ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College

  • Home
  • Ethiopia
  • Kelela
  • ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College
Directions Website Contact the university

ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College የኮሌጁ ራዕይ
በኢንዱስትሪ ውስጥ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት።

የኮሌጃችን ኢንስትራክተር የሆኑት አህመድ ጋሻው ይማም(እጩ ዶክተር) ከነዚህ የመጀመሪያ ዙር የ PhD ተማሪዎች አንዱ ናቸው። የኮሌጃችን የስራ ባልደረባ መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንሎት እ...
16/08/2026

የኮሌጃችን ኢንስትራክተር የሆኑት አህመድ ጋሻው ይማም(እጩ ዶክተር) ከነዚህ የመጀመሪያ ዙር የ PhD ተማሪዎች አንዱ ናቸው። የኮሌጃችን የስራ ባልደረባ መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንሎት እንመኛለን።

የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ምዘና (CoC) በማስመዘን ላይ ይገኛል​ከለላ፤ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኞችን ተወዳዳሪነትና ብቃት ለማረጋገጥ...
22/06/2026

የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ምዘና (CoC) በማስመዘን ላይ ይገኛል
​ከለላ፤ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም
​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኞችን ተወዳዳሪነትና ብቃት ለማረጋገጥ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። በዚህም መሠረት ኮሌጁ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑ የቤት አያያዝ (Domestic Work) ሰልጣኞችን እና በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ የመደበኛ ሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ምዘና (CoC) በስኬት በማስመዘን ላይ ይገኛል።
​ኮሌጁ በዛሬው ዕለት (ቀን 15/10/2018 ዓ.ም) እንደገለጸው፣ ይህ የሙያ ብቃት ምዘና ሰልጣኞች በንድፈ-ሀሳብና በተግባር የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር የሚያሳዩበት ሲሆን፣ ወደ ስራው ዓለም ከመሰማራታቸው በፊት የበቃ የሰው ኃይል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
​በተለይም ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ዝግጁ እየሆኑ ያሉ የቤት አያያዝ (Domestic Work) ሰልጣኞች በሂደቱ ማለፋቸው በውጭ ሀገር ያላቸውን ተወዳዳሪነትና ደህንነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ የመደበኛ ሰልጣኞች ምዘናም በተመሳሳይ የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ብቁ ባለሙያ ለማፍራት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
​ኮሌጁ የምዘና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት በሙሉ አሟልቶ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ሰልጣኞችም በከፍተኛ ተነሳሽነት ምዘናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

#ከለላፖሊቴክኒክኮሌጅ #የሙያብቃትማረጋገጫ #ምዘና #ሙያዊክህሎት #ዕውቀት #ተግባር #ስኬት

!
!

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ11ወራት ውስጥ ለ290 ነባርና አድስ ኢንተርፕራይዞች መደበኛ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ተገለፀ።  ከለላ፣ሰኔ:11/2018ዓ.ምበአብ...
18/06/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ11ወራት ውስጥ ለ290 ነባርና አድስ ኢንተርፕራይዞች መደበኛ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ተገለፀ።
ከለላ፣ሰኔ:11/2018ዓ.ም
በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ የከለላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት ለ290 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በድምሩ ለ762 አንቀሳቃሾች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት መስጠቱን ገለፀ። የኮሌጁ ም/ዲናን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ አወል ሁሴን(ኢ/ር) እንደገለፁት ኮሌጁ ከመደበኛ የትምህርትና ስልጠና ጎንለጎን በከለላ ከተማና በከለላ ወረዳ ለተመሰረቱ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተትፕራይዞች በየሙያ መስኩ ብቁ ባለሙያዎችን በመመደብ ሳይንሳዊና መደበኛ የስራ ላይ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ ይህ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት በዋናነት የኢንተርፕራይዞችን ክፍተት በመለየት ተገቢውን የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ እንድሁም የመርጃና ምክር አገልግሎትና የስራ ላይ ደህንነት ብሎም የካይዘንና ምርታማነት የድጋፍ ማዕቀፎችን ያካተተና ኢንተርፕራይዞች ካሉበት ችግር ሊያላቅቅ በሚችል መልኩ መተግበር መቻሉን ተጠቅሷል።

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ! ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
27/05/2026

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ!

ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

 #ማስታወቂያ የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ መመዘን ለምትፈልጉ በሙሉ
21/05/2026

#ማስታወቂያ
የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ መመዘን ለምትፈልጉ በሙሉ

 #ማስታወቂያ  #ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ
21/05/2026

#ማስታወቂያ
#ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ውጤታማነትን በተበለከተ የዳሰሳ ጥናት አቀረበ​ከለላ (ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም)  የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኢንተርፕራይዞች ላይ ...
07/05/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ውጤታማነትን በተበለከተ የዳሰሳ ጥናት አቀረበ
​ከለላ (ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም)
የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኢንተርፕራይዞች ላይ የሚሰጠው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ያመጣውን ለውጥና ውጤታማነት ተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ዛሬ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ለአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች አቀረበ።
​ኮሌጁ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የቴክኒክና ሙያ ድጋፍ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በኢንተርፕራይዞቹ ዕድገት ላይ የፈጠረውን ተጽዕኖ ለመለየት የሚያስችል ሰፊ የዳሰሳ ጥናት የቀረበ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይም የኮሌጁ
መሪዎች፣ ኢንስትራክተሮችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
-​ጥናቱ በዋናነት ኮሌጁ ባለፉት ጊዜያት ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ሲሰጥ የቆየው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የክህሎት ማሻሻያ እና የማማከር አገልግሎት በኢንተርፕራይዞቹ ምርታማነት ላይ የፈጠረውን ተጨባጭ ለውጥ ለመፈተሽ ያለመ ነው።
​የጥናቱ ዋና ዋና ነጥቦች
​በቀረበው ጥናት ላይ እንደተመለከተው፣ ኮሌጁ የሚያደርገው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ኢንተርፕራይዞች፦
-​የቴክኖሎጂ ሽግግር፡ አዳዲስና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን እንዲለምዱ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል።
-​የምርት ጥራትና ብዛት፡ በሰለጠነ የሰው ኃይል የታገዘ ድጋፍ በመደረጉ የምርቶቻቸውን ጥራትና ብዛት ማሳደግ መቻላቸው ተረጋግጧል።
-​የአሰራር ስርአት፡ የሂሳብ አያያዝ፣ የገበያ ትስስርና የሥራ አካባቢ አደረጃጀትን (5S) በማሻሻል ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
​የአሰልጣኞች ድርሻና የቀጣይ አቅጣጫ
​የጥናት ሰነዱ ከቀረበ በኋላ በአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች መካከል ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በድጋፍ ሂደቱ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ላይም ምክክር ተደርጓል። በተለይም አሰልጣኞች ወደ ኢንተርፕራይዞች በሚወርዱበት ወቅት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የአቅርቦትና የክትትል ክፍተቶች በዝርዝር ተነስተዋል።
-​የኮሌጁ አመራሮች በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና የስራ እድል ፈጠራን ለማገዝ ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ በጥናቱ የተለዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
-በመጨረሻም ​ይህ የዳሰሳ ጥናት ኮሌጁ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ በማጠናከር፣ ብቁና ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር ለሚያደርገው ጉዞ እንደ ትልቅ ግብዓት የሚያገለግል መሆኑ ተመላክቷል።

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ተጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው​(ከለላ፤ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም)​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በማጠናከር የአካ...
04/05/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ተጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው
​(ከለላ፤ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም)
​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን በማጠናከር የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ ነው።
ዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የኮሌጁ አመራሮች፣የከለላ ወረዳና የከለላ ከተማ ስራና ክህሎት አመራሮችና ቡድን መሪዎች እንድሁም ድጋፍ የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የኮሌጁ አሰልጣኞችና ዘርፍ አስተባባሪዎች በተገኙበት በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚገመግም መድረክ ተካሂዷል።
​የኮሌጁ አመራሮች በገለጹት መሰረት፤ ኮሌጁ ከመደበኛው የትምህርትና ስልጠና ስራው ጎን ለጎን ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ በማላመድና ወደ ማህበረሰቡ በማሸጋገር ረገድ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል። ይህም በተለይ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ስራ ለማቃለልና ገቢያቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው።
​የቴክኖሎጂ ሽግግር ዋና ዋና ትኩረቶች፡
​ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ማላመድ፦ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚው ማድረስ።
​የእውቀት ሽግግር፦ ለኢንተርፕራይዞችና ለግለሰቦች ቴክኖሎጂዎቹን እንዴት መጠቀምና መጠገን እንደሚችሉ ተግባራዊ ስልጠና መስጠት።
​ምርታማነትን ማሳደግ፦ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በማስፋፋት የጥራትና የብዛት ምርትን ማረጋገጥ።
​በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተመለከተው፤ ኮሌጁ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት በርካታ ውጤታማ ስራዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በቀጣይም የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
​በመጨረሻም ኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግር የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ያለውን ፋይዳ ለማረጋገጥ ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

 #ከለላ  ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሙያ ብቃት (COC) ተመዛኞች ምዘና መስጠት ጀመረ  ​ከለላ የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 16/08/2018 ዓ.ም በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች በመደበኛም ሆነ በአ...
24/04/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሙያ ብቃት (COC) ተመዛኞች ምዘና መስጠት ጀመረ
​ከለላ

የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 16/08/2018 ዓ.ም በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች በመደበኛም ሆነ በአጫጭር ለሰለጠኑ ሰልጣኞችና በስራ ላይ ያሉ የውጭ ተመዛኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘና መስጠት ጀምሯል።

​ኮሌጁ የሰለጠነና በገበያው ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የሙያ ብቃት ምዘና አንዱ መሆኑ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የተጀመረው ይህ ምዘና በንድፈ-ሐሳብ እና በተግባር የተደገፈ ሲሆን፣ ተመዛኞቹ በቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር የሚያሳዩበት ነው።

​ምዘናው ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የብቃት ማረጋገጫውን የሚያልፉ ተመዛኞች በሚሰማሩበት የሙያ መስክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ራሳቸውን ለመለወጥ ሰፊ እድል የሚያገኙ ይሆናል።

​" #ብቁ ዜጋ ለተሻለ የሀገር ግንባታ!"
የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

 #ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ​[ከለላ - ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም]​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአጠቃላይ ሠራተኞች  ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓ...
24/04/2026

#ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
​[ከለላ - ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም]

​የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

​በመድረኩ ላይ የዘጠኝ ወራቱ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ በተመዘገቡ ውጤቶችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ሪፖርቱን መነሻ በማድረግም ከኮሌጁ ሠራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በኮሌጁ አመራሮች አማካኝነት ዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

​የኮሌጁ አመራሮች በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ እንደገለጹት፤ መድረኩ ተቋማዊ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለይቶ ለማረም ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። በቀሪው የበጀት ዓመት ጊዜያትም​ የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎችንና ውጤታማ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፤
​በግምገማው ወቅት የታዩ ደካማ ጎኖችንና ያልተከናወኑ ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ፤
​ለተቋሙ ዕድገትና ለሰልጣኞች ብቃት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
​በመጨረሻም መላው የኮሌጁ ሠራተኛ ለተቀመጠው ግብ መሳካት በጋራ እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል።

" #ብቁ ዜጋ ለተግባራዊ ክህሎት!"
የከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

Address

Kelela

Opening Hours

Monday 08:00 - 20:30
Tuesday 08:00 - 20:30
Sunday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to ከለላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ - Kelela Polytechnic College:

Shortcuts

Share