Gambella Regional SCOUT Council

   #ተቋማዊትብብር    🕊️ የጋምቤላ ስካውት፣ የሰላም ዘብ!ዛሬ፣ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ታላቁን የሰላም ቀን አክብረናል። ነገም የሰላም መልዕክታችን ይቀጥላ...
15/10/2025

#ተቋማዊትብብር

🕊️ የጋምቤላ ስካውት፣ የሰላም ዘብ!
ዛሬ፣ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ታላቁን የሰላም ቀን አክብረናል። ነገም የሰላም መልዕክታችን ይቀጥላል!
ይህ በዲሲፕሊን የታጀበው ትብብር በማርሽ ባንድ ዜማ ቢደመቅ ኖሮ፣ የሰላም መልዕክቱ ይበልጥ ኃይለኛና በዓሉ ክብሩ የጎላ ይሆን ነበር!
✅ የሰላም ቀን የጎደለው የክብር ዜማ የጋምቤላ ስካውት ባንድ ነው!
የኛ ፕሮጀክት ለ32በላይ ወጣቶች ዲሲፕሊን በመስጠት፣ የሰላም እና ሥርዓት አስጠባቂ ትውልድ ያፈራል። ከቢሮዎችና ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ትብብር በክብር ያደምቃል።
ክብርት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አለሚቱ ኡመድ!
ማርሽ ባንድ እንዲቋቋም በመፍቀድ፣ የሚቀጥለው የሰላም ቀን በጋምቤላ ወጣቶች የክብር ማርሽባንድ እንዲደምቅ ታሪክ ይስሩ!
SHARE በማድረግ ድምፃችንን ከፍ እናድርግ!ማርሽባንድ





#ተቋማዊትብብር

ለክብርት ፕሬዚዳንት እናድርስወጣቶች ለአልባሌ ቦታ ሳይሆን ለክብር ሰልፍ!ፕሮጀክታችን  የሚጠይቀው ከፍተኛ ወጪ ለብረትና ለእንጨት ብቻ አይደለም፤ ወጪው ሙሉ በሙሉ በጋምቤላ ወጣት ትውልድ ላይ...
13/10/2025

ለክብርት ፕሬዚዳንት እናድርስ

ወጣቶች ለአልባሌ ቦታ ሳይሆን ለክብር ሰልፍ!
ፕሮጀክታችን የሚጠይቀው ከፍተኛ ወጪ ለብረትና ለእንጨት ብቻ አይደለም፤ ወጪው ሙሉ በሙሉ በጋምቤላ ወጣት ትውልድ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው!
🥁 በማርሽ ባንድ ምን እናገኛለን?
· 32 ወጣቶች: ከሱስ እና ከስራ አጥነት ወደ ስራ እና የጥበብ ሙያ ይቀየራሉ።
· 6 አሰልጣኞች: ለ6 ወራት የሙዚቃ ክህሎትና ከፍተኛ ዲሲፕሊን ይሰጣሉ።
· ዘላቂ የስነ-ስርአት ባህል: ስካውት ባንድ ማለት ተጠያቂነትና የቡድን ስራ ማለት ነው።
በጋምቤላ ወጣት ላይ ያተኮረ ይህን ታላቅ ዕድል መስተዳድሩ እንዲደግፍ በጋራ ድምጽ እናሰማ!
👉 አሁኑኑ ያጋሩት! ለወጣቶቻችን መብራት እንሁን!

ስካውት ዘወትር ዝግጁ!!
ጋምቤላ ስካውት
ጋምቤላ ስካውት
ጋምቤላ ስካውት

#ዲሲፕሊንለጋምቤላወጣት #ከስራአጥነትወደመድረክ #4ሚሊዮንተስፋ
Alemitu Omod Ojulu

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ትርጉም …18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት...
12/10/2025

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ትርጉም …

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡

ቀኑ “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚከበረው፡፡

በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት እና በሰንደቅ ዓላው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ምንድን ነው?

1. አረንጓዴው ቀለም፡- የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው፡፡

2. ቢጫው ቀለም፡- የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው፡፡

3. ቀዩ ቀለም ፡- ለነፃነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡

እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ የሚገኘው ዓርማ ትርጉም ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. ክብ የሆነው፡- ሰማያዊ መደብ ሰላምን ያመለክታል፡፡

2. ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች፡- የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የሐይማኖቶችን እኩልነት ያመለክታሉ፡፡

3. ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ፡- የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈቃቀድ የመሠረቱትን አንድነት ያመላክታል፡፡

4. ቢጫ ጨረሩ ደግሞ ፡- በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሔር፣ ብሔረሰቦች የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል፡፡
👉ኤፍ ኤም ሲ

የጋምቤላ ክልል ስካዉት ካዉንስል

12/10/2025
🚨 የጋምቤላ ክልልን ክብር በማርሽባንድ (በሙዚቃ ) ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው!ታውቃላችሁ? አሁን ላይ ጋምቤላ ክልል በእንግዶች አቀባበል እና በበዓላት ላይ የራሱን ክብር የሚያንፀባርቅ ቋሚ ...
12/10/2025

🚨 የጋምቤላ ክልልን ክብር በማርሽባንድ (በሙዚቃ ) ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው!

ታውቃላችሁ? አሁን ላይ ጋምቤላ ክልል በእንግዶች አቀባበል እና በበዓላት ላይ የራሱን ክብር የሚያንፀባርቅ ቋሚ ማርሽ ባንድ የለውም! ይህ ክፍተት የክልሉን ገፅታ ከሚፈለገው ደረጃ በታች አድርጎታል።

✅ ይህ ክፍተት መሞላት አለበት!

የጋምቤላ ክልል ስካውት ማህበር፣ ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ይዞ ቀርቧል! 32 በላይ የክልላችን ወጣቶችን ያቀፈ ሙያዊ ማርሽ ባንድ ለማቋቋም ዝግጅት አጠናቅቀናል።

በዚህ ሳምንት ታላቁን ፕሮፖዛላችንን ለመስተዳድር ምክር ቤት ለማቅረብ እየተዘጋጀን ነው። ክልላችንን ለማስከበር ለምናደርገው ጥረት የእርሶ SHARE እና LIKE ወሳኝ ነው።

የክብር ጥሪ! መልዕክቱን ለክብርት ፕሬዚዳንቷ እና ለምክር ቤቱ እናድርስ!
ስካውት ዘወትር ዝግጁ !!

#ጋምቤላማርሽባንድ #ክብራችንንእንጠብቅ #ለአራትቀንየሚቆይጥሪ

በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ የስካውት አባላት እየተሳተፉ ይገኛል ፡፡ሐምሌ 20/2017 አዲስ አበባ"ወጣቶች እንደ ለውጥ ፈጣሪ፥ ጥበብና ፈጠራ ለለውጥና ዘላቂ የም...
27/07/2025

በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ የስካውት አባላት እየተሳተፉ ይገኛል ፡፡
ሐምሌ 20/2017 አዲስ አበባ

"ወጣቶች እንደ ለውጥ ፈጣሪ፥ ጥበብና ፈጠራ ለለውጥና ዘላቂ የምግብ ስርዓት ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ የጉባኤው አካል የሆነ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በውይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠችና ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠረች ትገኛለች ።

በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርና የምግብ ዋስትናን በሚያረጋግጡ የምጣኔ ሃብት ዘርፎች ወጣቶችን በንቃት በማሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው።

በግብርናው ዘርፍ ለሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ለግብርና ቴክኖሎጂና ወጣቶች በምግብ ስርዓት ላይ ያላቸውን ሚና ማሳደግ በጉባኤው ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።

የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ በበኩላቸው፥ በዓለም የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች የምግብ ስርዓት ላይ ጫና እያሳደሩ መሆኑን አንስተዋል።
ለችግሮች መፍትሄ በመስጠት የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችና የአፍሪካ አጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ፥ በጣልያን እና በተመድ ትብብር የተዘጋጀው ሁለተኛው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የኢትዮጵያ ስካውት ማሕበር አባላት እየተሳተፉ ይገኛል ፡፡

ሐምሌ 20/2017 አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ስካውት ማሕበር

🪢⚜️ 🅢🅒🅞🅤🅣🅢 𝔢𝔳𝔢𝔯𝔶𝔴𝔥𝔢𝔯𝔢
10/07/2025

🪢⚜️ 🅢🅒🅞🅤🅣🅢 𝔢𝔳𝔢𝔯𝔶𝔴𝔥𝔢𝔯𝔢

የኢትዮጵያ ስካውት ማሕበር በመላው አገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ (Food for Life) ምግብ ለሕይወት ፕሮጀክት ስልጠና ለስካውት መሪዎች እና አስተባባሪዎች መስጠት ተጀመረ ፡፡ግንቦት 21/2...
29/05/2025

የኢትዮጵያ ስካውት ማሕበር በመላው አገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ (Food for Life) ምግብ ለሕይወት ፕሮጀክት ስልጠና ለስካውት መሪዎች እና አስተባባሪዎች መስጠት ተጀመረ ፡፡

ግንቦት 21/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ

ምግብ ለሕይወት (Food for Life) ፕሮጀክት በአለም ስካውት ፋውዴሽን ድጋፍ በኢትዮጵያ ፣ በማላዊ እና በሩዋንዳ ተግባራዊ የሚደረግ ፕሮጀክት ሲሆን ዋንኛ ዓለማው ታዳጊዎች መሰረታዊ የግብርና እውቀት ኖራቸው በትምህርት ቤታቸው እንዲሁም በአካባቢያቸው የጓሮ አታክልቶችን በቀላሉ በመትከል እና በማብቀል መጠቀም የሚችሉበትን ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል እንዲሁም ዘላቂነት ያለው የምግብ ፍላጎትን በሟሟላት ለአካባቢ ጥበቃ የበኩላቸውን አስተዋፆኦ እንዲወጡ የሚያስችል ነው ፡፡

በዛሬው እለተም በአዲስ አበባ እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ከቤንሻንጉል ክልል በስተቀር ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የስካውት መሪዎች ፣ መምህራን እና አስተባባሪዎች ስልጠናውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን ኬኒያ ከሚገኘው የአፍሪካ ስካውት ቢሮ በመጡ አሰልጣኝ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛል ፡፡

ግንቦት 21/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ስካውት ማሕበር

 #የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግንቦት 15/2017 ዓ.ምየጋምቤላ ክልል ስካውት ካውንስል አባላት  በጋምቤላ ከተማ ጎዳና ላይ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን ፀጉር የመቁረጥ እንዲሁም ለሴቶች እና ለህፃና...
26/05/2025

#የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
ግንቦት 15/2017 ዓ.ም
የጋምቤላ ክልል ስካውት ካውንስል አባላት በጋምቤላ ከተማ ጎዳና ላይ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን ፀጉር የመቁረጥ እንዲሁም ለሴቶች እና ለህፃናት የአልባሳት ድጋፍ አከናወኑ ።
የእለቱ በጎ ፈቃድ አገልግሎቶ የተለያዩ ደረጃ ላይ የሚገኙ ስካውቶች ተሳታፊ ሆነዋል ።

ግንቦት 15/2017 ዓ.ም
የጋምቤላ ክልል ስካውት ካውንስል

Address

Gambela
@GETMERCY

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gambella Regional SCOUT Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Gambella Regional SCOUT Council:

Shortcuts

Share