Gelilan tour Democracy

Gelilan tour  Democracy Dear followers of this page, this page called Galilan Tour Democracy is advertising, promot and News campany.

16/08/2026
16/08/2026
16/08/2026

ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ለህብረተስብ ክፍሎች የንቃቴ ህግ ትምህርት ለመስጠት የዝግጅት መደረጉን የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታወቀ

#ገሊላ | ነሀሴ 10/2018 ዓ.ም(የኣሪ ማህበረሰብ ሬዲዮ)፦ የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ለህብረተስብ ክፍሎች "የንቃቴ ህግ ትምህርት" ለመስጠት የዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።

የንቃተ ሕግ ትምህርት ዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን፣ እንዲሁም ሕጋዊ ግዴታዎቻቸውን እንዲያውቁና እንዲረዱ ለማድረግ የሚሰጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሆኑን የባስከቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ተናግዋል።

በተለያዩ የህግ ርዕሶች ላይ ለሚሰጠው የንቃተ ህግ ትምህርት የተዘጋጁ ስነዶች ከነሀሴ 11/2018 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 15/2018 ድረስ "የንቃቴ ህግ ትምህርት" የሚሰጥ መሆኑን ያስታወቁት የመምሪው ኃላፊ ይህም በላስካ ዙሪያ ወረዳ እና በላስካ ከተማ ላይ ከ10ሺ በላይ ለምሆኑ ለህብረተስብ ክፍሎች ይሰጣል ብለዋል።

በላስካ ዙሪያ ወረዳ የግንዛበ ስራ በክላስተር የሚሰጥ ስሆን ይህም ኦብጫ ክላስተር፣ ዋጳ ክላስተር፣ ደብጻ ክላስተር እና ጋራ ክላስተሮች ከዚህ በፊት በተሰሩ ዳሰሳ ጥናት መሰረት የተለዩ እና ላስካ ከተማ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ ለመንግስት ሰራተኞዎች በየተቋማቱ የህግ ግንዛቤ ሥራዎች እንደምሰራ ጭምር አስታውቀዋል።

የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ለዚህ ስራ ስኬት የመንግስት የስራ ኃላፍዎች እና መላው የከተማም ሆነ የዙሪያ ወረዳ ማህበረሰብ ክፍሎች ከፍትህ ተቋማት ጎን እንድሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው

ለተጨማሪ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገፃችንን ይከታተሉ፦

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/AriCommunityRadioFm
ቴሌግራም፦ https://t.me/acrsfmAriCommunityRedioStationFM
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/aricommunityradiostation
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/.fm93.9
ዋትሳፕ፡- [email protected]" rel="ugc" target="_blank">https://whatsapp.com/[email protected]

ለበለጠ መረጃ(ጥቆማ)፦ በ0463212054, 0463212123, 04632122258, 0923126016 ላይ በመደወል አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

የማህበረሰብ እውነተኛ ድምጽ !!
የኣሪ ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 93.9

14/08/2026

ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመላ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት

በሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ ታሪክና ባህል ሆኖ እየተከናወነ ያለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መካሄድ ከጀመረ እነሆ ዛሬ ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም አንድ ወር አስቆጠረ፡፡

ሂደቱ በሀገራችን ሲከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመሆኑ፣ ለምክክር የቀረቡ አጀንዳዎች እጅግ መሰረታዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ እንደመሆናቸው እንዲሁም የሀገራችንን ብዙኃነት መሰረት ያደረጉ ፍላጎቶች በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ጉባኤው የብዙዎች መነጋጋሪያ መሆኑ ለኮሚሽኑ አስገራሚ ነገር ሆኖ አልተገኘም፡፡

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያዊያን የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮቻቸው ላይ ለመምከር ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ በምክክሩ ሂደት እያሳዩት ያለው መከባበር፣ መደማመጥ እንዲሁም እያካበቱት ያለው ማህበራዊ ግንኙነት እጅጉን አመርቂ እና ተስፋ ሰጪም ነው፡፡

ይህ በሀገራችን አዲስ የሆነው የምክክር መድረክ ብዙዎች እንዲተዋወቁ፣ ‘የአንተ ችግር የእኔ ነው’ እንዲባባሉ፣ ለነገ ሀገራቸው የሚጠቅም የጋራ ሃሳብ በመግባባት እንዲያፈልቁ እያስቻለ ይገኛል፡፡
ሂደቱ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት አንዱን ምዕራፍ እየጨረሰ ወደ ሌላው ምዕራፍ ሲሸጋገር ቆይቶ አሁን ላይ ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

በኮሚሽኑ ግምገማ መሰረት ያለፈው አንድ ወር የምክክር ሂደት ስኬታማ ሥራዎች የተሰሩበት፣ ምክክር ባህል እንዲሆን መሰረት የሚጥሉ አዳዲስ ጉዳዮች የታዩበት ነው፡፡

ይህ ማለት ግን ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ ነበረ ማለት አይደለም፡፡ አለመግባባት የሚመስሉ ነገሮች ተስተውለዋል፡፡ እነዚህ ነገሮች አለመግባባት አለ ብለን ለተቀመጥን ወገኖች እንግዳ መሆን እንደሌለባቸው የኮሚሽኑ እምነት ነው፡፡

ኮሚሽኑ ካለው አሰራርና ልምድ በመነሳት እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ሊያግጥሙ እንደሚችሉ ምክክሩን ከማስጀመሩ በፊት በውል የተረዳው ጉዳይ ነው፡፡ጉዳዩ እንግዳ የመሰለው ለተመካካሪዎችና ወክለው ለመጡት አካል ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በዚህ ስጋት ላይ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች የሚያሰራጩት ሀሰተኛ መረጃ ሲጨመርበት ደግሞ ነገሩን ምን ያክል ውስብስብ እንደሚያደርገው ኮሚሽኑ ይረዳል፡፡

ለዚህ ነበር ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን በኮሚሽኑ ከሚወጡ መረጃዎች እንዲሁም በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ከሚያወጡት መረጃ ውጪ ካሉ መረጃዎች ራሱን በማቀብ ከሀሰተኛ መረጃዎች እንዲጠበቅ ሲያሳስብ የቆየው፡፡

አሁንም ምክክሩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን ተከትሎ የተዛቡ መረጃዎች በስፋት መውጣታቸውን ስለሚቀጥሉ በድጋሚ መላው ኢትዮጵያዊያን ኮሚሽኑ ከሚያወጣቸው መረጃዎች እንዲሁም በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ከሚያወጡት መረጃ ውጪ ያሉ መረጃዎችን ባለመከታተል ራሱን ከሀሰተኛ መረጃ እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ በድጋሚ ያሳስባል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችም ጫፍ ያልደረሰ መረጃ በማጋራት በህዝብ ላይ ያልተገባ ብዥታና መደናገርን ከመፍጠር እንድትቆጠቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ ያሳስባል።

መሰል ተግባራትን ኮሚሽኑ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት እየፈፀሙ ያሉ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑንም ማሳወቅ ይወዳል። ይህ ክትትልና እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ማሳሰብ ይወዳል።

ሀገራዊ ምክክር ለሀገራዊ መግባባት!

Address

Jinka

Telephone

+251924715008

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gelilan tour Democracy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share