26/12/2020
17/04/13
።
።
በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የፌደራል የ APA ሰላም አማካሪዎች እና የምስራቅ አማራ የአለም ባንክ አስተባባሪዎች እንዲሁም የከተማው አመራር እና ፎካል ፐርሰኖች በ2012 በከተማው የተሰሩ መሰረተ ልማቶች የአፈጻጸም ግምገማ የተካሄደ ሲሆን በዚ ግምገማ ላይ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር የተቀመጠውን የአለም ባንክ የመሰረተ ልማት መመዘኛ በብቃት እና በተሻለ ደረጃ በመፈጸማችን ሁሉንም ነጥቦች በመባል ጥሩ አፈጻጸም ካስመዘገቡ ከተማችን አንደኛዋ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ።
ለዚ ውጤት መሳካት እና የህዝባችንን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት ትልቅ አስተዋጾ ላደረጋችሁ ለምስራቅ አማራ የአለም ባንክ አስተባባሪዎች ለከሚሴ ከተማ ጠቅላላ አመራሮች ለፎካል ፐርሰኖች እና አጠቃላይ በዚ ልማት ስራ ላይ ጉልህ አስተዋጾ ላደረጋችሁ አካላት እና ለከሚሴ ከተማ ማህበረሰብ ምስጋናዬ የላቀ ነው።
ባለፈው አመት ባስመዘገብነው አመርቂ ውጤት መሰረት በማድረግ በቀጣይ 2013 የመሰረተ ልማት እቅዳችን ህብረተሰባችንን የሚያረኩ እና የሚያስደስቱ እንደምንሰራ እና ከዚ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደምንችል ቃል እየገባሁኝ የከተማው ህብረተሰብ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን በባለቤትነት እንዲጠብቅ እና የአካባቢውን ንጽህና እንዲጠብቅ እላለሁ።
ክቡር አቶ ኡመር አሷብ !!!
የከሚሴ ከተማ ከንቲባ!!!