16/12/2025
''ከእስር ቤት ስወጣ ቅምንና ጥላቻን ይዤ ከወጣሁ ከእስር ቤት አልወጣሁም''
ኔንሰል ማንዴላ !
በማረፊያ ቤት በጊዜ ቀጠሮ ላይ በነበርሁበት ወቅት፣ ለፍትህና ለህግ በጽናት የቆማችሁ የፍትህ አካላት፣ በየቤታችሁ እና በየቤተክርስቲያኑ በጸሎት ያገዛችሁኝ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ፍትህ የጠየቃችሁ፣ ቆይታዬ እንዳይከብድብኝ ያገዛችሁኝ ሁሉ የእያንዳንዳችሁ ድጋፍ ተስፋና ጉልበት ሆኖልኝ ዛሬ ነፃ ሆኜ ስቆም፣ ስለታማኝነታችሁና ሰብዓዊነታችሁ እግዚአብሔር ሁላችሁንም በብዙ በረከት ይባርካችሁ፣ ፍቅራችሁን ይመልስላችሁ፣ በሕይወታችሁ ሁሉ ሰላምና ብርሃን ያብዛላችሁ።
በዚህ የክስና መልስ ክርክር ሂደት ውስጥ ብቆይም፣ ከማንኛውም ወገን ጋር ቅሬታ፣ ቂም ወይም ጥላቻ የለኝም። ትላንትና፣ ዛሬ ነገም ዋና ዓላማዬ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና እድገት የአቅሜን ያህል መስራት ነው።
አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏
ሀብታሙ አበበ(ዶ/ር)