18/03/2025
ኢትዮጵያ ዉስጥ ከነገሱ ነገሥታት ከማንም በፊት ከየተኛውም ነጉሠ ነገሥትነኝ ብሎ ከፎከረ ንጉሥ ሁሉ በላይ
ያ ግፍ የወለደው ንፁህ ኢትዮጵያዊ የሐርላ ህዝቦች ቁንጮ
(ገራድ ኢማም አህምድ ኢብራሂም አል ገዓዚ )
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በአሁኑ ሰዓት ፦
ሱማሌ ሪፓብሊል
ኢትዮጵያ ሪፓብሊክ
ጅቡቲ ሪፓብሊክ
ኤርትራ ሪፓብሊክ
ተብሎ የተከፋፈሉትን አገራት እና ከፊል ሱደሰንን
ለ16 ዐሰመታት ቀጥ አድርጎ በፍትህና በርትዕ ገዝቷል ።
ገራድ ኢማም አህመድ ኢብራሂም አልገዓዚ ከሞተ እና የሐርላ ህዝቦች ሥርወ መንግሥት ከተፈረካከሰበት ከ16ኛው ክ/ዘመን ወዲህ የአፍሪካ ቀንድ ከግጭት ጋር የቆረበ የጦርነት ቀጠና ነው ይባለል ።
ይህ ለምን ሊሆን ቻለ?
የሚል ጥያቄ በማንሳት በስፋትና በጥልቀት መተንተን ተገቢ ቢሆንም በተለይ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ አሁን እኛ ያለነበት ትውልድ ድረስ አንደኛው ምናልባትም ቀዳሚው የግጭትና የጦርነት ምንጭ ሴራ፣ ተላላኪነት እና ስግብግብነት ያዋለደው የሀገራት አከላለል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ።
የአፍሪካ ቀንድ በዋናነት ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን፣ ጅቡቲን እና ሶማሊያን የሚያካትት ሲሆን የሀገራት ስፍት በስኩዬር ኪሎሜትር እንደሚከተለው ነው፦
– ኢትዮጵያ ➜ 1,128,571 Sq.km
– ኤርትራ ➜ 121,630 Sq.km
– ጅቡቲ ➜ 23,200 Sq.km
– ሶማሊያ ➜ 637,657 Sq.km
የሦስቱ ሀገራት ስፋት ድምር (782,487 Sq.km) ከኢትዮጵያ አንጻር ሲታይ 63% ነው። ሦስቱም ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ጥገኛ ናቸዉ። በተመሳሳይ የ Worldmeter የመረጃ ቋትን በመጠቀም እስኪ የ 2024 የአራቱን ሀገራት የህዝብ ብዛት እንመልከት፦
– ኢትዮጵያ ➜ 132,059,767
– ኤርትራ ➜ 3,535,603
– ጅቡቲ ➜ 1,168,722
– ሶማሊያ ➜ 19,009,151 ነው።
የሦስቱ ሃገራት ህዝብ ድምር (23,713,476) ከኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር ሲመዘን 18% ገደማ ነው። እንግዲህ ይህ ታላቅ ህዝብና ሀገር ነው ከቀይ ባህር እንዲርቅ የተፈረደበት።
ኤርትራ 2,234 ኪሎሜትር የሚረዝም የቀይ ባህር ጠረፍ ይዛ አዲስ ሀገር ሆና ስትወለድ በታሪክ የቀይ ባህር እመቤት ሆና የኖረችው ኢትዮጵያ ከድንበሯ በ 70 ኪሎሜትር በአነሰ እርቀት የሚገኘው ቀይ ባህር ተዘጋባት።
ኤርትራ ትክክለኛ ሀገር ሳትሆን ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር ለማራቅ በታሪካዊ ጠላታችን በግብፅ እና በስተራቲጂክ አጋሮቿ በምዕራባዊያን አገራት ያለ ኢትዮጵያ ህዝብ ፈቃድ በግፍ የተፈጠረች የጠላቶቻችን የክፋት ፍሬ ውጤት የሆነች ምናባዊ ሀገር ናት። ኤርትራ ሀገር የምትሆነው እናት ኢትዮጵያ በግፍ ያጣችው የቀይ ባህር ጠረፏ በየትኛውም አማራጭ ተመልሶላት የሉዓላዊ ግዛቷ አካል ሆኖ ጸንቶ ሲኖር ብቻ ነው።