Jinka poly technic College

Jinka poly technic College This is the official facebook Page of Jinka Poly technic collge

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተመራቂ ሰልጣኞች ከክቡር እንግዶችና ከኮሌጃችን ዲን ሽልማታቸውን ሲቀበሉ በፎቶ..... (ጂፖቴኮ)ተመራቂዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!!           Congratu...
15/08/2026

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተመራቂ ሰልጣኞች ከክቡር እንግዶችና ከኮሌጃችን ዲን ሽልማታቸውን ሲቀበሉ በፎቶ.....

(ጂፖቴኮ)
ተመራቂዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!!
Congratulations!!

ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
Phone= 0467750459
E-mail=[email protected]

''የአከባቢውን የመልማት ጸጋ መሰረት በማድረግ በእንስሳትና ሰብል ልማት ዘርፎች የልቀት ማእከል ለመሆን የሚያስችለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናውነ ባለበት ወቅት በመመረቃችሁ እጀግ ደስ ...
15/08/2026

''የአከባቢውን የመልማት ጸጋ መሰረት በማድረግ በእንስሳትና ሰብል ልማት ዘርፎች የልቀት ማእከል ለመሆን የሚያስችለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናውነ ባለበት ወቅት በመመረቃችሁ እጀግ ደስ ሊላችሁ ይገባል'' ክቡር አቶ አፌዶ ወርቁ የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊና የመንግት ዋና ተጠሪ የእለቱ የክብር እንግዳ


ነሐሴ 9/2018 (ጂፖቴክ) ጂንካ

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በቀንና በማታ መርሀግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

የኮሌጃችን ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትና የምረቃ ማብሰሪያ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የትምህርት መስክ ማህበረሰባቸውን በእውቀት በተግባር የታገዘ ስራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ አሳስበዋል።

አቶ አፌዶ ወርቁ የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊና የመንግት ዋና ተጠሪ ተመራቂ ሰልጣኞች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልኩ የዛሬ ተመራቂዎች ኮሌጃችን በክልል ደረጃ 1ኛ በመውጣትና በግብርናው ዘርፍ የአከባቢውን የመልማት ጸጋ መሰረት በማድረግ በእንስሳትና ሰብል ልማት ዘርፎች የልቀት ማእከል ለመሆን የሚስችለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያናውነ ባለበት ወቅት በመመረቃችሁ እጀግ ደስ ሊላችሁ ይገባል ሲሉ በተጨማሪም በኮሌጁ እየተከናወነ የግብርና እና የቴክሎጂ ምርቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ መሆናቸውን አንስተው ለተግባራቱ የኮሌጁን ዲኖች አሰልጣኞች አመስግነዋል።

ተመራቂዎችም Electrical and Electronic equipment surveying -plumbing -Garment production -HNS -Web development & Date administration -Cadastral Surveying and mapping -Automotive mechanics -Tour guide-Crop production -Animal production. የስልጠና ዘርፎች ያስመረቀ ሲሆን።

በምረቃ መርሃግብር ላይም የክልልና፣ የዞንና አመራሮች የኮሌጁ ስራ አመራር ቦርድ የከተማና የወረዳ አመራሮች የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች የኮሌጀ ዲኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም በየትምህርት ክፍሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ እንዲሁም አጠቃቂ ከኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን በመሸለም ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "
ለበለጠ መረጃ= 0467750459
ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
Phone= 0467750459
E-mail=[email protected]

በመካሄድ ላይ... ኮሌጃችን ለ23ኛ ግዜ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 335 ሰልጣኞች በድምቀት እያስመረቀ ይገኛል።ነሐሴ 9/2018 ።  (ጂፖቴኮ)ተመራቂዎቻችን እንኳን ደስ አላች...
15/08/2026

በመካሄድ ላይ... ኮሌጃችን ለ23ኛ ግዜ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 335 ሰልጣኞች በድምቀት እያስመረቀ ይገኛል።
ነሐሴ 9/2018 ።

(ጂፖቴኮ)
ተመራቂዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!!
Congratulations!!

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና Imagine One Day ለቀጣይ 5 ዓመታት በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ሰነድ ተፈራረመ።   ነሐሴ 7/2018 (ጂፖቴክ) ጂንካ የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እ...
13/08/2026

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና Imagine One Day ለቀጣይ 5 ዓመታት በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ሰነድ ተፈራረመ።


ነሐሴ 7/2018 (ጂፖቴክ) ጂንካ

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና Imagine One Day ጋር የተማሪዎችን የሙያ ክህሎት በማሳደግና የሥራ ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር ለቀጣይ 5 ዓመታት በጋራ ለመሥራት የጋራ ግብ ስምምነት ተፈራርሟል።

የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MoU) በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ እና በፖሊ ቴክኒክ (TVET) ተቋሙ መካከል የሚኖር የተግባርና የትብብር ክፍፍል የትብብር መስኮች (Areas of Collaboration): የመምህራን ሥልጠና፣ የትምህርት ግብዓቶች አጠቃቀም እና የቴክኒክ ድጋፎች የስምምነቱ ጸናት ጊዜና ሁኔታዎች (Validity & Terms): ስምምነቱ የሚፀናበት ጊዜ፣ የክትትልና ግምገማ (Monitoring & Evaluation) የሚጨምር ሲሆን ሥርዓት እና የስምምነት ማሻሻያ ደንቦች የትምህርት ጥራትን ማሻሻል፣ የመምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን አቅም መገንባት ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት መግቢያ ሰነድ(Mou) ሰነድ የፊርማ ስምንነት ተካሄዷል።

የስምምነቱ ዓላማ ዜጎችን በሙያና ክህሎት በማብቃት ሥራ ፈላጊ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማስቻል ነው በመሆኑም የሁለቱ ተቋማት የጋራ ዓላማ ዜጎችን በሥልጠና በማብቃት ከሥራ ዕድል ጋር ማስተሳሰር በመሆኑ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በጋራ በመሥራት የሚጨበጥ ውጤት እንደሚመዘገብ ተገልጿዋል።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
Phone= 0467750459
E-mail=[email protected]

እንኳን ደስ አላችሁ!!የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም የፊታችን ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ያካሄዳል።                                 Con...
10/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!!
የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም የፊታችን ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ያካሄዳል።


Congratulations!!
Jinka Polytechnic College will colorfully celebrate its students' graduation program on August 16, 2026.

ማስታወቂያ  ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም  (ጂፖቴኮ)የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ እና በግል ለCOC ምዘና የተመዘገባችሁ በሙሉ የCOC ምዘናው በሁለት ዙር ስለሚሰጥ በአንደኛው ዙር ...
03/08/2026

ማስታወቂያ

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም (ጂፖቴኮ)

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ እና በግል ለCOC ምዘና የተመዘገባችሁ በሙሉ የCOC ምዘናው በሁለት ዙር ስለሚሰጥ በአንደኛው ዙር ከክልሉ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት በHOLESTIC ማለትም በአንዴ ደረጃ አራት ምዘና የምሰጥ ሲሆን::

በቀን 30/11/2018 ዓ.ም እና በቀን 1/12/2018ዓ.ም ስለሚሰጥ በቀን 29/11/2018 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ስለሚሰጥ በኮሌጁ ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ሁለተኛውን ዙር ማለትም STREAM ሲሆን በየደረጃው የምዘና ምዘና ነው። ስለሆነም ቀኑን በቅርቡ የምናሳውቅ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሳሰብን ዲፓርትመንቶች ለተማሪዎች ለፈተናው አስፈላጊ የሆነውን ነገር ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
= 0467750459
E-email=[email protected]

በበና ፀማይ ወረዳ የቀይአፈር ቅዱስ ባኮስ ትምህርት ቤት ተመራቂ ተማሪዎች በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጀ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።   ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም  (ጂፖቴኮ) በበና ፀማይ ወ...
13/07/2026

በበና ፀማይ ወረዳ የቀይአፈር ቅዱስ ባኮስ ትምህርት ቤት ተመራቂ ተማሪዎች በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጀ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።


ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ጂፖቴኮ)

በበና ፀማይ ወረዳ የቀይአፈር ቅዱስ ባኮስ ትምህርት ቤት ተመራቂ ተማሪዎች በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጀ በመገኘት ጉብኝት አድረገዋል በጉብኝቱም የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና ቦታዎችን ጉብኝት አድርገዋል።

የኮሌጃችን ም/ዲን አቶ ምርድ ማደሪያ ለተማሪዎችና እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና አጠቃላ በኮሌጃችን እየተከናወኑ ስለሚገኙ ስራዎች ስለሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎችና የቴክኖሎጂ የግብርና ምርት ተግባራት አጠቃላይ ገለፃ አድርገዋል።

በጎብኝቱ ላይም ተመራቂ ተማሪዎች የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤትና የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎችና መምህራን የተገኙ ሲሆን።
በመጨረሻም የትምህርት ቤቱ ስራአስኪያጅ ቀሲስ ሊቀ ካህናት ነቢያት ደሪባ በኮሌጁ ስለተደረገላቸው ትብብርና አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
= 0467750459
E-email=[email protected]

''እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን'' የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደቡብ ኢትዮጰያ ስራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጀነት በተካሄደው የቴክኖሎጂ  ውድድር አሸናፊ ሆነ።   ሰኔ 25 ቀን 2018...
02/07/2026

''እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን''

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደቡብ ኢትዮጰያ ስራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጀነት በተካሄደው የቴክኖሎጂ ውድድር አሸናፊ ሆነ።


ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም (ጂፖቴኮ)

በውድድሩ ላይም በአራት ዘርፎች ማለት በአሰልጣኝ ቴክኖሎጂ፣በተግባራዊ ጥናትና ምርምር፣በሰልጣኝ ተክኖሎጂ፣በኢንተርፕራይዝ ቴክኖሎጂ ውድድር ተሳትፏል።

ኮሌጃችን ከተወዳደባቸው አራት ዘርፎች በሦስት ዘርፎች 1ኛ በመውጣት የሜዳልያ ተሸላሚ እንዲሁም ከአጠቃላይ ኮሌጆች አንደኛ በመውጣ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የኮሌጃችን ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው ለዚህ ስኬት እውን መሆን አስተዋፅኦ ያደረጉ የኮሌጁ ስራ አመራር ቦርድ፥ የኮሌጅ አመራሮች፥ አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች፣የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተወዳዳሪዎችን እንድሁም የዞኑ እና የጂንካ ከተማ ነዋሪዎችን አመስግነዋል።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "
ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
Phone= 0467750459
E-mail=[email protected]

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጀ ''በቴክኖሎጂ  እንቅደም ፤ ወደ ስኬት እንድረስ'' በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጰያ ስራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጀነት የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይና ውድድር በይፋ ተጀምሯል...
30/06/2026

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጀ ''በቴክኖሎጂ እንቅደም ፤ ወደ ስኬት እንድረስ'' በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጰያ ስራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጀነት የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይና ውድድር በይፋ ተጀምሯል።


ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (ጂፖቴኮ)

በፕሮግራሙ ላይም የደቡብ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊነ አቶ በዛብህ ገበየሁ የመክፈቻ ንግግር የተደረገ ሲሆን በማስቀጠልም የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

በኮሌጃችን የቀረቡ የቴክኖሎጂ ምርቶች የማህበረሰብ ችግር የሚፈቱና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከቀረቡ ምርቶቸ ከፍ ያለ የቴክኖሎጂ አቅም ያላቸውና ከውድድሩም የተሻለ ውጤት የሚጠብቁ የገለጹት የኮሌጃችን ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው ናቸው።

ኮሌጃችንም በኤግዚቢሽን ላይም የቴክኖሎጂ ምርቶች ለእይታ ያቀረበ ሲሆን የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያና፣ መፍጫ፣ መከትከቻ ማቀላቀያ ፓሌት የብሎኬትና የጭቃ ጡብ ማምረቻ ዘመናዊና ወጪ ቆጣቢ የዶሮ ቤቶችን አቅርቧል።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "
ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
Phone= 0467750459
E-mail=[email protected]

በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስተባባሪነት የጥናትና ምርምር የቴክኖሎጂ ውድድር ተካሄደ።  ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም (ጂፖቴኮ) በውድድሩ ላይም የክላስተር ኮሌጆች ማለትም የጋዘር ትምህርትና ...
25/06/2026

በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስተባባሪነት የጥናትና ምርምር የቴክኖሎጂ ውድድር ተካሄደ።



ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም (ጂፖቴኮ)

በውድድሩ ላይም የክላስተር ኮሌጆች ማለትም የጋዘር ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ፣የሌሞ ጌንቶ፣ገሊላና፣ የቱርሚ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የተወጣጡ ተወዳዳሪዎች ተሳተፊ ሆነዋል።

ውድድሩም በኣሪ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ በስሩ ባሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትና በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር አስተባባሪነት የተዘጋጀ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እና የቴክኖሎጂ ስራዎቻቸውን በማቅረብ ተሳትፈዋል።

በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር አስተባባሪነት የተዘጋጀወ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር በተቋማቱ የሚቀርቡ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ጥራታቸው የተረጋገጡና የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ሥራዎች እደሆኑ ተመላክቷል።

"ብቁና ተነሳሽነት ያለው ዜጋ እንፈጥራለን "

ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይወዳጁን:-
Telegram :-https://t.me/T_JCIC
Facebook :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100066875390848
Phone= 0467750459
E-mail=[email protected]

Address

Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jinka poly technic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share