16/08/2021
የታሊባን ወርቃማውን ድል .... አለመናገር እንዴት ይቻላል ??
* በፓሽቱኖች ቋንቋ ታሊባን (ጣሊባን) ማለት "ተማሪ" የሚል ትርጉም ሲኖረው.....በ1970ዎቹ በኢስላማዊ በትምህርት (መድረሳ) ቤቶች በተማሪዎች እንደተመሰረተ ይገመታል.....
* ታሊባን የተመሰረተው በዋነኝነት የነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ሱናና አስተምህሮትን ከፍ ለማድረግና ሸሪዓን የሚያውቅና በሸሪዓ የሚተዳደር ትውልድ ለመፈጠር አልሞ የተነሳ ጀመዓ ነበር፡፡
* ከኢራን የሺዓ አብዮት ፍንዳታ በኃላ የሺዓ የበላይነት በቀጠናው እንዳይመጣ ሳዑዲ አረቢያ ለታሊባን በትንሹ ድጋፍ ማድረግ ጀመረች፡፡
* በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ብዙ አለምአቀፍ አባላትን በመመልመል ትግል ማድረግ የጀመረው ታሊባን ከሶቪየት ህብረት ወረራ በኃላ አፍጋኒስታንን በአሜሪካን እጅ ሲያስተዳድር የነበረውን ሶሻሊስት ፓርቲን ጥለው በ1995 የአፍጋኒስታን መሪ ሆኑ፡፡
* የመጀመሪያው የታሊባን መሪ የነበሩት ሙላ መሀመድ ኦማር ሲሆኑ ... አብዱል ጋህኒ በርዳ...አክታር መንሱር....ሂበቱላህ አኩንዳዝ.....ሙሀመድ ራሱል ...ታሊባንን በተለያየ ጊዜ ውስጥ መርተውታል፡፡
* አሜሪካን አፍጋኒስታንን ከወረረች ጀምሮ እጅግ ብዙ ኦፕሬሽኖችን ብታደርግም አንድም ቀን የአፍጋኒስታን ሙጃሂዶችን አሸንፋ አታውቅም።
* የኦሳማ ቢን ላደን የቅርብ ጎደኛና የታሊባን የመጀመሪያ መሪ የነበሩት ሙላ መሀመድ ኦማር በአንድ ወቅት ይሄንን ተናግረው ነበር....!!!
" አሜሪካ እኮ የሙስሊሙን ሀገራት መንግስታት የምታሽከረክር ኃይል ናት፡፡ ህዝቡ እስልምናን እንከተል ይላል መንግስታቱ ግን በአሜሪካ ሳንባ የሚተነፍሱ በመሆናቸው ጥያቄውን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ይታወቃሉ፡፡ አንድ ሰው እንኳን ፅድቁን የእስልምና መንገድ ቢከተል መንግሥት ያስረዋል፡፡ ከዚያ አሰቃይቶ ይገድለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ የአሜሪካን ስራ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ አሜሪካ እነዚህን መንግስታት መርዳቷን ብታቆም ኖሮ ይሄንን ሁሉ መከራ ህዝባችን ባላየ ነበር፡፡" ብለዋል፡፡
* የአፍጋኒስታንን ተራራማና ተፈጥሮአዊ መልከአ ምድርን እየተጠቀሙ ከዘመኑ አንፃር ኃላ ቀር የሆነ ትጥቅ ታጥቀው ከአሜሪካንና ከአውሮፓውያን ጋር ብዙ ውግያዎችን አድርገዋል... አስገራሚው ነገር በአንድ ውጊያ እንኳን ታሊባኖች ተሸንፈው አያውቁም።
* ከዚህ በላይ በጦርነት መስዕዋትነት መክፈል ያልፈለገችው አሜሪካን በመጨረሻም ከታሊባን ጋር ያላትን ጉዳይ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈታ ፍላጎት አሳየች ድርድርም ማድረግ ጀመረች።
* በኳታር ዶሀ የተደረገው የሁለቱ ድርድር ፍሬ አፍርቶ ከወራቶች በፊት አሜሪካን አፍጋኒስታንን ለቃ ለመውጣት ተስማምታ ወታደሮቾቿን ከአፍጋኒስታን ማስወጣት ጀመረች።
* በዚህም የታሊባን ሙጃሂዶች ጠንካራ ወታደራዊ ዘመቻዎችን በማድረግ የአፍጋን ከተማዎችን መቆጣጠር ጀመሩ።
* በአጭር ጊዜ ውስጥም ሙሉ በሙሉ አፍጋኒታንን ለመቆጣጠር ተቃርበዋል። በዛሬው እለትም ሀገሪቱን ሲመሩ የነበሩት ፕሬዝዳንት አሽረፍ ገኒ በዋናው ከተማ ካቡል የሚገኘውን ቤተመንግሥቱን ለቀው ሸሽተው ወጥተዋል።
* በተመሳሳይም የአሜሪካን ኤምባሲ ሰራተኞችም ሆኑ ወታደሮች በአሁኑ ሰአት አፍጋኒስታንን ለቀው እየወጡ ነው።
* ካቡልን ከበው የሚገኙት የታሊባን ሙጃሂዶች በቅርብ ሰአታት ውስጥም ቤተመንግሥቱን ተቆጣጥረው ሀገሪቷን መምራት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
* በኢስላምና በሀገራችው ጉዳይ ከ20 አመታትን በላይ ትልቅ መስዕዋትነትና ትግል አድርገው ሀገራቸውን ነፃ አውጥተዋል። ጀግናዎቹን የአፍጋኒስታን ሙጃሂዶች አለማድነቅ አይቻልም። 👏👏
የፅናት ተምሳሌቶች ታሊባን