Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa

Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa "ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ለሁሉም"

ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በInnovative Pedagogy ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የተሰጠ የሚገኘው የInnovative P...
19/05/2026

ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በInnovative Pedagogy ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የተሰጠ የሚገኘው የInnovative Pedagogy ስልጠና በፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከፌደራል TVET ኢንስቲትዩት በመጡ የዘርፉ ባለሞያዎች እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማም የተለመደውን የማሰልጠኛ ስነ-ዘዴ ለማሻሻልና ጊዜው የደረሰበትን ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትምህርትና ስልጠናውን ለማዘመን ያለም ስልጠና እንደሆነም ተገልፇል::

ይህ በኮሌጁ ለ5 ቀናት የሚቆየው ስልጠናም ባለፉት 15 ቀናት አሰልጣኝ መምህራኑ በOnline ሲከታተሉት የነበረውን የ Innovative Pedagogy ስልጠና በተግባር የሚሰለጥኑበት እንደሆነው ተመላክቷል::

ስልጠናው በሀገሪቱ በሚገኙና የEASE ፕሮጀክት በሚተገበባቸው 24 ፖሊቴክኒኮች ላይ ለሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን አየተሰጠ እንደሚገኝም ታውቋል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድርን አስመልክቶ በኮሌጁ ምልከታ ተካሄደ::የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በካይዘን ፅንሰ-ሃሳብ መነሻነት እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና ወቅታዊ አፈፃ...
08/05/2026

ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድርን አስመልክቶ በኮሌጁ ምልከታ ተካሄደ::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በካይዘን ፅንሰ-ሃሳብ መነሻነት እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና ወቅታዊ አፈፃፀም ላይ ከፌደራል በመጡ ባለሙያዎች በዛሬው እለት ግምገማ ተካሂዷል::

የሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድር አካል በሆነውና ከፌደራል በመጡ ባለሙያዎች በተካሄደው ምዘና በኮሌጁ የስራ ቦታን ምቹ ከማድረግ ፤ ብክነትን ከመቀነስ፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ፍጥነትን ከማሻሻል አኳያ በተቀመጡ መመዘኛዎች የተከናወኑ ተግባራትንም ገምግሟል::

የምልከታ ቡድኑ በኮሌጁ የካይዘን ትግበራ አጠቃላይ የአፈፃፀም ሪፖርትን የተመለከት ሲሆን ከ8ቱ የውጤት አመላካች አኳያ የተገኙ ውጤቶችን በሪፖርቱ ተመልክተዋል::

በማስቀጠል ቡድኑ በተቋሙ የሚገኙ የስራ ክፍሎችና የስልጠና ወርክሾፖች ላይ የተከናወኑ የካይዘን ትግበራዎችን ከመመልከት በተጨማሪ የካይዘን ትግበራው ውጤታማነትና የተገኘውን ለውጥ የሚያመላክቱ ሰነዶችን በዝርዝር የገመገመ ሲሆን በኮሌጁ በትግበራ ወቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችንም መመልከት ችሏል::

"ዛሬን እናሻሽል፤ ብክነትን እንቀንስ፤ ጥራትና ፍጥነትን እንጨምር፤ ነገን እንገንባ"!!

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

28/04/2026

ለሥራ ፈላጊዎች የወጣ ማስታወቂያ

በተለያዩ የውጭ አገራት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ለምትፈልጉ ዜጎች የኢትዮጵያ መንግስት ከአገራቱ ጋር በፈጠረው ስምምነት እድሉ ተመቻችቷል።

በዚህም እስከ ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እና በሁሉም የአስተዳደሩ ወረዳ የሥራና ክህሎት ማስተባበሪያዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

24/04/2026
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚዘጋጁ  ኤክስፖዎች ለአገር በቀል አምራቾች የእርስበርስ ትስስርን መፍጠር እንደሚያችሉ ተገልፀ::"ድሬ ታምርት፤ ኢትዮጵያ ትበልፅግ” በሚል መሪ ቃል ከሚያዝያ 15 እስከ...
23/04/2026

በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚዘጋጁ ኤክስፖዎች ለአገር በቀል አምራቾች የእርስበርስ ትስስርን መፍጠር እንደሚያችሉ ተገልፀ::

"ድሬ ታምርት፤ ኢትዮጵያ ትበልፅግ” በሚል መሪ ቃል ከሚያዝያ 15 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየው አራተኛው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገር አቀፍ ንቅናቄና የኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽንን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬ እለት በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል።

በዛሬው እለት ጅማሮውን ባድረገው ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በዚህም በኮሌጁ የተሰሩና የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነታቸውን በይበልጥ እንዲያሳድጉ ለማስቻል የተሰሩ ተኪ ምርቶችንም ለጎብኚዎች ይዞ ቀርቧል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!!ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳሣኤው አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመተሳሰብ በዓል ...
11/04/2026

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳሣኤው አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመተሳሰብ በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ ከወዲሁ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

አቶ ታደለ አሰፋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን

09/04/2026
ለኢንተርፕራይዞች ስኬትና ዘላቂነት፦ የጀማሪ ኢንተርፕራይዞችን አቅም በመገንባት ውጤታማና ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና እንዱስት...
08/04/2026

ለኢንተርፕራይዞች ስኬትና ዘላቂነት፦ የጀማሪ ኢንተርፕራይዞችን አቅም በመገንባት ውጤታማና ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና እንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በአስተዳደሩ ከተለያዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::

ለኢንተርፕራዝ አንቀሳቃሾች የአቅም ግንባታ ስልጠናውን የሰጡት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ሀላፊ አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ውጤታማ፣ ተወዳዳሪና ዘላቂነት እንዲኖራቸው ለማስቻል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከትንሽ ተነስተው ትልቅ ቦታ ለመድረስ ያላቸውን ራዕይ አጠናክረው በቁርጠኝነት ሊተጉ እንደሚገባም ተናግረዋል::

በእለቱ ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠናው በዋናነት.....
- የንግድ ስነ-ምግባር..
- የገበያ ጥናት..
- የፋይናንስ አያያዝ..
- የቴክኖሎጂ ሽግግርና ካይዘን..
- የስራ ፈጠራና የንግድ ኢንኩቤሽን እና..
- የደንበኞች አያያዝ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሰፊው ግንዛቤ የተሰጠበት መድረክም ነበር::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ዋሂል ክላስተር በSolar PV Installation & Maintenance ስልጠናዋን ተከታትላ ላጠናቀቀች አካል ጉዳ...
03/04/2026

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ዋሂል ክላስተር በSolar PV Installation & Maintenance ስልጠናዋን ተከታትላ ላጠናቀቀች አካል ጉዳተኛ ወጣት በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) ድጋፍ አደረገ::

ድጋፉ በዋናነት በBMZ ADRA, Germany አማካኝነት የተገኘ ሲሆን ይህም 1.1 KW የሚያመነጭ የSolar PV System ዝርጋታ እና በሶላር የሚሰራ ማብሰያ ምድጃ(Solar Cooker) ያካተተ እንደሆነም ተገልፇል::

በፕሮጀክቱ ድጋፍ የተደረገላት ወጣት ፎዚያ ባጋጠማት የአካል ጉዳት ሳትበገር ከምትኖርበት ከዋሂል ክላስተር ጁጁማ ወረዳ ተነስታ ኮሌጅ ድረስ ለስድስት ወራት 20 ኪሎ ሜትሮችን እየተመላለሰች ስትሰለጥን የቆየች ብርቱ ሴት ስትሆን የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክትም የዚህችን ወጣት ድካም በመረዳት በአካባቢዋ የራሷን ቢዝነስ ሰርታ ገቢ ምታገኝበትን የSolar PV System ዝርጋታ እንዲሁም በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) በድጋፍ መልክ አበርክቷል::

የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በSolar PV Installation Maintenance ወጣቶችን አሰልጥኖ የሙያ ባለቤት ከማድረግም ባሻገር ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊ ድጋፎችን ሁሉ በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ያስታወሱት የADRA Germany ዋና ሀላፊ አቶ ዳዊት መሀሪ ሲሆኑ በድሬዳዋ ገጠር ክላስተር ላይ ለእህታችን ፎዚያ የተደረገው ድጋፍም ፕሮጀክቱ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽና አካታች መሆኑን ማሳያ ከመሆኑም በተጨማሪም የፕሮጀክቱ ከላይ እስከታች የሚገኙ ሀላፊዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ የመስራት ድምር ውጤት እንደሆነም ገልፀዋል::

ወጣት ፎዚያ በበኩሏ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከብዙ ድካም እንግልት እንዳሳረፋት በመግለፅ በተደረገላት ድጋፍም የተለያዩ ገቢዎችን በማመንጨት የራሷንም ሆነ የቤተሰቦቿን ህይወት እንደምታሻሽል የገለፀች ሲሆን በአጠቃላይ ይህ ድጋፍ እውን እንዲሆን ያደረጉ ለADRA ፕሮጀክት ሀላፊዎችንና አስተባባሪዎች በሙሉ ምስጋናዋን አቅርባለች::

በእለቱ በነበረው የድጋፍ ርክክብ ላይ የADRA Germany, የADRA Ethiopia ሀላፊዎች እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና የኮሌጁ አመራሮች በቦታው ተገኝተው የተደረገውን ድጋፍ ውጤታማነት የተመለከቱ ሲሆን ወጣቷንም አበረታተዋል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

Address

ድሬዳዋ ሳቢያን ከሰኢዶ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሚወስደው መንገድ 300 መቶ ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡
Dire Dawa

Telephone

+251920203994

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa:

Share