27/04/2026
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ የማጠናከሪያ ትምህርት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀመረ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አንድም ተማሪ ያላሳለፉ 60 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ የማጠናከሪያ ትምህርት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።
በዚህ መርሃ-ግብር ከ60ዎቹ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ 456 ተማሪዎች ለ45 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፤
ስልጠናው ተማሪዎች በቀጣዩ ብሔራዊ ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ዝግጅት ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ትኩረታቸውን ትምህርት ላይ እንዲያደርጉና የዩኒቨርሲቲውን ሀብቶች በአግባቡ እንዲንከባከቡ አሳስበዋል።
መምህራንም የተመደበውን አጭር ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ተማሪዎቹን ለፈተና ዝግጁ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ማልደዮ በበኩላቸው፤
በክልሉ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆን አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አንድም ተማሪ ያላሳለፉ 60 ትምህርት ቤቶች መኖራቸው፣ ይህን ልዩ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ እንዳደረገው ገልጸዋል።
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ ለተማሪዎቹ የምግብ፣ የመኝታና የህክምና አገልግሎቶችን በማመቻቸት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑንም ኃላፊው አክለዋል።
ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም
ዘገባው የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://t.