19/08/2026
# #አቶ ክንዱ ዘውዱ
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ፣ ከጠቅላላ ሠራተኞቹ ጋር በ2018 ዓ.ም በተገኘው የዕቅድ አፈጻጸም ውጤት እና ለቀጣይ ዓመት ባቀዳቸው የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ገንቢ ውይይት አድርጓል።
በዚህ የግምገማ ሂደት፣ መምሪያው ባለፈው ዓመት ያገኘው ውጤት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገልጿል ። አቶ ክንዱ እንዳስታወሱት፣ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ የተሰጠው እውቅና ለሠራተኞቹ ማበረታቻ ሲሆን፣ ይሁን እንጂ የተገኘውን ስኬት ለማስቀጠልና ደረጃውን ለማሻሻል ቀጣይ ተግባራትን በአግባቡ መፈጸም እዳ መሆኑን አሳስበዋል።
ከሁሉ በላይ ግን፣ የትምህርት አገልግሎታችን ዋና ተጠቃሚ ማኅበረሰባችን ተጨባጭ ጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ የሁላችንም ዋነኛ ሃላፊነት መሆኑን አጥብቀው ገልጸዋል።
በመቀጠልም፣ የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ነጋ ብርሀኑ ለሠራተኞቹ እንኳን ለተገኘው ስኬት ደስ አላችሁ በማለት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በተጨማሪም፣ የ2019 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባን በአግባቡ በማካሄድ እና የትምህርት ሥራችንን ውጤታማነት በማረጋገጥ ያለፈውን ስኬት መድገም እንደሚገባ አሳስበዋል።