ጎንደር ዮኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት Gondar University Students Union

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • ጎንደር ዮኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት Gondar University Students Union

ጎንደር ዮኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት Gondar University Students Union The University of Gondar is one of the first generation universities in Ethiopia. In the 2016 and 20

🎓የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ዛሬ እያስመረቀ ነው።ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ነው።ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ በድኅረ ምረቃ ፣...
25/06/2026

🎓የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ዛሬ እያስመረቀ ነው።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ በድኅረ ምረቃ ፣ በሰብስፔሻሊቲ እና በሦሥተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 4ሺህ 83 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

24/06/2026
24/06/2026
ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ለምትመረቁ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!በነገው ዕለት የሚካሄደው የዓመታዊ ምረቃ በዓል መድረክ ዝግጅት በከፊል ይህንን ይመስላል።፥፥፥፥፥፥...
24/06/2026

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ለምትመረቁ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

በነገው ዕለት የሚካሄደው የዓመታዊ ምረቃ በዓል መድረክ ዝግጅት በከፊል ይህንን ይመስላል።
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ሰኔ 16 ቀን 2018ዓ.ም.

Congratulations to the University of Gondar students graduating on June 25, 2026!

This is partly what the stage preparation looks like for tomorrow's annual graduation ceremony.
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
June 23, 2026

ይነበብ ይነበብ ይነበብ!! 🎓 ለ2018 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ! 🎓ውድ የ2018 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎች፣በመጀመሪያ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን በቅርቡ የት...
22/06/2026

ይነበብ ይነበብ ይነበብ!! 🎓 ለ2018 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በሙሉ የቀረበ ጥሪ! 🎓

ውድ የ2018 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎች፣

በመጀመሪያ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን በቅርቡ የትምህርት ጉዞአችሁን በስኬት አጠናቃችሁ ወደ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ለመሸጋገር በመዘጋጀት ላይ ትገኛላችሁ። ይህን አስመልክቶ የጎንደር ዪኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ግኑኝነት ቢሮ ከስራ ዕድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል ጋር መተባበር "ከካምፖስ ወደ ስራ ዓለም" በሚል መሪ ቃል የሙያ ልምድ ማካፈያ፣ የሥራ ዕድል አውደ ርዕይ፣ የሥራ ፈጠራ እና የኔትወርኪንግ መድረክ አዘጋጅቷል።
ይህ መድረክ ከግቢ ሕይወት ወደ ሥራ ዓለም የምታደርጉትን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የሚያግዝ በመሆኑ እንዲሳተፉ ስንል በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።

📅 ቀን: ሰኔ 16, 2018 ዓ.ም.
🕒 ሰዓት: ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30
📍 ቦታ: ቴዎድሮስ ግቢ፣ ፕሬዚዳንት ህንፃ
በዚህ መድረክ ላይ፦
🔹በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ የሆኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀድሞ ተማሪዎችን የሚያገኙበት እና ከልምዳቸው የሚማሩበት፤
ልዩ መድረክ ስለሆነ ሁላችሁም በሰዓቱ ተገኝታችሁ የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንድትሆኑ እናሳውቃለን።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
"ከካምፓስ ወደ ሥራ ዓለም የሚደረገውን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ በአንድነት እንጓዝ!"

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ከነርቸር ፕሮጀክት (NURTURE Project) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የተመራቂ ተማሪዎች የፋይናል ፕሮጀክት የውድድር መድረክ (Graduate Fin...
22/06/2026

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ከነርቸር ፕሮጀክት (NURTURE Project) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የተመራቂ ተማሪዎች የፋይናል ፕሮጀክት የውድድር መድረክ (Graduate Final Project - Competition Challenge) ላይ እንዲገኙ ጋብዞዎታል!

የዕለቱ ዋና ዋና ሁነቶች፦
የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን፦ የወደፊት ዲጂታል መፍትሄዎችን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይመለከታሉ፤ ለተቋምዎ የሚሆኑ አዋጭ የዲጂታል መፍትሄዎችንም ይመርጣሉ።

የሽልማት ሥነ-ስርዓት፦ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለሚወጡ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት (15,000 ETB፣ 10,000 ETB እና 7,000 ETB) እንዲሁም የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከታል።

የትስስር መድረክ (Networking)፦ ከተመራቂ ወጣቶችና ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር ትስስር የሚፈጠርበት ምቹ አጋጣሚ እንደሚሆንም ይታመናል።

ሁነቱ የሚካሄድበት ቀን እና ቦታ፦
ቦታ፦ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ፣ PG አዳራሽ (College of Informatics PG Hall)
ቀን፦ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. (June 24, 2026)

ሰዓት፦ ጠዋት 2:30

የነገዎቹን የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል በመገኘት እንዲያበረታቱ እና ለተቋምዎ የሚሆኑ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያበረታቱ በአክብሮት ተጋብዘዋል!

Graduate Final Project – Competition Challenge

The College of Informatics, in collaboration with the NURTURE Project, cordially invites you to the Graduate Final Project Competition Challenge. Join us to support our graduating students and discover cutting-edge digital solutions tailored for your institution!

Key Highlights of the Event

👉Innovation Exhibition: Explore future-ready digital solutions and technological advancements. A prime opportunity to scout viable digital products for your organization.

👉 Award Ceremony: Celebrating excellence with attractive cash prizes for top performers—1st Place (15,000 ETB), 2nd Place (10,000 ETB), and 3rd Place (7,000 ETB)—along with Certificates of Achievement.

🤝 Industry-Academia Linkage: A dynamic networking platform to connect talent with potential industries and sector experts.

Event Details@

👉 Venue: College of Informatics, PG Hall

👉 Date: June 24, 2026

👉 Time: 2:30 Local Time (8:30 AM)

Be there to empower tomorrow's tech leaders in person and explore innovative breakthroughs ready for institutional adoption. Your presence is highly valued!

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የምናካሂደውን የተማሪዎቻችንን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።To watch the live broadcast of o...
22/06/2026

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የምናካሂደውን የተማሪዎቻችንን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

To watch the live broadcast of our students’ graduation ceremony, which will be held on June 25, 2026, use the link below.

https://youtube.com/live/Y6P--G3uI5w?feature=share

11/06/2026

በአገራችን ወግ " *ቡና እየጠጣን እንጫወት* " ከተባለ፣ ከልብ ሊያወጉት ያሰቡት ትልቅ ቁምነገር አለ ማለት ነው።

የኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ፤ በህይወት ጉዟቸው ስኬትን የተጎናጸፉ፣ ለማህበረሰባቸው የሚበጅ በጎ ተግባርን በትጋትና በቅንነት ያበረከቱ ታላላቅ ሰዎችን ተሞክሮ የምንቀስምበት *'የቡና ወግ' /Coffee Talk* / የተሰኘ ደማቅ ዓመታዊ መርሃ-ግብር አለው።

የዘንድሮ ልዩ እንግዳችን *የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን* ናቸው። ከስኬታቸው በስተጀርባ የነበሩ እልህ አስጨራሽና አበረታች ጉዞዎችን እያነሳን፤ ስለ ህይወት ፍልስፍናቸው፣ ስለ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሪነት ሚና፣ ስለ ትናንት ትውስታቸው፣ ስለ ዛሬው እውነታና ስለ ነገው ራዕያቸው እንጠይቃቸዋለን፡፡

*ይህ ተራ የቡና ግብዣ አይደለም!*
ቡናችን በእጅ የተለቀመ፣ በሙያ የተቆላና በፍቅር የሚፈላ እውነተኛ አገራዊ ቡና ነው። በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው የልብዎን ጥያቄ እንዲያቀርቡና እንዲወያዩ እንደ አንድ *የልብ ወዳጅ* ተጋብዘዋል።

*ማሳሰቢያ፦*
1. *ቅድመ-ምዝገባ* ፦ ለዝግጅቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መመዝገብ ግዴታ ነው። ብዚህ ሊንክ ይመዝገቡ
https://gqr.sh/bVBB
*2. ሰዓት ማክበር፦* "ቡና ትኩሱን ነው" እንዲሉ፣ ሰዓት ማክበር የዝግጅታችን ዋነኛ ውበት ነው።

*የፕሮግራሙ ዝርዝር፦*
*• ቀን፦* ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (June 15, 2026)
* *ሰዓት፦* ጠዋት 2፡30 (በአገራችን የሰዓተ አቆጣጠር)
*• ቦታ፦* የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት፣ 6ኛ ፎቅ
እንዳይቀሩ! ትኩስ ቡና እና ጣፋጭ ወግ ይጠብቅዎታል።
*አዘጋጅ፦* ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ (College of Informatics)

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪ (አሉምናይ) ኖት?እንግዲያውስ ይህ ዝግጅት ለእርስዎ ነው!የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ግንኙነት ቢሮ ከ ስራ እድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል ጋር በመተ...
10/06/2026

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪ (አሉምናይ) ኖት?
እንግዲያውስ ይህ ዝግጅት ለእርስዎ ነው!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ግንኙነት ቢሮ ከ ስራ እድልና ፈጠራ ልማት ማዕከል ጋር በመተባበር በሚከተለው ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ በደስታ ይጋብዝዎታል፦
የቀድሞ ተማሪዎች የሙያ ውይይት፣ የስራ ፈጠራ፣ የቅጥር አውደ-ርዕይ (Job Fair) እና የትስስር መድረክ

መሪ ቃል፦ ከካምፓስ ወደ ስራ ዓለም
ቀን፥ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦታ፥ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ ግቢ ኘሬዚዳንት ህንፃ
⏰ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ

ከቀድሞ ተማሪዎች ጋር ይገናኙ፣ የስራ እድሎችን ያስሱ፣ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን ያቅርቡ እና ሙያዊ ትስስርዎን ያስፉ።

✨ ለመማር፣ ለመገናኘትና ለማደግ የሚያስችለው ይህ አስደሳች እድል እንዳያመልጥዎት!

አሁኑኑ ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡና ቦታዎን ያስጠብቁ።
https://forms.gle/cgk7L7acdi87qTxA6

Are you an alumnus/alumna of the University of Gondar?
Then this event is for you!

The University of Gondar Alumni Relations Office in Collaboration with Center for Employabilty and Entrepreneurship Development (CEED) invites you to the:
Alumni Career Talk, Entrepreneurship, Job Fair & Networking Event

Theme: From Campus to Career
Date: June 23, 2026
Venue: University of Gondar, Tewodros Campus, President Building
⏰ From 8:30 AM

Connect with successful alumni, explore career opportunities, showcase innovative ideas, and expand your professional network.

✨ Don't miss this exciting opportunity to learn, connect, and grow!

👉 Register now using the link below and secure your place.
https://forms.gle/cgk7L7acdi87qTxA6

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጎንደር ዮኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት Gondar University Students Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share