እንጅባራ መምህራን ትም/ት ኮሌጅ Injibara College of Teachers' Education - ICTE

  • Home
  • Ethiopia
  • Injibara
  • እንጅባራ መምህራን ትም/ት ኮሌጅ Injibara College of Teachers' Education - ICTE
Directions

እንጅባራ መምህራን ትም/ት ኮሌጅ Injibara College of Teachers' Education - ICTE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እንጅባራ መምህራን ትም/ት ኮሌጅ Injibara College of Teachers' Education - ICTE, College & University, Injibara.

ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉበዲግሪ እና KG ዲፕሎማ መረሃ ግብሮች 2018ዓ.ም Teachers Pay Teachers
15/07/2026

ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
በዲግሪ እና KG ዲፕሎማ መረሃ ግብሮች
2018ዓ.ም
Teachers Pay Teachers

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ14ኛ ጊዜ በዲግሪና በዲፕሎማ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 818 በዛሬው ዕለት ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ፕሮግራሙ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ጌታቸው አድማሱ ያስ...
06/07/2026

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ14ኛ ጊዜ በዲግሪና በዲፕሎማ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 818 በዛሬው ዕለት ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ፕሮግራሙ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ጌታቸው አድማሱ ያስተላለፉት መልዕክት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።

የእለቱ የክብር እንግዶች ክቡራን የበዓሉ ታዳሚዎች
የዛሬው የምረቃ በዓል የአንድ ዓመት ስኬት ብቻ አይደለም። ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የተከናወኑ የብዙ ዓመታት ጥረቶች፣ ውጤቶች እና ስኬቶች የተገናኙበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። ስለዚህ ዛሬ የምናከብረው የምዕረቃ በዓል የብዙ ዓመታት ጥረትና ትጋት የወለደውን ፍሬ ነው።
ኮሌጃችን ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ ማህበረሰባቸውን በብቃት የሚያገለግሉ ብቁ እና ቁርጠኛ መምህራንን በተለያዩ ሞዳሊቲዎች ሲያሰለጥን ቆይቷል። በዚህ ሂደት ከ30000 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአገራችን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በመቅረጽ እና የሀገራችንን የወደፊት እጣፈንታ በመገንባት ላይ ይገኛሉ።
ኮሌጃችን በ2003 ዓ.ም የዲፕሎማ ተመራቂዎችን በማስመረቅ የጀመረው ጉዞ ዛሬም በበጋና በክረምት በመማር ላይ ካሉት ወ 761 ሴ 1286 ድ 2047 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ 322 በዲግሪ እንዲሁም ለ14ኛ ጊዜ 496 በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን በድምሩ 818 ዕጩ ተመራቂዎችን ለማስመረቅ አዲስ የስኬት ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ክቡራን እንግዶች፣ መምህራን፣ ወላጆች እና ተመራቂዎች
እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በቀጣይ ዓመታትም የትምህርት ጥራት በማሳደግ፣ የምርምር ሥራዎችን በማጠናከር፣ የማህበረሰብ አገልግሎቱን በማስፋት እና ብቁ ዜጎችን በማፍራት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅቷል። ከመማር ማሰተማር ፣ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ጎን ለጎን ኮሌጁ ተቋማዊ አቅሙን ለማጠናከርና እራሱን በራሱ የሚደግፍ ተቋም ለመሆን በተለያዩ ገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች ላይ በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ ረገድ የወተት ሃብት ፣ የእርሻ ስራና ሌሎች የልማት ፕሮጄክቶችን በመጀመር ማህበረሰቡን በመጥቀም ላይ የሚገኝ ሲሆን ወደፊትም እነዚህን ልማቶች አስፋፍቶ ይቀጥላል፡፡
ውድ ተመራቂዎች!
በዛሬው ቀን የምናከብረው የብዙ ዓመታት ድካም፣ ጥረት፣ ትዕግሥት፣ መስዋዕትነት እና ተስፋ የወለደውን ፍሬ ነው። ከክፍል ውስጥ ትምህርት እስከ ትምህርት ቤት ልምምድ፣ ከመጻሕፍት ጥናት እስከ ተግባራዊ ልምድ፣ ከችግር እስከ ስኬት የተጓዛችሁበት መንገድ ዛሬ በድል ተቋጭቷል።
የዛሬው ተማሪ የነገው መሪ ነው። የዛሬው ተማሪ የነገው ሐኪም፣ ኢንጅነር፣ ዳኛ፣ ሳይንቲስት እና ፖሊሲ አውጪ ነው። ስለዚህ የእናንተ አስተምህሮ የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርፃል።
መምህር ማለት የሙያ ሰው ብቻ ሳይሆን የለውጥ ወኪል ነው። ዛሬ የምትቀበሉት የዲግሪ ወይም የዲፕሎማ ማረጋገጫ ወረቀት ብቻ አይደለም። የህዝብ አደራ፣ የትውልድ አደራ እና የሀገር አደራ ነው።
መምህር ማለት እውቀትን ብቻ የሚያስተላልፍ ሰው አይደለም። መምህር ማለት ሰውን የሚገነባ፣ ባህሪን የሚቀርጽ፣ ተስፋን የሚያበራ እና ሀገርን የሚለውጥ ሰው ነው።
መምህር መሆን ስራ ብቻ አይደለም፤ አደራ ነው፣ ኃላፊነት ነው፣ ህዝብን የመገንባት ተልዕኮ ነው። የዛሬው ዓለም የሚፈልገው ትውልድን በእውቀት፣ በሥነ-ምግባር፣ በሀገር ፍቅር እና በፈጠራ ማነጽ የሚችል መምህር ነው። ስለዚህ የዛሬው የዲግሪ ወይም የዲፕሎማ ሰርተፊኬት የጉዞ መጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ኃላፊነት መጀመሪያ ነው።
እናንተ በምትመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ሁሉ የእውቀት ብርሃን ሁኑ፤ ለተማሪዎቻችሁ ተስፋ ሁኑ፤ ለማህበረሰባችሁ አርአያ ሁኑ። የምታስተምሩት ትውልድ የነገው መሪ፣ ሳይንቲስት፣ ሐኪም፣ መምህር፣ ኢንጅነር እና የሀገር ተስፋ መሆኑን ሁልጊዜ አስታውሱ።
ዓለም በፍጥነት እየተቀየረች ነው። ሰው ሰራሽ አስተዋይነት (AI)፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ኢንተርኔት እና ዓለም አቀፋዊ ትስስር አዳዲስ ዕድሎችን እና ተግዳሮቶችን ይዘው እየመጡ ነው።
በዚህ ዘመን መምህር መሆን በመጽሐፍ ውስጥ ያለውን ብቻ ማስተማር ማለት አይደለም። ተማሪዎችን እንዴት ማሰብ እንደሚችሉ፣ እንዴት ችግር እንደሚፈቱ፣ እንዴት መረጃን እንደሚገመግሙ እና እንዴት ፈጠራ እንደሚያደርጉ ማስተማር ነው።
ስለዚህ ራሳችሁን የምታሻሽሉ፣ የምታነቡ፣ የምትመራመሩ እና የምትማሩ መምህራን ሁኑ። እውነተኛ መምህር መማሩን ፈጽሞ አያቋርጥም። ዛሬ ከኮሌጁ በክብር ትለያላችሁ፤ ነገር ግን ከኮሌጁ ቤተሰብ አትለዩም። እናንተ የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አምባሳደሮች ናችሁ። በምትሄዱበት ሁሉ የኮሌጁን መልካም ስም፣ የሙያ ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት መንፈስ ተሸክማችሁ ትሄዳላችሁ። ይህ ምረቃ የአንድ ተቋም ስኬት ብቻ ሳይሆን የትምህርት ልማት፣ የማህበረሰብ ግንባታ እና የሀገር እድገት ምልክት ነው። እኛ ዛሬ የምናስመርቀው ተማሪ ብቻ አይደለም፤ የሀገር ተስፋ፣ የማህበረሰብ መሪ እና የነገው ትውልድ ገንቢ ነው።

ክቡራን ወላጆች!
የዛሬው ስኬት የእናንተም ስኬት ነው። ልጆቻችሁ በትምህርታቸው እንዲበረቱ በብዙ መስዋዕትነት ያደረጋችሁት ድጋፍ ዛሬ ፍሬ አፍርቷል። በእናንተ ጸሎት፣ ምክር፣ ፍቅር እና ትጋት እነዚህ ተመራቂዎች ለዚህ ቀን ደርሰዋል። ዛሬ በፊታችሁ የተቀመጡት ተመራቂዎች የእናንተ ጥረት ውጤት ናቸው። ለብዙ ዓመታት የከፈላችሁት መስዋዕትነት፣ የሰጣችሁት ፍቅር፣ ምክር እና ድጋፍ ዛሬ ፍሬ አፍርቷል።
አንዳንዶቻችሁ ከባድ ኢኮኖሚያዊ ችግር በመቋቋም ልጆቻችሁን አስተምራችኋል። አንዳንዶቻችሁ ከራሳችሁ ፍላጎት ይልቅ ለልጆቻችሁ ትምህርት ቅድሚያ ሰጥታችኋል። ስለዚህ ዛሬ እናንተም እንደ ተመራቂዎቹ ሁሉ ክብር ይገባችኋል። በኮሌጁ ስም ከልብ እናመሰግናችኋለን።
ውድ የኮሌጃችን መምህራንና ሰራተኞች
በትዕግሥት፣ በእውቀት እና በሙያዊ ብቃት በማስተማር ይህን ትውልድ ለማብቃት ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ የሚያኮራ ነው። የኮሌጃችን ውጤት በእናንተ ትጋት ላይ የተመሰረተ ነው። በትዕግሥት፣ በእውቀት፣ በሙያዊ ብቃት እና በከፍተኛ ተጠያቂነት ይህን ትውልድ ለማብቃት ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ በቃላት ሊገለጽ አይችልም።
ከመምህራን በተጨማሪ የኮሌጁ አመራሮች፣ የላይብረሪ ሰራተኞች፣ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የግቢ ጥበቃ እና ሌሎች የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው።

01/02/2026
የሴቶች ተሳትፎ ‼️
01/02/2026

የሴቶች ተሳትፎ ‼️

እንኳን ሰው ፈረሱም ጭምር እንግዶቹን በክብር መቀበል ያውቅበታል‼️Awi communication Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን   #አዲናስ
01/02/2026

እንኳን ሰው ፈረሱም ጭምር እንግዶቹን በክብር መቀበል ያውቅበታል‼️
Awi communication Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
#አዲናስ

01/02/2026

EthioTube

26/01/2026

ሌላኛው የዞናችን ገፀ በረከት‼️

... 📢🔊አየደረሰ ነው‼️ጥር 23/2018 ዓ.ም🫵🏻አይቀርም🏇🏻🐎🎉🏖️🎠🚆🚌✈️
26/01/2026

... 📢🔊አየደረሰ ነው‼️
ጥር 23/2018 ዓ.ም
🫵🏻አይቀርም🏇🏻
🐎🎉🏖️🎠🚆🚌✈️

ከተማችንን ለእንግዶቿ ሳቢ እና ውብ የማድረግ ሥራው በሚገባ እየተከናወነ ይገኛል።Awi communication
26/01/2026

ከተማችንን ለእንግዶቿ ሳቢ እና ውብ የማድረግ ሥራው በሚገባ እየተከናወነ ይገኛል።
Awi communication

26/01/2026

Address

Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እንጅባራ መምህራን ትም/ት ኮሌጅ Injibara College of Teachers' Education - ICTE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share