Abyssinia-Ethiopia

Abyssinia-Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abyssinia-Ethiopia, Injibara.
(1)

"በሃሳቡ ያልታሰረ ያልሞተ የለም። መብት በልመና አይመጣም ወጣቱ መፍራት ካለበት ፈጣሪንና ፈጣሪን ብቻ ነው..." በአንድ ወቅት እንደዚህ አይነት ፖለቲካዊ ዜናዎችና ቀልዶች ስትሰራ አትፈራም ...
18/06/2026

"በሃሳቡ ያልታሰረ ያልሞተ የለም። መብት በልመና አይመጣም ወጣቱ መፍራት ካለበት ፈጣሪንና ፈጣሪን ብቻ ነው..."

በአንድ ወቅት እንደዚህ አይነት ፖለቲካዊ ዜናዎችና ቀልዶች ስትሰራ አትፈራም ወይ ተብሎ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ ነበር።

ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል እጅግ ጎበዝ ባለብዙ ተስጦ ኮሜዲያን ነው። ምንም ሳይፈራ ሃሳቡን በስራዎቹ የሚያቀርብ.... በስራዎች ምክኒያት ታስሯል። እንግዲህ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ወደ እስር ቤት ማስገባት ጀምሯል።

ፍቱት ምናለ ጠመንጃ አልታጠቀም....

በተያያዘ ዜና አቤል አቡና ከሳምንታት እስር በሗላ ተፈቶ ለቤቱ በቅቷል።

17/06/2026
ለሚመለከታችሁ
17/06/2026

ለሚመለከታችሁ

የአማራ ወጣቶች እንዲታገሉ አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ!   የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ለአማራ ወጣቶች አነጋጋሪ የትግል ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አመራሮቹን ሄዳችሁ ታገሏቸው›› ሲሉ ተ...
15/06/2026

የአማራ ወጣቶች እንዲታገሉ አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ!

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ለአማራ ወጣቶች አነጋጋሪ የትግል ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አመራሮቹን ሄዳችሁ ታገሏቸው›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አረጋ ይህን ያሉት “ባህር ዳርን ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ የወጣቶች ሚና የማይተካ ነው” በሚሉ መሪ ቃላት ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቾት አልባ የሚያደርገው የአስተዳደር ብልሽት መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ አመራሩ በቀላሉ የሚገኝ፣ ቀላልና ውሳኔ መስጠት የሚችል መሆን እንዳለበት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን በተለይም በሕዝብና በሀገር ላይ የሚፈጸሙ የሌብነት ድርጊቶችን ወጣቱ በግንባር ቀደምትነት ሊታገላቸው ይገባል ብለዋል።

“ሌብነት ውስጥ የመሬት ስርቆት፣ የግብር ስርቆት፣ የኮንትራት ስርቆት ውስጥ የሚገባ፣ ግን መስረቅ ሳያንስ የሚመራውን ደሃ ሕዝብ የጎሪጥ የሚያይ አመራር ላይ በጽናት መታገል ያስፈልጋል።” ሲሉ የባህር ዳር ወጣቶች በተሰበሰቡበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በንግግራቸው ላይ የእርስዎ አስተያየት ምን ይሆን?

መጥፎ ስትሰሩ የረገመ አንደበት መልካም ስትሰሩ ያመሠግናል፥ በርቱ አሁን ጥሩ ላይ ናችሁ።
14/06/2026

መጥፎ ስትሰሩ የረገመ አንደበት መልካም ስትሰሩ ያመሠግናል፥ በርቱ አሁን ጥሩ ላይ ናችሁ።

 #የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር እና በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና በማግኘት ማህበሩን የሚመሩ አስፈጻሚዎች በማስመረጥ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ...
13/06/2026

#የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር እና በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና በማግኘት ማህበሩን የሚመሩ አስፈጻሚዎች በማስመረጥ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ ይገኛል።
በዚህ መሰረት ማህበሩ የመምህራንን መብት ለማስጠበቅ እና ከመምህራን የሚቀርቡ ጥያቄዎች በቅድሚያ ምላሽ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮችን በመለየት ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በቁጥር EUTA 0037/18 በቀን 14/09/2018 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ከቀረቡት ጉዳዮች ውስጥ የመምህራን የመኖሪያ ቤት አንዱና ዋነኛው ጉዳይ መሆኑን እየገለጽን ይህንን ችግር በቀጣይ መፍትሔ ለመስጠት እንዲቻል በዩኒቨርሲቲያችሁ ያሉ መምህራን በሚገኙበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ያልተሰጣቸው መምህራን ስም ዝርዝር ይህ ደብዳቤ ወጪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲላክ ጠይቋል።

ተብላችኋል!
12/06/2026

ተብላችኋል!

''የምንረዳው ሓቅ አሳሪው ከገዳዩ የራቀ አለመሆኑን ነው'' የሚስጥረስላሴ ታምራት አነጋጋሪ መልዕክት''የፖለቲከኛዋ ሚስጥረስላሴ ታምራት መልዕክት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ...
11/06/2026

''የምንረዳው ሓቅ አሳሪው ከገዳዩ የራቀ አለመሆኑን ነው'' የሚስጥረስላሴ ታምራት አነጋጋሪ መልዕክት''

የፖለቲከኛዋ ሚስጥረስላሴ ታምራት መልዕክት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ፈታኝ ሁኔታ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አንድምታውን በጥልቀት የገመገመና ወቅታዊ ስጋትን ያነገበ ነው።

የሚስጥረስላሴ መልዕክት :- በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያና ማሳደድ አልበቃ ብሎ የቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪዎችና አገልጋዮች እየታደኑ እየታሰሩ ከመሆናቸው ሁነት የምንረዳው ሓቅ አሳሪው ከገዳዩ የራቀ አለመሆኑን ነው ይላል።

በዝርዝር ስንመለከተው!
1. የትርክቱ መንፈስና ዋናው መልዕክት
የሚስጥረስላሴ መልዕክት ማዕከላዊ ሃሳብ "አሳሪውና ገዳዩ አንድ ናቸው" የሚል ነው። ይህ ማለት በቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ በአገልጋዮችና በምዕመናን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች (ግድያ፣ መፈናቀል፣ ማሳደድ) እና በሌላ በኩል ደግሞ ለቤተክርስቲያን ድምፅ የሚሆኑ ሰዎችን (አገልጋዮችን፣ ምሁራንንና ተቆርቋሪዎችን) ማሰርና ማሳደድ ተነጣጥለው የሚታዩ ክስተቶች አይደሉም የሚል እምነት አለው።

መልዕክቱ እነዚህ ሁለት ድርጊቶች የአንድ ትልቅ ስልታዊ እቅድ አካላት መሆናቸውንና ዓላማቸውም ቤተክርስቲያኗን መከላከያና ድምፅ አልባ ማድረግ እንደሆነ ያመላክታል።

2. ከግድያና ማሳደድ ወደ ስልታዊ ማዳከም (ከአካል ወደ ድምፅ)
• የመጀመሪያው ምዕራፍ (አካላዊ ጥቃት)፦ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ የካህናት መታረድ እና የክርስቲያኖች መፈናቀል ምዕመናንን በአካልና በስነ-ልቦና ለማዳከም የተደረጉ ጥቃቶች ተደርገው ይወሰዳሉ።

• የሁለተኛው ምዕራፍ (ተቆርቋሪዎችን ማሰር)፦ ይህ አካላዊ ጥቃት አልበቃ ብሎ፣ ስለ ጥቃቱ የሚናገሩ፣ ፍትህ የሚጠይቁ እና የቤተክርስቲያንን መብት የሚያስከብሩ አገልጋዮችና ተቆርቋሪዎች ላይ የሚፈጸመው እስር የቤተክርስቲያኗን "የመከላከያ ጋሻ" የመስበር ስራ ተደርጎ ይተረጎማል።

"ድምፅ የሚሆኑ ሰዎችን ማሰር ማለት፣ ተበዳዩ አካል ብሶቱን እንኳ እንዳይናገር አፍን የመልቀም አካሄድ ነው።"

3. "አሳሪው ከገዳዩ የራቀ አይደለም" የሚለው አንድምታ
ይህ አገላለጽ በፖለቲካዊና ህጋዊ መዋቅሩ ላይ የፅኑ ትችት ምልክት ነው። በአንድ በኩል በታጠቁ ኃይሎች ወይም በማንነት ላይ ባተኮሩ ጥቃቶች ምዕመናን ሲገደሉ በሌላ በኩል ደግሞ ህግንና ስርዓትን ለማስከበር ስልጣን ባላቸው የመንግስት አካላት አማካኝነት ተቆርቋሪዎች ሲታሰሩ በሁለቱ መካከል የጥቅምና የዓላማ ትስስር (Symbiotic Relationship) አለ የሚል ጥንካሬ ያለው ድምዳሜ ነው።

ይህ ድምዳሜ የሚያሳየው ጥቃቶቹ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ ሳይሆኑ አንዱ ሌላውን የሚደግፍና የቤተክርስቲያንን ተሰሚነትና ተጽዕኖ የማዳከም ስትራቴጂ አካል መሆናቸውን ነው።

4. ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተፅዕኖው
•የፍትህ መጓደል ስሜት፦ ምዕመናን ህግና መንግስት ጥበቃ ሊያደርግላቸው ሲገባ ይልቁኑ ድምጻቸውን በሚያሰሙት ላይ እርምጃ ሲወሰድ ሲያዩ በመንግስታዊ መዋቅሩ ላይ ያላቸው እምነት ሙሉ በሙሉ እንዲሸረሸር ያደርጋል።

• አንድነትና ፅናት፦ መሰል መግለጫዎችና ትንታኔዎች በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ያለውን የበደል ስሜት ወደ አንድነትና ይበልጥ ወደ መጽናት እንዲቀየር ያደርጉታል። ታሪክ እንደሚያሳየው የቤተክርስቲያን አገልጋዮች መታሰር ምዕመናንን ከማስፈራራት ይልቅ ለበለጠ ተጋድሎና ለአቋም ጥንካሬ ያነሳሳቸዋል።

ማጠቃለያ
የሚስጥረስላሴ ታምራት መልዕክት በወቅታዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እየገጠማት ያለውን

የክልሎች የድጎማ በጀት‼️የፌዴራል መንግስት ለክልሎች 520.6 ቢሊዮን ብር የበጀት ድጎማ መደበ‼️የፌደራል መንግስት ለ2019 ባዘጋጀው በጀት፤ ለ12 ክልሎች እና ለሁለት ከተማ አስተዳደሮች ...
10/06/2026

የክልሎች የድጎማ በጀት‼️
የፌዴራል መንግስት ለክልሎች 520.6 ቢሊዮን ብር የበጀት ድጎማ መደበ‼️

የፌደራል መንግስት ለ2019 ባዘጋጀው በጀት፤ ለ12 ክልሎች እና ለሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተመደበው የገንዘብ ድጎማ መጠን ለመጀመሪያ ጊዜ ግማሽ ትሪሊዮን ብር ተሻገረ። በዚህ የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ ባለፈው ዓመት ከድጎማ ዝርዝር ውጭ ተደርጎ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተመልሶ የተካተተ ቢሆንም፤ የተመደበለት የገንዘብ መጠን ግን ሩብ ቢሊዮን ብር እንኳ የማይሞላ ሆኗል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት የተመደበለት የገንዘብ ድጋፍ መጠን 74.53 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ለፓርላማ አባላት ከተሰራጨው የበጀት ሰነድ ላይ ተመልክታለች። የከተማ አስተዳደሩ በ2017 ከፌደራል መንግስት የተመደበለት ድጎማ 5.45 ቢሊዮን ብር ነበር።

ዘመናዊ ሄሊኮፕተር በኢራን ተመቷል-ትራምፕ‼️Apache የተሰኘ የአሜሪካ ዘመኒዊ እና ቅንጡ ሄሊኮፍተር በትናትናው በሆርሙዝ ፓትሮል እያደረገ ባለበት ሰዓት በኢራን ተመቶ መውደቁን ዶናልድ ትራ...
09/06/2026

ዘመናዊ ሄሊኮፕተር በኢራን ተመቷል-ትራምፕ‼️
Apache የተሰኘ የአሜሪካ ዘመኒዊ እና ቅንጡ ሄሊኮፍተር በትናትናው በሆርሙዝ ፓትሮል እያደረገ ባለበት ሰዓት በኢራን ተመቶ መውደቁን ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው አስፍረዋል።
በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ ሁለቱም አብራሪዎች ከሞት ተርፈዋል ብለዋል።
ኢራን ለፈፀመችው ጥቃት ምላሽ እንሰጣለን ብለዋል። የዚህ ሄሊኮፕተር ዋጋ 67 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ይገመታል።

Address

Injibara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abyssinia-Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share