World Bright College

World Bright College World Bright College
ወርልድ ብራይት ኮሌጅ
We strive for sustainable community Development.

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ጽ/ቤት በወንጌላዊ ታደሰ አበራ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ    ---  == -- ==የወንጌል አርበኛና ትጉ አጋልጋይ  ወንጌለዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ከዚህ ዓለም በሞ...
08/05/2026

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ጽ/ቤት
በወንጌላዊ ታደሰ አበራ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
--- == -- ==

የወንጌል አርበኛና ትጉ አጋልጋይ ወንጌለዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ስረአተ ቀብራቸውም በሀድያ ዞን በጊምቢቹ ከተማ ቃለ-ህይወት ቤተክርስቲያን መከነ መቃብር ሥፍራ ተፈጽሟል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ከአባታቸው ከአቶ አበራ ሀቦሬ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አዳነች ፎራጎ በሀድያ ዞን በቀድሞ በሶሮ ወረዳ በኩፋና ቀበሌ በ1956 ዓ.ም ተወለዱ።

ወንጌለዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ዕድሜያቸው ለትምህት ስደርስ የ1ኛ ደረጀ ትምህርታቸውን በወንዶ-ገነት ቃ/ህ/ቤ/ያን፣ በወንዶገነት መከነ ኢየሱስ ቤ/ክ/ያን፣የ2ኛ ጀረጀ ትምህርታቸውን በጊምብቹ ከፍተኛ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት ተከታትለዋል።

ወንጌለዊ ታደሰ አበራ በመንፈሳዊ ትምህርት ዘርፍም በቦቢቾ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅና በሆሳዕና እናት ቃ/ህ/ቤ/ያን በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በዲፕሎማና በዲግሪ ትምህርቱን ተከታትለው ተመርቋል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ገና በልጅነት ዕድሜያቸው የክርስትና እምነት ከተቀበሉ ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ መንፈሳዊ ዘርፎች ጠንካራና ለሌሎችም አርኣያ የሆኑ አገልጋይ ነበሩ።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ በወንዶገነት ከተማ ዙሪያ ፣በአሩሲ አውራጃና በሌሎችም አከባቢዎች የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ደከመኝ ሰለቸኝ ሰይሉ በትጋትና በቆራጥነት ያገለገሉ መንፈሳዊ አባት እንደ ነበሩ የህይወት ታሪካቸው ይናገራል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ በክርስትያኖች ላይ ስደትና መከራ በሚደርስበት በደርግ ዘመን የወቅቱን ስደት ፣ ዛቻ ፣ ማስፈራሪያና እስር ሳይፈሩ ራሳቸውን ለወንጌል የሰጡ ቆራጥ የወንጌል አርበኛ እንደነበሩም በህይወት ታሪካቸው ተመልክቷል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ በጊምቢቹ ቃ/ህ/ቤ/ያን ከ1985 ዓ/ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ቤተክርስቲያኗን በወንጌል አገልግሎት፣በወንጌል ሥርጭት አስተባባርነት ፣በአስተማሪነት፣ በመሪነት እና በሌሎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶች በአጠቃላይ ላለፉት 31 ዓመታት ምዕመናንን በታማኝነት ያገለገሉ ጠንካራ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩም ይነገርላቸዋል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ባሸገር በህዝብ ዘንድ በአስታራቅነት፣ በትህትና ፣በታማኝነት ፣በሰው ወዳድነትና አክባሪነት ፣በቅንነት ፣በጽኑ እምነት አቋምና፣ለሌሎች በመኖር የተመሠከሩ አባትም ነበሩ።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ባደረባቸው ህመም ምንክያት በተለያዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በህክምና ስረዱ ቆይተው ሚያዝያ 27 /08/ 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ62 ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የወንጌላዊ ታደሰ አበራ ሥርዓተ ቀብራቸውም ሚያዝያ 29/08/18 ዓ/ም በጊምቢቹ ከተማ ቃ/ህ/ቤ/ያን መካነ መቀብር ሥፍራ ዘመድ አዝማዶችና ወደጆቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ባለትዳርና የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች በድምሩ የአምስት ልጆች አባት ነበር።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፀን ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን። ቤተሰቦቻቸው !!!

ዘገባው ፦
የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ።
ዕለተ ሀሙስ ሚያዝያ 29/08/18 ዓ/ም
ጊምቢቹ

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ ( ዶ/ር) ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰ...
12/04/2026

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ ( ዶ/ር) ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን::

የትንሳዔ በዓል ከሌሎች በዓላት ለየት ያለ ትርጉም ያለ የነጻነትና የድል በዓል ነው። በትንሣኤው ሞት የተሸነፈበት፤ ሰይጣን የተረታበት ፥ የኃጢአት ዕዳ የተከፈለበት እና ደስታ የተገኘበት ነው።

በትንሳኤ ከጨለማ ወደ ሙሉ ብርሃን፤ ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገር የተቻለበት ሰይጣን የተሸነፈበት የድል በዓል ነዉ።

ትንሳኤ መዳን የታየበት ተስፋ የተገለጠበት፤ ቂም የተሻረበት ፍጹም ሰላምና ታላቅ ፍቅር የተሰጠበት ነው ሲሉም ጠቅሰዋል።

ክርስቶስ ለሰው ልጅ ደህንነት ሲል ጽኑ ግፍና በደልን በፅናት ሽሮ የአዳም ዘርን ከሞት ወደ ሕይወት ቀይሯል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ጥላቻን እና መጠፋፋትን ያስወገደ፣ ሰላምን ያሰፈነ እና ዕርቅን ያረጋገጠ መሆኑን ዶክተር ተሰማ አብራርተዋል።

ስለሆነም በዚህ ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም የትንሣኤ በዓል ስናከበር የተቸገሩ እና የኢኮኖሚ ችግር ያሉባቸውን ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይገባል ሲሉም ፕሬዚዳንቱ መልዕታቸዉን አስተላልፏሉ።

በድጋሜ መልካም የትንሳኤ ብዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ!!

ዘገባው :- የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት
ዳይሬክተሮት ነዉ::

ሚያዝያ 04/ 8/2018 ዓ/ም

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው የወርልድ ብራይት አካዳሚ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች  መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና  ከወረቀት ነጻ በሆነ አሰራር እየሰጠ...
27/01/2026

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው የወርልድ ብራይት አካዳሚ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከወረቀት ነጻ በሆነ አሰራር እየሰጠ እንዳለ አስታወቀ።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው ወርልድ ብራይት አካዳሚ ከኬጅ እሰከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የ2018 የትምህርት ዘመን የአንደኛ ሴሚስተር ፈተና በተቀመጠው መርሃ ግብር መሠረት በአግባቡ በመፈተን ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከወረቀት ነጻ በሆነ መንገድ በOnline በመፈተን ላይ ናቸው ።

ይህም በቀጣይ ለሚወስዱት ለሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና የሚያግዝ እንደሆነ ተመላክቷል።

ጥረቱ ተቋሙን መሉ በሙሉ ወደ ዲጅታል ሲስተም የመቀየር ብስራት እንደሆነም ተገልጿል።

የኮሌጁ አስተዳዳርም ለመላው የኮሌጁና የአካዳሚው ማህበረሰብ እንኳን ለዚህ ስኬት አበቃችሁ እያለ በዓይነቱ ልዩ በሆነው አሰራር ከኮሌጁ ባሸገር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ ለብሔራዊ (National Exam ) ራሳቸውን እንዲዘጋጁ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪም ተማሪዎች በቀጣይ ተከታታይ ምዘና በOnline እየወሰዱ ከወዲሁ በዕውቀት እና በስነ ልቦና ሙሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያግዝ ስሆን ተቋሙ በሀገር ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት እንዲችል ውጥኑ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ኮሌጁ አስታውቋል።

ዘገባዉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙት ዳሬክቶሬት ነዉ
ጥር 19/2018 ዓ/ም

ከኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ የክትትልና ድጋፍ ቡድንየወርልድ ብራይት ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ ላይ ኢየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ምልከታ አደረገ። የወርልድ ብራይት ፕሬዝዳንት እና መስራች...
14/01/2026

ከኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ የክትትልና ድጋፍ ቡድን
የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ ላይ ኢየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።

የወርልድ ብራይት ፕሬዝዳንት እና መስራች ዶክተር ተሰማ አበራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት ኮሌጁ "ለዘላቂ ማህበረሰብ ዕድገት እንተጋለን" የሚል መሪ ቃል አንግቦ ጥራት ያለውን ትምህርት በመስጠት በዕውቀት፣በክህሎት እና በቴክኖሎጂአጠቃቀም የበቁ ስልጣኞችን ለማፍራት እየተጋ መሆኑን አንስተዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ ስድስት ካምፓሶችን በክልሉ ባሉ ከተሞች በመክፈት ከድፕሎማ እስከ ማስተርስ በተለያዩ ፕሮግራሞችበማስተማር ላይ ይገኛል።

በባለፉት ዓመታት በTVET ፕሮግራም ብቻ 2ሺህ7መቶ ሰልጣኞችን በሆሳዕና ካምፓስ ብቻ ማስመረቁንና ከነዚህም 1ሺህ5መቶ70 ሴቶች መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ኮሌጁን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ለማድረግ የመንግስት የትምህርት ፖሊሲን መሠረት በማድረግ አስፈላጊ ግብአቶችን የማሟላት ስራ መስራቱን አንስተው አጠቃላይ ተግባሩን ዘመናዊ ለማድረግ አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረግ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ዶ/ር ተሰማ አስረድተዋል።

በኮሌጁ በሆሳዕና ካምፓስ ብቻ በሁሉም ፕሮግራሞች ከ1መቶ 38 በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር የስራ አጥነትን ችግር በመቀነሱረገድ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ዶ/ር ተሰማ አክለዋል።

በዋናነት የኮሌጁ የመማር ማስተማር ሰራና አደረጃጀቱን እንዲሁም ቤተ መጻህፍት፣የአይ ሲ ቲ ወርክ ሾፕ እና የዲጂታል ላቦራቶሪ፣ የፋይናንስና ሪጅስትራር ዘርፎችን ምልከታ ተደርጓል።

በኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሆቴልና ቱሪዝም ክትትል ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በዚህ ወቅት በሰጡት አስተያየት በኮሌጁ የመማር ማስተማር ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ጠንካራ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

ከሰልጣኝ ቅበላ ጋር ተያይዞ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በመደበኛና በአጫጭር ስልጠናዎች እንዲሁም በሌሎችም ሞዳሊቲዎች ዜጎች እንዲሰለጥኑ ኮሌጁ በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል።

ከትኩረት መስኮች አንጻር የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቅርቡ ጥናት እንዳደረገ አንስተው በጥናቱ ውጤትም ጥናቱ ስልጣኞች እንደየአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ አዋጭ በሆኑ ዘርፎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው የሚገልጽ ስለመሆኑም አንስተዋል።

ይህም ዜጎች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ወጥተው ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ ስራ ፈጥረው ራሳቸውም መለወጥ እንዲችሉ አይነተኛ ሚና እንዳለውም በአጽንኦት ተናግረዋል።

ኮሌጁ በስልጠና ሂደቱ ወቅቱ የሚጠይቃቸውን ዘርፎች በማጥናትና ስራዎችን በመስራት የዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቀነስ ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ እንዲችልም ጥሪ አቅርበዋል።

በምልከታው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊ አቶ አሰፋ ዶቼን ጨምሮ የክልልና የዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሌሎች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል::

ዘገባው የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ።
ቀን 06/5/2018 ዓ/ም

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ! መላው የክርስትና እምነት ተከታ...
07/01/2026

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለልደት መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

ይህ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በሙሉ አምላክ ሆኖ ሳለ ራሱን ዝቅ በማድረግ ከድንግል ማሪያም ስጋ ለብሶ በመወለድ እኛን ልያድነን ስል ፍጹም አምላክ የሆነው ኢየሱስ ስለእኛ ልራራልን ፍጹም ሰው የሆነበትን ለማሳየት ባልተጠበቀበት በከብቶች በረት በቤቴልሄም ስለ እኛ የተወለደበት የድንቅ ፍቅር ማሳያ ነዉ።

በዚህ የምንረዳው እኛም ከክርስቶስ በተማርነው የፍቅርን እና የትሕትናን መንፈስ ተለብሰን ሌሎችን ለማገልገል እና በምንችለው ሁሉ ለማገዝ መሥራት ይጠበቅብናል።

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ እንደ ስሙ ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ዕደገት መሰረት የሆነውን ከኬጅ እሰከ ኮሌጅ ከዲፕሎማ እሰከ ማስተርስ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ በጥራት፣ በትጋትና በታማኝነት ሕዝቡን በማገልገል ላይ የምገኝ አንጋፋ ተቋም ነዉ።

ኮሌጃችን ሆሳዕናን ዋና ካምፓስ በማድረግ ጥራት ያለውን ትምህርት ብቃት ባላቸው መምህራን ከመንግሥት ጎን በመሆን በሆሳዕና ፣ በሀላባ፣ በሀደሮ፣ በቡታጅራ፣ በዱራሜ እና በአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሕዝብ እና ለመንግሥት ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማበርከት ላይ እንገኛለን።

ኮሌጃችን ትምህርት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሰው ተኮር ሥራ እየሰራ ያለ ስሆን የትምህርቱን ጥራት በማስጠበቅ ከፍሎ ለመማር አቅም ለሌላቸው እና የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው በልዩ ድጎማ እያስተማርን ያለ ስሆን በዚህ ዓመት ከወትሮ በበለጠ እንደተማሪዎቹ ጥያቄ እና ችግር አንጻር ጥያቄያቸውን ተቀብለን ከእግዚአብሔር በተሰጠን አደራ እና ፍቅር ዘንድሮ ልዩ ተጠቃሚ የምናደርገው በመሆኑ ሁሉም የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስባለሁ።

ወድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሠላም፣የጤና የበረከት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በዓሉን ስናከብር እንደየ አቅማችን አቅም በፈቀደው ሁሉ ሌሎችን በማገዝና ማዕድ በማጋራት እንድሆን እንመኛለን።

ዘገባዉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ

በድጋሚ መልካም የገና በዓል!
ዶክተር ተሰማ አበራ

ታህሳስ 29/02/2018

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ለኮሌጁ ማህበረሰቡ ዲጂታል አሠራርን እውን የሚያደርጉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራን አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ (ዶ/ር) ገለፁ።ኮሌጁ የዲጂታል ቴ...
09/11/2025

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ለኮሌጁ ማህበረሰቡ ዲጂታል አሠራርን እውን የሚያደርጉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራን አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ (ዶ/ር) ገለፁ።

ኮሌጁ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓትን በማዘመን የመማር ማስተማር ስርዓትን ዲጂታለይዝ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተሰማ አበራ ተቋማችን እንደ ሀገር ዲጂታል አሰራርን በመተግበር በኮሌጃችን ተጀምሮ የነበረዉን ወረቀት አልባ አሰራርን የላቀ ለማድረግ እና በሀገር ደረጃ ተመራጭ ተቋም እንዲሆን የዘመኑን የቴክኖለጂ ውጤት ማስታጠቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የዚህ ዲጂታል አሠራር የተገልጋይ ማሕበረሰቡን እንግልት ከማስቀረትም ባሻገር፣ ወጭ ቆጣቢ፣ ተደራሽ እና አገልግሎቶችን በፍትሐዊነት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልጿል።

የትምህርት ሴክተር ዲጅታል እንዲሆን መንግስት አቅጣጫ ማስቀመጡን ተከትሎ ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ከኢትዮጵያ አልፎ በምስራቅ አፍርካ ግንባር ቀደም የልህቀት ተቋም እንዲሆን በቴክኖሎጂ ዲጅታል የማድረጉን ተግባር ትኩረት ሰጥተው እያከናወነ መሆኑን ዶክተር ተሰማ ጠቁመዋል።

በኮሌጁ ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ከወረቀት ነጻ አገልግሎት በማጠናከር የተማሪዎችን ዶክመንት ደህንነቱ ተጠብቆ ለዘመናት እንቆይ እና የመረጃ ሥርዓት እንድሁም የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዲጂታለይዝ እየተደረገ እንደሆነ አንስተዋል ።

ተቋሙ ተፈላጊ እና ጥራት ያለው የመረጃ ማዕከል እንዲሆን የበለፀገ ሶፍትዌር ግዢ ከኢትዮ ቴሌኮም በመፈጸም እንደ ስሙ ወርልድ ብራይት እንዲሆን አንድ እርምጃ ወደፍት እንዲጓዝ በማድረጋችን የተሰማን ደስታ ወደር የለዉም ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

በቀጣይ ሁሉንም አሰራር ዲጂታል በማድረግ የክፍያ ስራዓትን በቴሌ ብር የምከፍሉበት ፣እና ባሉበት ሆኖ ዉጤታቸዉን የሚከታተሉበት እንድሁም ምዝገባ ማካሄድ የሚችሉበት ቴክኖሎጂ ተግበራዊ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በገባነው ዉል መሠረት በፍጥነት ወደ ትግበራ የምገባ መሆኑን ዶክተር ተሰማ አረጋግጠዋል።

በኢትዮ ቴሌኮም የሪጂናል ኦፕሬሽን ማናጀር አለማየሁ አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ፣ አገልግሎታቸውን በፍጥነት ተደራሽ እንዲያደርጉና ምርታማነታቸው እንዲጨምር የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን ለትምህርት፣ለጤና፣ለግብርና እና ለሌሎች ተቋማት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

መንግስት ለዜጎች የሚሰጠውን አጠቃላይ አገልግሎት ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም አስቻይ ሁኔታዎችን የመፍጠር ስራዎቹን በጥራት ሌት ቀን እየተወጣ እንደሚገኝ ዶክተር አለማየሁ ገልጸዋል።

በዚህም ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ያለምንም የቴክኖሎጂ ውስንነት ስራቸውን መከወን የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር መፈጠሩን ዶክተር አለማየሁ ገልጿል።

ዘገባዉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ

ጥቅምት 30/02/2018

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር) በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ። የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር) በቀድሞ የ...
19/10/2025

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር) በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር) በቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እጅግ ትሁትና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የሚወደዱ መካሪ አባታችን ነበሩ ሲሉም ገልጸዋል።

ለሕዝበ ሙስሊሙ ለሁለንተናዊ ጥቅም በማገልገል እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሠላምን እና አንድነት በመስበክ የምታወቁ " ሰዉነት ይቀድማል " በሚል ንግግራቸው ብዙዎች የሚያዉቁአቸዉ ጥላቻን አምርረው የምቃወሙ አስታራቂ አባትም ነበሩ።

ለችግሮችም እራሳቸውን የመፍትሔ አካል አድርገው ጽናትን ያሳዩ ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡

ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድና ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

ዘገባው ፦ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ።
ጥቅምት 09/02/2018

ተማሪዎች ነገ የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ዛሬ ላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ  ፕሬዚዳንት እና የአካዳሚ ቦርድ ሰብሳቢ ተሰማ አበራ(ዶ/ር) ገለፁ።የ2018 የትምህርት...
15/09/2025

ተማሪዎች ነገ የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ዛሬ ላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት እና የአካዳሚ ቦርድ ሰብሳቢ ተሰማ አበራ(ዶ/ር) ገለፁ።

የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በወርልድ ብራይት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ እና በአካዳሚ ተጀምሯል፡፡

የወርልድ ብራይት አካዳሚ ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አበራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የዘንድሮ የትምህርት አጀማመር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለምረቃ በበቃበት መግስት መሆኑ ልዩ እንደሚያድረገው ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተለያዩ እስትራቴጂዎችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አንስተዋል።

በትምህርት አጀማመር ወቅት የተገኙት የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፍ ተወካይ እና የትምህርት ጥራት ባለሙያ አቶ አድነው አብዮ በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማ ለማድረግ የተማሪዎችና መምህራን ተሳትፎ የጎላ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

የተሻለ ውጤት ለመምጣት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለመስራት ጠንክሮ መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዘንድሮው ትምህርት ዘመን ተማሪዎች ስልክ እና የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት እንደሌለባቸው አቶ አድነው አስተውቀዋል።

የወርልድ ብራይት አካዳሚ ቦርድ ሰብሳቢ ተሰማ አበራ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት እና ልማት ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል።

በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በስነ-ምግባር የታነጹ እንዲሁም ሀገር ወዳድ ዜጎች እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ዶክተር ተሰማ ጠቁመዋል።

ነገ የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ዛሬ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ዶክተር ተሰማ ተማሪዎች በፈጠራ ስራ በተለይም በሳይንስ ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው መክረዋል።

በትምህርት አጀማመሩ ላይ አግኝተን ያናገርናቸው መምህራን መካከል መምህር ፀደቀ ነጋሽ እንደተናገሩት ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ለዘንድሮው ትምህርት እያዘጋጁ እንደነበር ጠቁመዋል።

ተማሪዎችም መምህራኖችን በአግባቡ በመከታተል እና የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለመምጣት መትጋት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በትምህርት አጀማመር ላይ የተገኙት ተማሪዎች በበኩላቸው ትምህርት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ጠቁመው በዓመቱ የተሻለ ውጤት ለመምጣት እንደሚተጉ ገልጸዋል።
ዘገባዉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ
መሰከረም 05/01/2018 ዓ/ም

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ አዲሱን ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም  ምኞት መልዕክት አስተላለፉ 2018 ዓ.ም አዲሱ ዓመት ለአዳዲስ ስኬቶች ራሳችን...
11/09/2025

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ አዲሱን ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

2018 ዓ.ም አዲሱ ዓመት ለአዳዲስ ስኬቶች ራሳችን የምናዘጋጅበት፤ ለእድገትና ለለውጥ አቅደን የምንነሳበት፣ ተስፋና መልካም ምኞትን የምንሰንቅበት ነው።

በአዲሱ ዓመት ዋዜማ የተመረቀው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአይቻልም መንፈስን የሰበረና የአፍሪካ ትልቅ ተምሳሌት የሆነ ፕሮጀክት የሀገራችን ስኬት ማሳያ ነው።

ግድቡ ለዘመናት በየትውልዱ እየተነገረ የሚኖር ድልን የያዘ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የወዳጅና የጎረቤት አፍሪካ ሀገራት ሁሉ ኩራት እና በኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት የደም እና የላብ ጠብታ እንድሁም የሕይወት መሰዋእትነት የተገነባ መቻልን በተግባር ያሳየንበት ነው።

በተለይም የዘንድሮው አዲስ ዓመት ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተበሰረበት ማግሥት የምናከብረው በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል።

አዲሱን ዓመት ስንቀበል የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት ሊሆን ይገባል ሲሉ ዶክተር ተሰማ መክረዋል።

ባለፈው ዓመት በኮሌጃችን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ባደረግነው የተቀናጀ ርብርብ አመርቂ ስኬት ያስመዘገብንበት ዓመትም ነበር ፕሬዚዳንቱ።

አዲሱ ዓመት የእቅዶቻችንን ፍሬ የምናይበት፣ አዳዲስ መልካም ነገሮችን የምንዘራበት፣ በትጋት እና በቁርጠኝነት የምንፈጽምበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል ዶክተር በመልዕክታቸው።

መልካም አዲስ ዓመት!
ተሰማ አበራ(ዶ/ር)

ዘገባው :- የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተሮት ነዉ::

መሰከረም 01/01/2018 ዓ/ም

18/08/2025

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ቡታጅራ ካምፓስ በድግሪ እና  በዲፕሎማ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎችን አስመርቋል።ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ቡታጅራ ...
02/08/2025

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ቡታጅራ ካምፓስ በድግሪ እና በዲፕሎማ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎችን አስመርቋል።

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ቡታጅራ ካምፓስ በዲፕሎማና በመጀመሪያ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን በደማቅ ስነስርዓት አስመረቀ።

ከተመራቂ ተመሪዎች መከካል 443 ሴቶች ናቸው።

በምረቃው መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ዳቼ እንደገለፁት፤ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ በመሆኑ የባህልና የእውቀት ሽግግር ያመጣል ብለዋል።

በሀገራችን ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ትምህርት ቁልፍ መስሪያ እንደሆነም አቶ አሰፋ አንስተዋል::

መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርቱ ዘርፍ በርካታ ምሁራንን እያፈሩ እንደሚገኙ በመግለጽ ወርልድ ብራይት ኮሌጅም ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንዳሚገኝ ተናግረዋል።

ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን ህብረተሰቡን እና ሃገርን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል አንዳለባቸውም አቶ አሰፋ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ በበኩላቸው ኮሌጁ በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 6 ካምፓሶች ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት ለሀገር እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

በአሁኑ ጊዜም ኮሌጁ ከ4መቶ በላይ ለሆኑ ቋሚ እና ጊዜያዊ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

ኮሌጁ የመንግስትን የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኮሌጁን በ2030 የምስራቅ አፍሪካ ታዋቂ የትምህርትና የምርምር ልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎችም በኮሌጅ ቆይታ የቀሰማችሁትን እውቀት በመጠቀም ራሳችሁንና ሀገራችሁን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል አለባችሁ ሲሉም ዶ/ር ተሰማ መክረዋል።

ከዛሬ ተመራቂ ከሆኑ ከ819 ተማሪዎች ውስጥ 443 ሴቶች መሆናቸዉንም ዶ/ር ተሰማ ገልጸዋል።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ አበራ በበኩላቸው ኮሌጁ በመማር ማስተማር በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎቶች በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ያገኛችሁትን እውቀት በመጠቀም ሀገርንና ቤተሰብን እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዕለቱም በትምህርታቸው ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳሊያ እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በምርቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ኃላፊና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አሰፋ ዳቼ፣ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተሰማ አበራ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የኮሌጁ ስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የሴኔት አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኮሌጁ ሠራተኞች፣ መምህራን፣ ተመራቂ ተማሪዎች የተመራቂ ተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።

ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም
ዘገባው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው

Address

916576626
Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when World Bright College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share