TVET Trainer's Sound

TVET Trainer's Sound የ TVET አስተማሪዎች እየገጠማቸው ያለው ችግሮችን በ አንድ ድምፅ�

09/09/2024
02/09/2024

It is time for training. We are all participating in the training.
Where is your training location?
How is it going?

02/09/2024
27/08/2024

ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2016(ኢዜአ)፦ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የቴክኒክና ሙያ የአሰልጣኝ መምህራን አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት መደረጉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስቴሩ ከነገ ጀምሮ "ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት" በሚል መሪ ኃሳብ ለ12 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እንደሚያስጀምር አስታውቋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ሥልጠናው አዲስ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ወደ ሥራ መግባቱን መሠረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው በዚሁ ሥልጠና 24 ሺህ የሚደርሱ ሰልጣኞች እንደሚሳተፉና ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 በ17 ማዕከላት በሁሉም ክልሎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ሥልጠናው አዳዲስ የሪፎርም እሳቤዎችንና የፖሊሲ ጉዳዮችን አረዳድ ተቀራራቢ ወደ ሆነ ግንዛቤ በማድረስ የዘርፉን እሳቤዎች በውጤታማነት ለመተግበር እንዲያስችል ታሳቢ ያደረገ ሥልጠና መሆኑን አስረድተዋል።

ሥልጠናው ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል የሰው ኃይል ለማፍራት ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ አሰልጣኞች ላይ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

ሥልጠናው አዳጊ፣ ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃትን በማላበስ የአሰልጣኞች አቅም የሚገነባበት መሆኑን ተናግረዋል።

በነገው ዕለት የሚጀመረውን ሥልጠና በውጤታማነት ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጸው፤ ሁሉም አካል የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

26/06/2024
For graduating students
11/08/2023

For graduating students

For TVTI Summer students.
02/08/2023

For TVTI Summer students.

25/07/2022

በመጪው ዓመት በቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ይደረጋል
************************

በመጪው ዓመት በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የትምህርት እና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ጥናት መሠረት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የቴክኒክ እና ሙያ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ጉድለቶች እንዳሉ በጥናት መለየቱን የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተሻለ ብሬቻ ገልጸዋል።

እነዚህን ጉድለቶች የሚሞላ እና ሠልጣኞች በሁሉም ሙያዎች የተሟላ እውቀት እና ክህሎት ይዘው እንዲወጡ የሚያደርግ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመጪው ዓመት ተግባራዊ ይደረጋል።

እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት ዜጎችን በሥራ ዓለም ላይ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ የሚያደርጉ ክህሎቶች ከማካተት አንጻር ሥርዓቱ ትምህርቱ ጉድለት እንደነበረበት አመልክተው፣ ከጉድለቶቹ አንዱ እና ትልቁ ሥርዓተ ትምህርቱ ትኩረት የሚያደርገው የቴክኒካል ክህሎት ብቻ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ለምሳሌ ሥልጠና የሚሰጠው የእንጨት ሙያ ከሆነ በእንጨት ሙያ ላይ ብቻ ያተኮረ ትምህርት ሲሰጥ እንደቆየ አውስተው፣ ይህ ደግሞ ሠልጣኞች ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም ሲሠማሩ በሥራ መስካቸው ሆነ በሥራ ፈጠራ ውጤታማ እንዳይሆኑ ክፍተት ፈጥሯል ብለዋል።

ሌላው በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተፈላጊ የሆኑ የሥራ ፈጠራና የዲጂታል አይሲቲ እውቀቶችንና ክህሎቶችን በአግባቡና በተደራጀ መንገድ ያላካተተ በመሆኑ ሥርዓተ ትምህርቱን ማሻሻል ማስፈልጉን አብራርተዋል።

አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት እነዚህን ክፍተቶች በተሟላ መልኩ የሚያሟላ ነው ያሉት ዶ/ር ተሻለ፣ ሥርዓተ ትምህርቱ የሚመለከታቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶችን እና ኢንዱስትሪዎች ጭምር ተሳትፈውበት የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ሥርዓተ ትምህርቱ ሠልጣኞች ኮሌጆች ውስጥ እያሉ እንዴት ሥራ መፍጠር እና ራሳቸውን ለሥራ ማዘጋጀት እንደሚችሉ በተግባር የሚለማመዱበት ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው፣ ዘመኑ ያፈራውን የቴክኖሎጂ እውቀት እና ክህሎት የሚያስጨብጥ ነውም ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በአዲሱ ዓመት በአገሪቱ ባሉ በሁሉም የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ተግባራዊ ለማድረግ የማስተዋወቅ እና የዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ከ1 ሺህ 800 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ያሉ ሲሆን የተቀረጸው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሚቀጥለው አዲሱ ዓመት በእነዚህ ተቋማት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ታውቋል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

For Ethio china fresh students only
20/04/2022

For Ethio china fresh students only

16/03/2022
04/03/2022

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ/ም ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
***************

1. የምደባ ቦታችሁ በቀድሞው በተመደባችሁበት ሲሆን በሰርቬይንግ ቴክኖሎጂ (Surveying Technology) እና በሮድ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ (Road Construction Technology) ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የተመደባችሁ መሆኑን፤

2. በመጀመሪያው ምደባ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ እና የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ ተለያዩ ካምፓሶች ተበትናችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች በጥያቄያችሁ መሰረት ወደ መጀመሪያው ምድብ ቦታችሁ ማለትም አዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት እንድትመለሱ የተደረገ መሆኑን፤
ነገር ግን በየወሩ ከሚከፈለው ስድስት መቶ ብር (ብር 600) ውጪ ምንም አይነት የመኝታም ሆነ የምግብ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከወዲሁ እንድታዘጋጁ፤

3. በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ (Manufacturing Technology) በአምቦ እና አሰላ ካምፓሶች ለመማር ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በቁጥር ማነስ ምክንያት ወደ የተመደባችሁ መሆኑን እንድታውቁ፤

4. በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህርታችሁን ለመከታተል በዋናው ጊቢ ፈተና የወስዳችሁ ተማሪዎች ወደ ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን፤

5. የመመዝገቢያ ቀን ቀድሞ በየሳተላይቶቻችሁ በተገለፀው መሰረት /2014ዓ/ም ሲሆን በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን /2014 መሆኑን አውቃችሁ በእለቱ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ለበለጠ መረጃ
 +251918029487 Bahir Dar
 +251911183073 Gen Wingate
 +251913513977 Kenenisa
 +251912066165 Adama
 +251913155598 Amboo
 +251913487801 Wolkitie
 +251910090164 Tegbare Eid
 +251921636755 Kombolcha
 +251912691060 Dire Dawa Polytechnic
 +251913503317 Arba minch
 +251910069776 Ethio Italy
 +251912498943 Holeta

የሳተላይት ማዕከላት ማስተባባሪያ ዳይሬክቶሬት

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TVET Trainer's Sound posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share