The fastest University info

The fastest University info Please follow us to get accessible and fastest information. University info.com

02/04/2025

የመጋቢታዊያን የንስሩ ጋሞ የከፍታ ዘመኖች ከሚያሰኙ ኩነቶች ውስጥ የሚከተሉት ናቸው:-
1 -የጫኖ-ዋጫ ግራጫ 120 ኪ.ሜ 24 ቢሊዮን ብር!
2 -የጋሞ አርባምንጭ እስታዲዮም በ6 ቢሊዮን ብር!
3 -230k ቮልት የኤሌትሪክ ሰብ እስቴሽን በ21 ቢሊዮን ብር!
4 -ገበታ ለአገር አርባምንጭ ከስማርትሲቲ ጋር 10 ቢሊዮንብር
5-ኮሪደር አርባምንጭ በ8 ቢሊዮን ብር!
6-የጋሞ ቲቪ በ1 ቢሊዮን ብር!
7-ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ሪፈራል ሆስፒታል 20 ቢሊዮንብር!
8-የአፕልና የሙዝ ብራንድ ፍራፍሬ ገቢ 20 ቢሊየሸን ብር!
9-የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ በ10 ቢሊዮን ብር!
10-በይራ አዳሪ ት/ቤ በአነድ ቢሊዮን ብር!
11-የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ 880h በ6 ቢሊዮን ብር!
12-ተወዳዳሪ የሌለው የአለም የሰላም ተምሳሌት ምድር ጋሞ በመሆኑ በቱሪዝም ከኢትዮጵያ አንደኛ ስለወጣ... !!!
13-የጋሞ ልማት ማህበር በውስጡ የያዛቸው ሰላም ማይክሮ ፋይናንስ፣ኮንስትራክሽን፣970 ሄክታርእርሻ፣ጋራዥ፣ፋብሪካ፣የተለያዩ ንግዶች!
14-በ12 ክፍል በአገር አቀፍ ፈተና 638 ሺ ተማሪዎች ውስጥ 600/566 በማምጣት በIQ አንደኛ የሆነው የጋሞ ዳግማዊ ቅጣው እጅጉ ተማሪ ደፋሩ በመሆኑ...!!!
15-ከ50 ሺ በላይ የጋሞ የኳስ ደጋፊዎች የአበበ ቢቂላ እስታዲየምን ሞልተን አሸንፈን ዋንጫ በማንሳት በአንደኝነት ፕሪመርል ሊጉን የተቀላቀለበት የከፍታ ዘመናችን በመሆኑ...!
ወዘተ...!!!
16-የጋሞ ተወላጁ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን
ፕሬስዳንት በመሆኑ...!!!
17-ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ ከሰባት ጊዜ በላይ በፍቅርና በናፍቆት የጎበኛት ምድር በኢትዮጵያ ውስጥ ቢኖር ጋሞ አርባምንጭ ብቻ በመሆኑ...!!!
18-ስለ ጋሞ አርባምንጭ በከፍተኛ ሁኔታ ብዙ ዘፈኖች አሞጋግሶው በመዝፈናቸው ...!!!
19-ጋሞ አርባምንጭ በአገር ውስጥና በውጪ ጎብኚዎች በከፍተኛ ቁጥር በመጎብኘት በኢትዮጵያ አንደኛ በመውጣቱ...!!!
ወዘተ...!!!
20-በ1.6 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የደቡብ ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የቅኔና የድቁና መንፈሳዊ ተቋም ጋሞ ዚጊቲ አቡዬ ገዳም በመሆኑ....!!!
21-በአሁኑ አመታት ከሰባት በላይ ሆስፒቲሎች በሰባት ወረዳዎች ላይ በ4 ቢሊዮን ብር ተገንብተው ወደ መጠናቀቅ ደረጃ ላይ ስለሚገኙ...!!!
22-በጋሞ ብሔር ተወላጁ በኢትዮጵያ በሀብቱ በሶስተኛ ደረጃ የሚገኘው ጃል ፍሬው ቱፋ የሚያስገነባው የአልማዝ ማዕድናት አለም አቀፍ ደረጃ ሰርተፊኬት ሰጪ ተቆም 16 ቢሊዮን ብር የሚገነባው በጋሞ...!!!
23-በጋሞ አርባምንጭ በ3 ቢሊዮን ብር የተሠራው የቀን ከ70ሺ ሊትር በላይ ወተት እያቀናበረው ያለው ፋብሪካ ...!!!
24-የ4 ቢሊዮን ብር ተገንብቶ እያለቀ ያለው የታላቁ አትሌት የቀነኔሳ ሪዞልትና ሎጆ ስለሚገኝ...!!!
25-በ3 ቢሊዮን ብር ተገንብቶ እያለቀ ያለው ኩሪፊቱ አርባምንጭ ሪዞልትና ሎጅ ስለሚገኝ...!!!
26-በ2.7 ቢሊዮን ብር ተገንብቶ እያለቀ ያለው ሌዊ ሪዞልትና ሎጅ ስለሚገኝ...!!!
27-ከአዲስ አበባ-ሶዶ-አርባምንጭ 490ኪ.ሜ ርቀት 12 ሰዓታት የሚፈጀው አሰልቺ የትራንስፖርት መንገድ ወደ ኢንተርናሽናል የፍጥነት መንገድ አዲስ አበባ-አዋሳ-ዲላ-አርባምነሰጭ 340 ኪ.ሜ ርቀት በ4 ሰዓት

30/03/2025

የማሃተማ ጋንዲ ምርጥ ንግግሮች!

"በአለም ላይ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሁን"

"ደካሞች ይቅር ማለት አይችሉም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ነው"

"ነገ እንደምትሞት ኑር ለዘላለም እንደምትኖር ተማር"

"ደስታ ማለት የምታስበው፣ የምትናገረው እና የምትሰራው ነገር ሲስማማ ነው"

"ሰው የሃሳቡ ውጤት ነው ያሰበውን ይሆናል"

"ጥንካሬ ከሥጋዊ አቅም አይመጣም ከማይበገር ፈቃድ ነው"

"የወደፊቱ ጊዜ ዛሬ በምትሠራው ላይ የተመሰረተ ነው"

"መጀመሪያ ችላ ይሉሃል፣ ከዚያም ይስቁብሃል፣ ከዚያም ይዋጉሃል፣ ከዚያም ታሸንፋለህ"

"ጤና ነው እውነተኛ ሀብት የወርቅና የብር ቁራጭ አይደለም"

"የአንድ ሀገር ታላቅነት እና የሞራል እድገቷ የሚለካው በእንስሳቱ አያያዝ ነው"

"በድርጊትህ ምን ውጤት እንደሚመጣ ማወቅ አትችልም ነገር ግን ምንም ካላደረክ ምንም ውጤት አይኖርም"

"ድርጊት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ይገልጻል"

"አመጽ የኃያላን መሳሪያ ነው"

"በብዝሃነት ወደ አንድነት የመድረስ ችሎታችን የሥልጣኔያችን ውበትና ፈተና ይሆናል"

" ከምንናገረው ይልቅ የሆንነው ነገር ይበልጣል"

"እርካታ በጥረት ላይ እንጂ በመድረስ ላይ አይደለም ሙሉ ጥረት ሙሉ ድል ነው"

"አንድን ነገር ስታደርግ በፍቅር አድርገው ወይም በጭራሽ አታድርገው"

"ምድር የሰውን ፍላጎት ለማርካት በበቂ ሁኔታ ትበቃለች ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ስግብግብነት አለበት"

"ሌሎች በቀላሉ እንዲኖሩ በቀላሉ ኑሩ"

"መሪነት በአንድ ወቅት ጡንቻ ማለት ነው ብዬ አስብ ነበር ዛሬ ግን ከሰዎች ጋር መግባባት ማለት ነው"

የአሜሪካ 2024 ምርጫ ለአለም በጣም አስጊ ሆኗል !!!የሁለቱንም ተወዳዳሪዎች ሀሳብ በአጭሩ ልንገራችሁ እና ለሀገራችን ማን ይጠቅማል የሚለውን ትመርጣላችሁ።1ኛ:- ካሚላ ሀሪስ 👇- ከ 115...
28/07/2024

የአሜሪካ 2024 ምርጫ ለአለም በጣም አስጊ ሆኗል !!!

የሁለቱንም ተወዳዳሪዎች ሀሳብ በአጭሩ ልንገራችሁ እና ለሀገራችን ማን ይጠቅማል የሚለውን ትመርጣላችሁ።

1ኛ:- ካሚላ ሀሪስ 👇

- ከ 115 በላይ ፆታ አለ ብላ ታምናለች ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ትደግፋለች

- ለጥቁሮች እና ለ ሴቶች ጥሩ የሆነ እይታ አላት

- በአለም ላይ ጣልቃ በመግባት የአሜሪካን ጥቅም ለማስጠበቅ ትሰራለች

- ህገወጥ ስደተኞች ላይ የላላ ቁጥጥር ታደርጋለች

- ወላጆች ከ 18 አመት በታች ባሉ ልጆቻቸው ላይ ስልጣን እንዳይኖራቸው የማድረግ ህፃናቶች በራሳቸው ፍቃድ ፆታቸውን በቀዶ ጥገና እንዲያስቀይሩ የሚፈቅደውን ህግ በሁሉም ስቴቶች ለማፅደቅ እቅድ አላት። ባይደን በካሊፎርኒያ ይሄን ህግ አፅድቋል

2ኛ:- ዶናልድ ትራምፕ 👇

- እኔ ከተመረጥኩ በመንግስት ደረጃ ሁለት ብቻ ፆታ ነው የሚኖረው እሱም ሴት እና ወንድ ብሏል

- ህገወጥ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የምችለውን በሙሉ አደርጋለሁ የገቡትንም ወደ ሀገረቸው እጠርዛለሁ ብሏል

- አሜሪካ ውስጥ ያሉትንም ሆኖ ከአሜሪካ ውጪ ያሉ ሙስሊሞችን በአይነ ቁራኛ እከታተላቸዋለሁ አሜሪካን ከጥቃት ለመጠበቅ ብሏል።

- ለአሜሪካ ጥቅም ብለን የሰው ሀገር ውስጥ እጃችንን አናስገባም ብሏል

=> የሁለቱ አላማ በአጭሩ ይህ ነው። ሁለቱም ጥሩ የሚባል ነገር አላቸው እንዲሁም በጣም መጥፎ ፖሊሲም አላቸው ሀገራችንን ጭምር ስጋት ውስጥ የሚከት ። ግን ለአለም ህዝብ ማን ቢመረጥ ትንሽም ቢሆን ይሻላል ትላላችሁ ? ከላይ የጠቀስኩትን ነጥቦች መርምራችሁ ምጫውን ምረጡ።

ሀ▶ ካሚላ ሀሪሳ
ለ▶ ዶ/ትራምፕ

15/07/2024

🙏90 ፐርሰንት የሚሆኑ የሀገራችን ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸውን ጥናቶች አመላከቱ‼️

👉 'በሀገራችን ኢትዮጵያ🇪🇹 የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል?' በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ገልፀዋል።

ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም ላይ በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ የተናገሩ ሲሆን፤ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልፀው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መልክ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉ ሲሆን፤ በዚህ ሂደት ውስጥም ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን ፣ ርዕሰ መምህራን እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ብለዋል።

ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም የተናገሩት ተመራማሪው፤ የተጀመረው የበይነ በረብ/Online ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና እንደሚኖረው መግለፃቸውን ከFBC የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

15/07/2024

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሰጠው መረጃ

| በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የቡ ከተማ በቅርቡ ከሰማይ እንደመጣ የተነገረለትን ድንጋይ በተመለከተ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሰጠው መረጃ‼️

አስትሮይድ (Asteroid) በህዋ ውስጥ የሚገኙ ድንጋያማ አካላት ናቸው፡፡ በዋነኛነት የስርዓተ ጸሐይ አካል በመሆን በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው ስፍራ የመቀነት ቅርጽ (Asteroid Belt) ፈጥረው ጸሐይን ይዞራሉ፡፡

እነዚህ የሰማይ አካላት ግዙፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹም በመቶ ኪሎሜትሮች የሚቆጠር ዲያሜትር ያላቸው ናቸው፡፡

በአንፃሩ ሜትሮይትስ (Meteorites) ወደ ምድር ከባቢ አየር የገቡ የአስትሮይዶች ወይም ኮሜት ቁርጥራጮች ናቸው። በሌሊት ሰማይ ላይ የምናያቸው የብርሀን ጅራቶች ሜትሮይድ (Meteoroid)፣ ትንሽ የጠፈር አለት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገባና ሲቃጠል የሚፈጠር ነው።

የሜትዮር ሻወር (Meteor Shower) አስደናቂ የብርሃን ትዕይንት በሰማይ ላይ የሚፈጥሩ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ሜትሮይዶች ጥቃቅን እና መሬት ላይ ከመድረሳቸው በፊት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የሚጠፉ ናቸው።

በመጠን የገዘፉ እና ጠንካራ የሆኑት አለቶች ከእሳታማው መተላለፊያ እና የመሬት ከባቢ አየር ተርፈው መሬት ላይ ይደርሳሉ።

ከላይ በምስል የሚታየው አለት በጅማ ዞን በየቡ ከተማ የተገኘ ሲሆን በተለያዩ ሚዲያዎች መነጋገርያ ሆኖ መቆየቱን ተመልክተናል፡፡ የተገኘው ድንጋይ ሜትሮይት ወይም ሌላ ዓይነት ከህዋ የተገኘ አለት መሆን አለመሆኑን ለመወሰን የላብራቶሪ ምርመራ አስፈላጊ በመሆኑ፤ አሁን ባለበት ደረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንደማይቻል ልናሳውቅ እንወዳለን።

Meteorites ከተለመዱት የምድር አለቶች የሚጋሩት ነገር ቢኖርም በራሳቸው ደግሞ የተለየ ስሪት እና አወቃቀር ያላቸው በመሆኑ በአይን በማየት ብቻ ለመለየት አዳጋች ይሆናል፡፡ የመስኩ ተመራማሪዎች የሜትሮይትን ስብጥር ለመተንተን የረቀቁ ቴክኒኮችን እና የሳይንስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ።

ይህም የማዕድን ይዘቱን ለመመርመር ከምድር ውጭ ያሉ ንጥረ ነገሮች መኖራቸውን መለየት እና የተረጋጋ የአይሶቶፖች ምጥጥንን (isotope ratio) መለካትን ጭምር ያካትታል። እነዚህ ትንታኔዎች የሜትሮይትን አመጣጥ እና ስለ መነሻ ምንጫቸው አስመልክቶ ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳሉ።

ሜትሮይት በምድር ላይ የሚያስከትሉት ተጽእኖ እና ጉዳት በአንፃራዊነት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ በየዓመቱ ወደ ምድር ገጽ የሚወርዱትም በቁጥር ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኛው አካላቸው በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ሲያልፍ ተቃጥሎ ስለሚያልቅ፤ የሚያደርሱት ጉዳት ያነሰ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉልህ የሆነ ውድመት ሊያስከትሉ የሚችሉት በሚሊዮን አንዳንዴም በሺህ ዓመታት የሚከሰቱት ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ አኳያ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ቴሌስኮፖችን በመጠቀም ካለማቋረጥ እንቅስቃሴያቸውን በንቃት በመከታተል ከፍተኛ ጉዳት ለያመጡ የሚችሉትን አስቀድሞ በመለየት የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ።

ለምሳሌ ያክል በሀገራችን አቆጣጠር ከአምስት ዓመት በኋላ ማለትም በሚያዝያ ወር 2021ዓ.ም. አፓፊስ (Apophis) የተሰኘ 340 ሜትር ስፋት ያለው አስትሮይድ Geosynchronous ሳተላይቶች ካሉበት 35, 786 ኪ.ሜ. ከፍታ ዝቅ ብሎ ከመሬት በ31, 860 ኪ.ሜ. ከፍታ ላይ እንደሚደርስ ትንበያዎች ያሳያሉ ፡፡

የሰው ልጅ የተለያዩ መሳሪያዎችን እና ቴክኒኮችን በመጠቀም ህዋን መመርመር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህንን ያክል ግዙፍ አለ

05/11/2022

We are here to help you

17/05/2022
23/02/2022

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
----------------

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ ም 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር አገር አቀፍ የትምርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሁለት ዙር የተሰጠው 2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለአገር አቀፍ ፈተና ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች መካከል 599,003 (96.9%) ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት በመታየቱ ምክንያት የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑን ጠቁመዋል።

አቶ ተፈራ ፈይሳ አክለውም ሁሉም ተማሪዎች የግልም ሆነ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ተወስኖ ወደፊት ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- -
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች፡- student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት ይችላሉ።

10/10/2021

አዲሱ የትምህርት ስርዓት '‼️

በዘንድሮ 2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን በሙከራ ደረጃ እንዲሁም በ2015 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ የሚገባው አዲሱ የኢትዮጵያ 🇪🇹 የትምህርት ስርዓት ምን ምን ጉዳዮችን አካቷል ⁉️

- አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለሀገር በቀል እውቀት ትኩረት የሰጠ ነው።

- ከመዋለ ህፃናት አንስቶ የግብረገብ ትምህርት መስጠት የሚያስገድድ ነው።

- በብቃት ላይ የተመሰረተ ፣ የሞያ እና የቀለም ትምህርትንም አብሮ በሚያስኬድ መልኩ የተቀረፀ ነው።

- ከምርት እና ከተግባር ጋር የተሳሰረ ብቃትን 21ኛው ክ/ዘመን የሚፈልገውን እውቀት የሚያስጨብጥ ፣ በቴክኖሊጂ ተደግፎ እንዲሰጥ የሚያስችል ነው።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተማሪዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ 6ኛ የግብረገብ ትምህርት አይነት፣ ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ የስነዜጋ ትምህርት እንዲወስዱ ያስገድዳል።

ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጥ የነበረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ከ7ኛ ክፍል እንዲጀመር ያደርጋል።

የጤና፣ የግብርና ትምህርት አይነቶችም ተካተዋል።

12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ተማሪ በመለስተኛ ባለሞያነት በዲፕሎማ ተመርቆ ወደስራ እንዲገባም ያስችለል። ለዚህም ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ ከመደበኛ ትምህርቶች በተጨማሪ ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ በተግባር የተደገፈ ስልጠና የሚያገኙበት እንድል ተመቻችቷል።

11ኛ እና 12ኛ ክፍል በሁለት ይከፈላሉ የማህበራዊ (ሶሻል) እና የተፈጠሮ (ናቹራል) ሳይንስ በሚል።

ተፈጥሮ ሳይንስ (ናቹራል) የመረጠ ተማሪ ሰባት (7) ትምህርቶችን ለአካዳሚክስ ይጠቀምበታል፤ ይህም ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚቀመጥበት ነው።

እነዚህም የትምህርት አይነቶች ፦
- እንግሊዘኛ
- ሂሳብ
- ፊዚክስ
- ኬሚስትሪ
- ባይሎጂ
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
- #ግብርና ናቸው።

" ግብርና " 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲማሩ ይደረጋል ፤ በብሄራዊ ፈተናም (የ12ኛ ክፍል ፈተና) እንዲመጣም ይደረጋል።

ከ7ቱ ውጭ ደግሞ በምርጫ ተማሪዎች 5 የትምህርት መስኮችን መምረጥ ይችላሉ፤ እነዚህ መርጠው የሚማሩት ሲሆን ፤ የትምህርት መስኮቹ ፦
- ማኑፋክቸሪንግ
- ኮንስትራክሽን
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
- ጤና ሳይንስ እና ግብርና ሳይንስ ናቸው። ከአምስቱ አንዱን መርጠው ይማራሉ።

የማህበራዊ (ሶሻል) ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ 6 የጋራ ትምህርቶች አላቸው ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚያቀመጡበት / ጥሩ ነጥብ ካላቸው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ነው።

ከዚህ ውጭ ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፦
- ከቋንቋ እና ማህበራዊ ሳይንስ
- ቢዝነስ
- ስነ ጥበባት መካከል አንዱን መርጠው ይማራሉ።

ከላይ የተገለፁት ኮርሶች የሁሉም ሞጁሎች ተዘጋጅተው አልቀዋል።

በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠነ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ ተማሪ ለማፍራት ትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነትን ተፈራርሟል።

ሰባቱ ተቋማት የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት በዘንድሮው ዓመት 2014 ዓ/ም እስከ ስምንተኛ ለሙከራ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ፣ 11ኛ ክፍል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ባሉ ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል።

የ8ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና የሚዘጋጁበት ዓመት ስለሆነ እነሱ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም። በ2015 ሙሉ በሙሉ በመላው ሀገሪቱ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች ተግባራዊ ይደረጋል።

: ከላይ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ የተገኘው ከ30ኛው የሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።

"በ2014 #በሙከራ ደረጃ ይትገበራል " ማለት ምን ማለት ነው ?

በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ማለት ነው።

ለምሳሌ ፦ አንደኛ ደረጃ ከ40 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች አሉ ከነዛ ውስጥ የተወሰኑ (በሺዎች የሚቆጠሩ) ተመርጠው ሙሉ ትግበራ ይደረግባቸዋል።

አንድ ትምህርት ቤት ከ1 እስከ 12ኛ ክፍል ቢኖረው ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጭ በትምህርት ቤቱ ሙሉ ትግበራ ይደረጋል።

በዚህም ሙከራ ተብሎ የተገለፀው በሁሉም የሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለማይተገበር ነው።

ነገር ግን በተመረጡት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል።

ሙከራ ይደረግባቸዋል በተባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደግሞ ለተወሰኑ ክፍሎች የድሮው ለተወሰኑ ክፍሎች አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል ማለትም አይደለም ፤ በትምህርት ቤቱ ሙሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል።

(11ኛ ክፍል ግን በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ ይደረጋል) - ይህን መረጃ ከቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ነው ያገኘነው)

ስርዓተ ትምህርቱ ዝግጅት ላይ ፦
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- በመቐለ ዩኒቨርሲቲ (መጀመሪያ አካባቢ-ከግጭቱ በፊት)
- በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- በጅማ ዩኒቨርሲቲ
- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ከ200 በላይ ምሁራን ተሳትፈውበታል።

‼️በቴሌግራም ቻናላችን ወቅታዊና የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኝት ይቀላቀሉን


ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን👇👇
https://t.me/joinchat/CxKqD3ixLoJhMjc8

29/08/2021
12/07/2021



የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ ነገ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫው ነገ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ስዓት በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ ይሰጣል።

Address

Www. The Fastest University Info. Comshuwapeace@gmail. Com
Hagere Hiywot
4455

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The fastest University info posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to The fastest University info:

Share