Dbeki Tube

Dbeki Tube የምንለቃቸውን አስተማሪ ቪድዎችን ለመመልከት ዩቲዩብ ላይ እና በተጨማሪ ቴሌግራም ላይ
ታገኙታላችሁ
https://www.youtube.com/

27/01/2024
Today best picture ❤❤❤                        #ዘማሪትመልካምስማቸው
26/01/2024

Today best picture
❤❤❤












#ዘማሪትመልካምስማቸው
















 ጥር ዐስራ ስምንት በዚች ቀን የሰማዕታት አለቃ   አፅሙ ተቃጥሎ ተደቁሶ የተበተነበት ነው፣ የሀገረ ንጽቢን ኤጲስቆጶስ   አረፈ፣   (ባኮስ) ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መታሰቢያው ነው፣ የአልዓ...
26/01/2024



ጥር ዐስራ ስምንት በዚች ቀን የሰማዕታት አለቃ አፅሙ ተቃጥሎ ተደቁሶ የተበተነበት ነው፣ የሀገረ ንጽቢን ኤጲስቆጶስ አረፈ፣ (ባኮስ) ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መታሰቢያው ነው፣ የአልዓዛር እህቶች መታቢያቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



ጥር ዐስራ ስምንት በዚች ቀን የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ አፅሙ ተቃጥሎ ተደቁሶ የተበተነበት ነው፡፡

ይኸውም ሰባ ነገሥታት ማሰቃየት በሰለቻቸው ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አውጥተው ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት ንጉሥ ዱድያኖስ አዘዘ፡፡ አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረግፉት ድረስ እንዲህ አደረጉበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከስቃይ ብዛት የተነሳ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ሥጋውንም በሙሉ በእሳት አቃጠሉት አመድም ሆነ፡፡

ከሐዲው ንጉሥ ዱዲያኖስ የተቃጠለውን የሥጋውን አመድ አፍሰው በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ወስደው ምዕመናን ራሩን አመዱን እንኳን እንዳያገኙት በነፋስ እንዲዘሩት አዘዘ፡፡ ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ማለት ነው፡፡ ወታደሮቹም የሥጋውን አመድ በተራራ ላይ ነስንሰው የተመለሱበት፣ የሥጋው አመድ ያረፈበት ዕፅዋት ሁሉ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ያሉበት፣ ጌታችን ከመላእክት ጋር ተገልጦ አራቱን የምድር ነፋሳትንም የቅዱስ ጊዮርጊስ የሥጋውን ትቢያ እንዲሰበስብ አዞ። "የኔ ሆይ! የመረጥኩህ ወዳጄ ጊዮርጊስ ከሞት ተነሥ አትፍራ፤ እኔ አዝዤሀለሁና" ሲል ኀያሉን ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠራው። ያን ጊዜ ልዑል ንዑድ ጊዮርጊስም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ምንም ሕማም ሳይኖርበት ተነሣ።

መድኃኒታችንም ባረከው። "አትፍራ፤ ይኸንን ከሀዲ ንጉሥም እስክታሳፍረው ድረስ እኔ አጸናሀለሁ። ከእንዲህስ ወዲህ አምላኩ ከእጃችን ሊያአድነው አይችሉም እንዳይሉ እነዚህን ከሐድያን ነገሥታትና የረከሱ ጣዖታቸውን ታሳፍራቸው ዘንድ ተነሣና ወደ አገር ውጣ፤ ሰላሜ ለዘለዓለም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ተናግሮ ሳመው። በፍጹም ምስጋናም ወደ ሰማይ ዐረገ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጌታችን ይህንንም ቃል ኪዳን የተቀበለበት ቀን ነው፡፡

✝ Dbeki Tube

26/01/2024

Dbeki Tube🥰🥰🥰:::
24/01/2024

Dbeki Tube🥰🥰🥰
:
:
:





















07/01/2023

Address

Jimma
#KONTA

Telephone

+251928535428

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dbeki Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share