Adis መረጃ

Adis መረጃ we send to new information with you

በመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት የእሳት አደጋ አጋጠመ !!አዲስ አበባ አያት በሚገኘው የመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት ዛሬ ከ9:00 በኋላ የእሳ...
19/10/2024

በመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት የእሳት አደጋ አጋጠመ !!

አዲስ አበባ አያት በሚገኘው የመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት ዛሬ ከ9:00 በኋላ የእሳት አደጋ ማጋጠሙን የደረሱኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

አዲስ በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው ህንፃ ስር ተነስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ስላደረሰው የጉዳት መጠን የተገለፀ ነገር የለም።
እሳቱ ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀ ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉንለማወቅ ይችሏል ።

የያህያ ሲንዋር መገደል የጦርነቱ ፍጻሜ አይደለም-  ጠ/ሚ ኔታንያሁአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል የሃማስ መሪ የነበሩትን ያህያ ሲንዋርን ጋዛ ውስጥ መግደሏን አረጋ...
18/10/2024

የያህያ ሲንዋር መገደል የጦርነቱ ፍጻሜ አይደለም- ጠ/ሚ ኔታንያሁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል የሃማስ መሪ የነበሩትን ያህያ ሲንዋርን ጋዛ ውስጥ መግደሏን አረጋግጣለች፡፡

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ÷ የያህያ ሲንዋር መገደል ከፍተኛ ድል ቢሆንም የጦርነቱ ፍጻሜ እንዳልሆነ አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በሀማስ እገታ ሥር የሚገኙ እስራኤላውያን እስከሚለቀቁ ድረስ ጦርነቱ ይቀጥላል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በርካታ እስራኤላውያን እንዲገደሉ እና እንዲታገቱ በተደረገበት የጥቅምት 7 ጥቃት የያህያ ሲንዋር ሚና ከፍተኛ እንደነበር አንስተው÷ የመሪው መገደል በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ሊቀይረው እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የያህያ ሲንዋር መገደል ለእስራኤል ብሎም ለአሜሪካ ትልቅ ድል መሆኑን ገልጸው÷ የመሪው መገደል ምን አልባትም ጦርነቱ በአጭር ጊዜ እንዲቋጭ ሊያደርገው ይችላል ብለዋል፡፡

በአንጻሩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢራን ልዩ መልዕክተኛ በበኩላቸው÷ የያህያ ሲንዋር መገደል እስራኤልን ከምን ጊዜውም በላይ ለመፋለም የሚያነሳሳ የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጠናል ብለዋል፡፡

ሁኔታው ጦርነቱን ከማብረድ ይልቅ ሊያባብሰው እንደሚችልም ነው ያስረዱት፡፡

የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል እስራኤል ገለጸችየእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጋዛ ውስጥ ባደረገው ኦፕሬሽን አዲሱ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል እያጣ...
17/10/2024

የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል እስራኤል ገለጸች

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጋዛ ውስጥ ባደረገው ኦፕሬሽን አዲሱ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት እና የደህንነት ኤጀንሲ በጋራ ባወጡት መግለጫ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጋዛ ውስጥ ባደረገው ኦፕሬሽን ሦስት የሐማስ ቁልፍ አመራሮች ተገድለዋል።

ከተገደሉት መሪዎች ውስጥም አንዱ ያህያ ሲንዋር ሊሆን እንደሚችል በመግለጫው ተጠቁሟል።

ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው የጥቅምት 7 ጥቃት ዋነኛ መሪ የነበረው ያህያ ሲንዋር እስራኤል ልትገድላቸው ከምትፈልጋቸው ሰዎች መካከል በግምባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው።

የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ የ56 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት በኢትጵያ የምግብ ዋስትናን ጨምሮ ለተለ...
17/10/2024

የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ የ56 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት በኢትጵያ የምግብ ዋስትናን ጨምሮ ለተለያዩ ዘርፎች የሚውል የ56 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ድጋፉ ይፋ የተደረገው የኢትዮ-ጀርመን የልማት ትብብር መድረክ በአዲሰ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ÷ ኢትዮጵያ ያደረገችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመተግበር የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ማሻሻያዎችን በማድረግ በቁርጠኝነት እየተገበረች መሆኗን አስገንዝበው÷ ማሻሻያዎቹን በመተግበር ረገድ እንደ ጀርመን ያሉ አጋር ሀገራት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሃንፊልድ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያና ጀርመን ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው÷ የልማት ትብብር መድረኩ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል፡፡

በጀርመን ኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ዲቪዥን ኃላፊ ማርከስ ቮን ኤሴን÷ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ላይ ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ መጨረሻም የጀርመን መንግስት ለምግብ ዋስትና፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ፣ ለትምህርት እና ለመሬት አስተዳደር ማጠናከሪያ የሚውል የ56 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ጆን ዳንኤል ላይ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የዋስትና ብይን አጸናአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአውሮፕላን አንወርድም ...
17/10/2024

ጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ጆን ዳንኤል ላይ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የዋስትና ብይን አጸና

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአውሮፕላን አንወርድም በማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው የተከሰሱት ስድስት ግለሰቦች ላይ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገባቸውን የዋስትና ጥያቄን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አፀና።

ከ15 ቀናት በፊት በስር ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ የተባሉ ተከሳሾች ግን በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር።

ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የይግባኝ ባዮችን አቤቱታን እና የከሳሽ ዐቃቤ ሕግ መልስ፣ የግራ ቀኝ ክርክርን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ከህግ አንጻር ተገቢ ነው በማለት ብይኑን በማጽናቱ ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ይከታተላሉ።

በታሪክ አዱኛ

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ የኩባንያውን ተወዳዳሪነት ከማሻሻል ባሻገር በርካታ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ቦታ ሆነው በሀገራቸው ኢንቨስት እንዲያደርጉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው።
17/10/2024

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ የኩባንያውን ተወዳዳሪነት ከማሻሻል ባሻገር በርካታ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ቦታ ሆነው በሀገራቸው ኢንቨስት እንዲያደርጉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው።

17/10/2024

በአዲስ አበባ ለሦሥተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ትናንት ምሽት ተሰማ
********************************
በአዲስ አበባ ለሦሥተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ትናንት ምሽት ተሰምቷል፡፡

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

ትናተት ምሽት 5፡11 ደቂቃ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

በአካባቢው ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴው አሁንም እንዳልቆመ ዶክተር ኤሊያስ ተናግረዋል።

07/02/2024

NEW CAR SALES

Address

Laftu

Telephone

+251930776522

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adis መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share