Kombolcha Polytechnic College

Kombolcha Polytechnic College Welcome to Kombolcha Polytechnic College's page: A College Striding for Quality Training!

✨መልካም የፋሲካ በዓል!✨
11/04/2026

✨መልካም የፋሲካ በዓል!✨

✨✨ Eid Mubarak ✨✨
19/03/2026

✨✨ Eid Mubarak ✨✨

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተገኝቶ ሱፐርቪዥን አካሄደ......................................በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስተ...
24/02/2026

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተገኝቶ ሱፐርቪዥን አካሄደ......................................

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስተር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራው ከበደ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን የኮምቦልቻ ሪጂዮ ፖሊታን ከተማ ስራና ክህሎት መምሪያና የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት አሰመልክቶ ሱፐርቪዥን አካሂጿል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ ዋናዋና የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽ የሥራ እንቅስቃሴዎችን የዳሰሰ ሲሆን ኮሌጁ ራሱን ለማዘመን በዲጂታላይዜሽ መስክ የሚያደርገውን ተሃድሶ፣ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጆት እየሰጠ ያለዉን አገልግሎትና ከሌሎች የኮሊደር ልማት ስራዎች አንፃር እየሠራ ያለውን የለውጥ ሥራዎች አይቷል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በሥልጠና ዘርፎች ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ፣ በአውቶሞቲቭ ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን በዓለም ባንክ የገንዝብ ድጋፍ ፕሮጀክት እያስገነባ ያለውን የማስልጠኛ ወርክሾፕ፣ የቢሮና ሌሎች የገቢ ማስገኛ ማዕከላት ግንባታ፤ እንድሁም በኮሌጁ ውስጥ እየተከናወነ ያለዉን የኮሊደር ልማት እንቅስቃሴ አድንቋል::

የካቲት 2018
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮለጅ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ የካቲት 16/2018 ዓ.ም. የስልጣኞች መማክርት የተወካዮች አባላትን በኮሌጅ ም/ዲንና ትም / ስልጠና  ቡድን ቢሮ ከኮሌጅ የሙያ ድጋፍና አማካሪ ተጠሪና አባ...
23/02/2026

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ የካቲት 16/2018 ዓ.ም. የስልጣኞች መማክርት የተወካዮች አባላትን በኮሌጅ ም/ዲንና ትም / ስልጠና ቡድን ቢሮ ከኮሌጅ የሙያ ድጋፍና አማካሪ ተጠሪና አባላት በተገኙበት የ 2018 ዓ.ም አንደኛ የስልጠና ዘመን ከስልጠና ጥራት፤ ከትብብር ስልጠና፤ ከተቋም ውስጥ ምዘና፣ የትግባር፣ የዕወቅት እና አመላካከት ስልጠና፤ digital ክህሎት እና በሌሎች የኮሌጅ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በጥንካሬ፤ በክፍተት እና ወደፊት በተሻለ ለመስራት በሚያስችሉ ሃሳቦች ላይ በኮሌጁ ም/ ዲን በአቶ ሰለምን ነጋሽ መሪነት ውይይት ተደርጓል፡፡ በወ/ሮ ተናኘወርቅ ወ/ሃና የሙያ አማካሪ እና በአቶ ወርቅዬ ሃይሌ የተመራቂዎች ዳሰሳ ጥናት ባለሙያ በኩል ውይይቱ ተካሒዷል። የሰልጣችም ተወካዮች በውይይቱ ጥሩ ተሳትፎ አድርገዋል።

የኮሌጁ ሠራተኞች የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት አፈፃፀማቸውን ገመገሙ ***********************የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የ2018 በጀ...
11/02/2026

የኮሌጁ ሠራተኞች የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት አፈፃፀማቸውን ገመገሙ
***********************
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀማቸውን ገመገሙ። የኮሌጁ እቅድና በጀት ክትትል ባለሙያ አቶ ስለምን በልሁ ከጠንካራና ክፍተት ከታየባቸው አፈፃፀሞች አንፃር ሪፖርቱን ለተሳታፊዎች በአጭሩ አቅርበዋል።

በጠንካራ አፈፃፀም ከቀረቡት ውስጥ
ሁሉም የስልጠና ዘርፎች የአጫጭር ስልጠና በመሰጠት ተሳታፊ መሆናቸው፣ ለአጫጭር ስልጠና ተመልምለው የመጡ ሰልጣኞች ተገቢዉን ስልጠና ማግኘታቸው፣ በቤት አያያዝ ስልጠና 100% መሳካቱ፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ለመስጠት ለተመደቡ ኣሰልጣኞች ግንዛቤ ስልጣና መሰጠቱ፣ የካይዘንና የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ያለማቋቋረጥ ማስቀጠል የሚያስችል አሠራር እየተፈጠረ መሆኑ፣ በሁሉም ዘርፎች የመረጃና የማስልጠኛ ማቴሪያሎችን አደራጅተዉ መያዝ መቻላቸው ተጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ የቴክኒካል ምዘና ውጤት አነስተኛ መሆን፣ የቤት አያያዝ ስልጠና የሚሰጡ አሰልጣኞች እጥረት መኖሩ፣
በተለያዩ መንገዶች የአዲስ ገቢ ስልጣኞች ቅስቀሳ ቢደረግም የተመዘገቡት ሰልጣኞች ከተያዘው እቅድ በጣም ያነሰ መሆኑ፡ ለአጫጭር ስልጠና የማስተማሪያ ክፍል እጥረት መኖሩ፣ የማስልጠኛና የምዘና ጥሬ እቃ ችግር የመሳሰለሉት በአፈፃፀም ወቅት ያላደማናቸው ተግዳሮቶች ናቸው ሲሉ የእቅድና በጀት ክትትል ባለሙያው አቶ ሰላሞን አንስተዋል።

ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎና አሰተያየቶች የኮሌጁ ዲኖች መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የሥራ አፈፃፀም ውጤት አሞላልን (BSC) አሰመልክቶ መበኛ የማሰልጠን ሥራ በሌላቸው መምህራን "ቀደም ሲል የምንገመገምበት መደበኛ ስልጠና እየሰጠን በነበረበት ጊዜ የተዘጋጀውን መስፈት አሁን በመደበኛ ስልጠና የምናስለጥነው ተማሪ ሳይኖርን በዚያው መስፈርት እንዲንገመገም መደረጉ በደመወዝ እድገትና ጥቅማ ጥቅም ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ ለቀረበው አስተያየት የኮሌጁ ዲን አቶ ኤርሚያስ ጌትነት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

በኮለጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን (የካቲት 3/2018)

የኮሌጁ የመረዳጃ ማህበር የሥራ ዘመን  ሪፖርት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የአድስ የሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ***********************የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአሰልጣኝ ...
11/02/2026

የኮሌጁ የመረዳጃ ማህበር የሥራ ዘመን ሪፖርት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የአድስ የሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ
***********************

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአሰልጣኝ መምህራንና ሠራተኞች መረዳጃ ማህበር ከተቋቋመ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ዛሬ የማህበሩ ሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴዎች በሥራ ዘመን ቆይታቸው ያከናወኗቸውን ተግባራት አጪር ሪፖርት ለመላ አባሉ አቅርበዋል።

የማህበሩ ሰብሳቢ አሰልጣኝ መምህር ተስፋዬ ኃይለማሪያም እንደተናገሩት ማህበሩ 212 አባላት ያሉት ሲሆን ባሳለፍናቸው ሁለት ዓመታት ያጋጠሙንን የደስታም ሆኑ የሀዘን ጊዜያት የማህበሩ አባላት የሰጣችሁንን ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት ስንወጣ ቆይተናል ብለዋል።

ሰፊ አባላትን ያቀፈ ማህበር ለመምራት ቅንነትንና ፈቃደኝነትን የሚጠይቅ ከባድ የሥራ ኋላፊነት መሆኑን ጠቅስው ማህበሩ በሥራ ዘመኑ በርካታ ስኬታማ የሆኑ ተግባራትን ያካናወነ ቢሆንም በኛ በኩል በሚያጋጥም የሥራ መደራረብና በአባላቱ ዘንድም በሚስተዋለው የመረጃ ቅብብሎሽ ችግር ምክንያት ማን እንደወለደ፣ ማን ሀዘንና ህመም እንደገጠመው ወቅታዊ መረጃ ባለማግኘት ከሁነቱ ተዘግይቶ ለተጠየቁ አባላት በማህበሩ ስም ይቅርታ ጠይቀው ማንኛውም ሰው የደስታና የመርዶ ቀናቶች የሚያልፍ በመሆኑ እርስበርስ መቀራረብ፣ መደጋገፍና መጠያቅ ይገባል፡፡ የታመመን መጠየቅ፣ ያዘነን ማስተዛዘን፣ ማፅናናት ልምድ ልናደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው በማለት የማህበሩ ሰብሳቢ አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማህበሩ ለሰርግ፣ ለሞት፣ ለመርዶ፣ ለልደት፣ ወዘተ. ለመሳሰሉ የማህበራዊ ክስተቶች ያወጣውን ወጪ አጭር ሪፖርት በማህበሩ ሰብሳቢ አሰልጣኝ መምህር ተስፋዬ ኃይለማርያም ከቀረበ በኋላ ውይይት ተካሂዶበታል። የገቢና ውጭ ሂሳቡ በልፅ ተዘርዝሮ ማጠቃለያ እንዲሠራ አሰተያዬት ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የማህበሩ የሥራ ዘመን በመጠናቀቁ አዲስ የሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተካሂዷል። በዚህም መሰረት 1) አሰልጣኝ ሁነኛው ዘላለም (ሰብሳቢ) 2) አሰልጣኝ እየብ አራጌ (ም/ ሰብሳቢ) 3) ወ/ሮ ንግስት ገ/ኪዳን 4) ተስፋዬ ኃ/ማርያም
5) አሰልጣኝ ሰብለ ጣሹ የማህበሩ ኣባላት ሆነው በአብላጫ ድምፅ ተመርጠዋል።

በኮለጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን (የካቲት 3/2018)

በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ ላይ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ************************"አድሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስ...
11/02/2026

በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ ላይ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
************************

"አድሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ ከተደራሽነት ይልቅ በጥራት ላይ ትኩረት የሚሰጥ ስትራቴጂ ነው!" ወ/ሮ ጦይባ አህመዲ መድ፦ ምክትል ዲንና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎኖሎጂ ሽግግር ቡድን ቡድን መሪ

ቀደም ሲል በ 2000 የወጣው ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆነውንና እያደገ የመጣውን የዲጅታላይዜሽን ዓለም፤ ሀገራዊ ለውጥ እንድሁም የሥራ ገበያውን ዳይናሚዝም ከግምት በማስገባት በርካታ ማሻሻያዎችን አካቶ በ2017 በአዲስ መልክ ወጥቷል።

በመሆኑም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በባለቤትነት ተሰማርቶ እየሠራ ያለዉን የሰዉ ኃይል ለውጡ ያካተታቸውን አዳዲስ ቁም ነገሮች ማሳወቅና ግንዛቤ መፍጠር አሰፈላጊ በመሆኑ የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የአንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ ወ/ሮ ጦይባ አህመድ ለኮሌጁ ሠራተኞች በስትራቴጂው ላይ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

"አድሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ ከተደራሽነት ይልቅ በጥራት ላይ ትኩረት የሚሰጥ ስትራቴጂ" መሆኑን ወ/ሮ ጦይባ ገልፀው በቀድሞውና በአዲሱ ስትራቴጂ መካከል ያሉትን ስትራቴጂያዊ ለውጦች፣ ልዩነቶችና ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎች ግንዛቤ ፈጥረዋል።

በኮለጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን (የካቲት 3/2018)

29/01/2026

በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የመምሪያና የፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለዉ ስልጠና ቀጥሏል!
***

በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሦስተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የምስራቃ አማራ የመምሪያ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ዲኖች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በሰው ኃይል ስነ-ምግባርና በተሻሻሉ የመምህራን ዝውውር መመሪያ ላይ የስልጠናና የውይይት መድረክ በጥሩ ሁኔታ ቀጥሎ ውሏዋል።

በትናንትናው አለት በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ላይ የተሰጠውን ስልጠና አሰመልክቶ ሠልጣኞች በተግባራዊ አሠራር እያዩ የበለጠ እንድገነዘቡት ለማስቻል የበጀትና ፋይናንስ ባለሙያዎች በኮምፒዩተር የላብራቶሪ ክፍል ልምምድ አድርገዋል።

የአሰልጣኞች /መምህራንና ሠራተኞች ዝውውርና ምደባ ከሚፈፀምባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ አገልግሎት፣ ጋብቻ፣ የሹመት፧ የህግ ከለላ፣ የደህንነት ስጋት፣ የአካል ጉዳትና የጤና እክል መሆናቸው በስልጠናው ላይ ተጠቅሰዋል።

ዝውውርና ምደባ ከመሠራቱ ጋር ተያይዞ የትምህርት ማስረጃ ማጣራትና የስነ ምግባር ጉድለት ችላ የማይባሉና በትኩረት የሚታዩ ጉዳዮች መሆናቸውን የአማራ ክልል ሥራ ና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኋላፊ ክቡር አቶ አማረ አለሙ ተናግረዋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አያይዘው እንዳሉት በዝውውርና ምደባ አሠራር ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄና ቀድሞ የማጣራት ሥራ ካልተሠራ የማይገባው ሰው ያልተገባው ቦታ ላይ ይመደባል ካሉ በኋላ የቴክኒክና ሙያ ተቋሞቻችን /ኮሌጆቻችን በስነ ምግባራቸውና በሙያ ብቃታቸው አንቱ የተባሉ አሰልጣኞች መሰባሰቢያ ሲሆኑ ዘርፉ የሰልጣኞች ቁጥር አንድ .ምርጫ እየሆነ ይመጣል ብለዋል።

በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን
ጥር 21/2018

በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የመምሪያዎች፤ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ዲኖች፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው!..................................................
27/01/2026

በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የመምሪያዎች፤ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ዲኖች፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው!....................................................................................

"በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የተሰማሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የዘርፉ ምሰሶዎች በመሆናቸው በየጊዜው በአዳዲስ መመሪያዎችና አሠራሮች ላይ ጥልቅና የጠራ ግንዛቤ እንድኖራቸው ማስቻል ለተሻለ ውጤት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል!" ዶ/ር ስቡዕ ገበያው:- የእማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት (አብክመ) ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ዲኖች፣ የሰው ኃይል አስተዳደርና የውስጥ ኦዲት ቡድን መሪዎችና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በአዳድስ መመሪያዎችና አሠራሮች ላይ በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና እየሰጠ ነው::

የክልሉ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ዶ/ር ስቡዕ ገበያው በስልጠና መርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት "በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የተሰማሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የዘርፉ ምሰሶዎች በመሆናቸው በየጊዜው በአዳዲስ መመሪያዎችና አሠራሮች ላይ ጥልቅና የጠራ ግንዛቤ እንድኖራቸው ማስቻል የድጋፍ ስጭ አመራሩ የዘርፉን እሳቤዎችና የአሠራር ለውጦች ተግንዝበው ተግባሮቻቸውን መፈፀም ያስችላል ብለዋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ስቡዕ ገበያው አያይዘው እንደ ተናገሩት የትምህርትና ስልጠና፧ የሥራ እድል ፈጠራ እንድሁም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባሮቻችን ውጤታማ የሚሆኑት በአስተሳሰቡ የተቃኘና የአሠራር ስርዓቱ የሚመራው ሠራተኛ መፍጠር ሲቻል መሆኑን የደቡብ ኮርያን ተሞክሮ በማንሳት ሲቪል ሰርቫንቱ በራሱ አውቆ መሥራትና ግዴታውን መወጣት የሚያስችል እንደ ባህል የፀና ጠንካራ የአሠራር ስርዓት (system) መፈጠር አለበት ብለዋል።

በተገኘው የክልላችን አንፃራዊ የሠላም ሁኔታ የቢሮው ኮር አመራሮች በየደረጃው ከሚገኙ የተቋማትና ኮሌጅ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በመገናኘት መሥራት አሰፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ስቡዕ አሳስበዋል።

ስልጠናው ለሚቀጥሉት አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር፣ በውስጥ አዲት አሠራር፣ በሰው ኃይል ስምሪት ስነ ምግባርና በተመረጡ የህዝብ ግንኙነት ተግባራት ላይ ያተኮራል።

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን
ጥር 19/2018

በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአሰልጣኞች የሚሰሩ የድርጊታዊ ጥናትና ምርምርንድፈ ሀሳብ /action research proposal/ ግምገማ ተካሄደኮምቦልቻ 04/05/2018*************...
16/01/2026

በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአሰልጣኞች የሚሰሩ የድርጊታዊ ጥናትና ምርምርንድፈ ሀሳብ /action research proposal/ ግምገማ ተካሄደ
ኮምቦልቻ 04/05/2018
*************************************************
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመንግስት ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከለል በማህበረሰብ ብሎም በኮሌጁ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ጥናትና ምርምር በማድረግ ችግሮችን መፍታት አንዱ ተግባር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የኮሌጁ አስልጣኞች በሚያሰለጥኑበት ወቅት እና ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕረይዞች ድጋፍ ቢያደርጉበት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን መሰረት በማድረግ በተሰሩ የድርጊታዊ ጥናትና ምርምር ንድፈ ሀሳብ /Action research proposal/ ለዳኞች እና ለኮሌጁ ማህበረሰብ ቀርበው አስተያየት ተሰቶባቸዋል፡፡
በኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጅ ሽግግር የስራ ሂደት የኢንኩቤሽን ማዕከል አካል የሆነው የጥናትና ምርምር ስራ በ 2018 ዓ.ም የስራ ዘመን ለሚሰሩ ድርጊታዊ ጥናትና ምርምር ስድስት የተለያዩ ርእስ ያያዙ ንድፈ ሀሳቦች/Proposal/ ቀርበው በዳኞችና በተሳታፊ የኮሌጁ ማህበረሰብ ሀሳብ ተሰቶበት ሶስት ድርጊታዊ ጥናትና ምርምሮች የተመረጡ ሲሆን አቅራቢዎችም በዳኞች የተሰጡትን አስተያየቶች በማካተት በአስቸኳይ ወደ ስራ እንደሚገቡ እና ዳኞችም አስፈላገውን ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው ሃሳብ ሰተዋቸዋል፡፡

በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሳታላይት ማዕከል ለኮሌጁ ማኑፍክቸሪንግ አሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ                                              ...
26/12/2025

በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሳታላይት ማዕከል ለኮሌጁ ማኑፍክቸሪንግ አሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ *************************************************
15 ለሚሆኑ የኮምቦልቻ ፖቴክኒክ ማኑፋክቸሪንግ አሰልጣኝ መምህራን ለ14 ቀን የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደጀመሩ የሳታላይት አስተባባሪው አቶ ምትኩ ተሻገር ገለፁ፡፡ ስልጠናወ የሚሰጥባቸው ዕርዕሶች
✅ Solidwork(CAM/CAD)
✅ CNC Milling
የሳተላይቱ አስተባበሪ እንደገለፁት ሳተላይት ማዕከላት በአካበባው ያሉ ቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በቅርበት መደገፍ ዋና ተግባራቸው ስለሆነ በቀጣይም የክላተር ኮሌጆችን የክህሎት ክፍተት በመለየት ስልጠናዎችን አጠናክረው እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

Address

Kombolcha
Kombolcha

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251335512510

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kombolcha Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Kombolcha Polytechnic College:

Share