆሎፎርኒስን ድል አደረገች፡፡ ሕዝቦቿን ቅድስቲቱንም ከተማ ከጥፋት ታደገች፡፡
ዛሬም ምእመናን እግዚአብሔር አምላክ የዮዲት ጾምና ጸሎት ሰምቶ ኢየሩሳሌምንና ሕዝቦችዋን ከጥፋትና ከመከራ እንደዳናቸው፣ ያለፈ በደላቸውን ደምስሶላቸው አዲሱን ዘመን የደስታና የተድላ፣ የድልና የስኬት፣ የቅድስናና የበረከት ያደርግላቸው ዘንድ የፈቃድ ጾም ይጾማሉ፡፡
በጳጉሜን ጠበል መጠመቅ
በወርኀ ጳጉሜን ሌላው ጎልቶ የሚታየው ምእመናን በየአጥቢያቸው በሚገኝ ቤተክርስቲያን በመሄድ ጠበል ይጠመቃሉ፡፡ ጠበል መጠመቁ ሃይማኖታዊም፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው፡፡ በጳጉሜን ጠበል የመጠመቁ ምክንያቱ ምንድን ነው? ስንል፡-
የመጀመሪያው ምእመናን ከበሽታ ለመዳን ይጠመቃሉ፡፡ ሰዎች በሥጋዊ ሕመም ሲያዙ ጠበል ተጠምቀው ከሕመማቸው ይፈወሳሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም እንደተገለጸው ንዕማን በዮርዳኖስ ጠበል ተጠምቆ ከበሽታቸው ተፈውሷል /፩.ነገ.፭፥፩/፡፡ ኢዮብም በዮርዳኖስ ተጠምቆ እንደተፈወሰ መምህራን በትርጓሜ መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ሁለተኛው ቅዱስ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” እያለ ያስተምርና የንስሐ ጥምቀት ያጠምቅ ነበር፡፡ ዛሬም ይህን ለማስታወስ ምእመናን በጳጉሜን ወር ይጠመቃሉ፡፡ ሦስተኛው በንጹሕ ሰውነት አዲስ ዓመትን ለመቀበል ሲሉ ይጠመቃሉ፡፡ የእግዚአብሔርን በዓል ሰውነትን ታጥቦ፣ ንጹሕ ልብስ ለብሶ ማክበር ተገቢ ነው፡፡ ይህም ለበዓሉና ለበዓሉ ባለቤት ያለንን ክብር ያስረዳል፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ “ውረድ ዛሬና ነገ ራሳቸውን ያነጹ፤ ልብሳቸውንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝቡን እዘዛቸው፡፡ በሦስተኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጅተው ይጠብቁ” /ዘፀ. ፲፱፥፲-፲፩/ እንዲል፡፡

በዚህም መሠረት ምእመናን ዓመቱን ሙሉ የተለያየ ኃጢአትን ሲሠራ የቆየ ሰውነትን ለመገሰጽ፣ በደልን እያሰቡ በዕንባና በዋይታ፣ በንስሐ፣ እየጾሙ፣ እየጸለዩና እየሰገዱ አምላካቸውን ይማጸናሉ፡፡ አዲሱን ዓመት በአዲስ ማንነት ለመቀበል እንዲሁም ባለፈው ዓመት ያላሳኩትን፣ ያልሠሯቸውን ሥራዎች ለማሳካት ዕቅድ የሚያወጡበት ወር ነው፣ ጳጉሜን፡፡ ስለዚህ የበደልነውን ክሰን፣ ንስሐ ገብተን አዲሱን ዓመት እንቀበል ዘንድ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡ አሮጌው ዓመት በአዲስ ሲተካ እኛም ደግሞ በኃጢአት ያደፈውን ሰውነታችን አንጽተን መቅረብ ይጠበቅብናል፡፡ይህንን እንድናደርግ እግዚአብሔር አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን፡፡
በወርኃ ጳጉሜን በሃይማኖት ጸንተን፣ በመልካም ሥነ ምግባር ታንጸን ለዘመነ ሉቃስ እንዲያደርሰን የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዋቢ መጻሕፍት

✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር ጳጉሜን ሦስት
✍️ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት
✍️ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
✍️ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት
✍️ Enclopedia of Aethiopica. Vol II.

06/09/2026
በደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ።
15/08/2026

በደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ።

የደብረ ታቦር በዓል ያለውን ማህበራዊ መስተጋብር ጠብቆ ለማቆየት በትውልዱ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

ለረጅም ጊዜያት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው የደብረ ታቦር በዓል አከባበር ከፍተኛ የማህበራዊ ትስስር ያለው መሆኑን ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል።

በአዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከር አኳያ የራሱ ሚና እንዳለው የሚናገሩት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ አዱኛ፣ በከተሞች ባለው የአኗኗር ዘይቤ እና ዘመናዊነት ምክንያት መቀዛቀዝ እና የባህል መበረዝ የሚስተዋልበት መሆኑን ተናግረዋል።

የቡሄ በዓል ማህበረሰቡን እርስ በእርስ ከማቆራኘት አንጻር ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ባህሉን መጠበቅ እንደሚገባ ባለሙያው ገልጸው፤ አሁን ያለው ትውልድ ለቀጣይ ከማሻገር አኳያ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

ቡሄ ባለው ባህላዊ ክንዋኔ መከባበርን፣ የስራ ክፍፍልን፣ በጋራ መስራትን እና ሌሎችንም የሚያስተምር መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሾሎጂ መምህር እና ተመራማሪ ዶ/ር ክቡር እንግዳወርቅ ይናገራሉ።

ምንም እንኳን መነሻው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቢሆንም ሁሉም የሚያከብረው በዓል መሆኑን ተመራማሪው ጠቅሰዋል፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚታየው የባህል መበረዝ ከስልጣኔ መስፋፋት እና ከሌሎችም ምክንያቶች ጋር የተያያዘ ቢሆንም፣ ትውልዱን ከባህሉ ያፈነገጠ እንዳያደርገው መጠንቀቅ እንጂ የግጥሞች እና የክንዋኔዎች ለውጥ ከዘመኑ ጋር አብረው የሚመጡ መሆናቸው ከግንዛቤ ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ቡሄ ባህሉን ለማስቀጠል እና የጋራ የማህበረሰብ ትስስርን ከመጨመር አንጻር ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ ማህበረሰቡ ሊጠብቀው እንደሚገባ ተመላክቷል።

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yonas tesfaye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share