Semara University Librarian

Semara University Librarian ለመታየት አትስራ ! ሰርተህ አሳይ !!

05/06/2026
 የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ተብሏል።የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ...
03/06/2026



የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ተብሏል።

የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል ነው።

በመሆኑም ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች የብሔራዊ መታወቂያ FAN ቁጥርዎን በመጠቀምና የግል መረጃ በማማሟላት የራሳችሁን መለያ ማረጋገጫ ማጠናቀቅ ይጠበቅባችኋል።

https://verify.ethernet.edu.et/ ከተጫኑ በኋላ Exit Examination የሚለውን ይጫኑ፣ Continue Verification የሚለውን በመጫንና የሚያስፈልገውን በመሙላት ያረጋግጡ።

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

27/03/2026
 የፈተና ቀኖቹ ላይ ማስተካከያ ተደረገ።አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ሙሉ ቀን በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት የሚ...
26/02/2026



የፈተና ቀኖቹ ላይ ማስተካከያ ተደረገ።

አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ሙሉ ቀን በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።

አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት የሚሰጠው ፈተና ከጁምዓ ሶላት ስግደት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ቅዳሜ በሚሰጡ ፈተናዎች ላይ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በኩል ቅሬታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስተካከያ ማድረጉ ታውቋል።

በዚህም አርብ በሁለተኛ ክፍለ-ጊዜ (ከ5:00-7:30) ፈተናዎች ላይ ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ፈተናው የማይሰጥ ይሆናል።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተስተካከለውን መርሐግብር (ከላይ ተያይዟል) ለተፈታኝ ተማሪዎቻቸው በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።

Via

 !የ2018ዓ.ም የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች በሙሉ! የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የካቲት 17/2018 ዓ/ም መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ያልታ...
24/02/2026

!
የ2018ዓ.ም የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች በሙሉ!
የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የካቲት 17/2018 ዓ/ም መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ያልታሰበ የኃይል መቆራረጥ ችግር በዳታ ማዕከል ላይ በማጋጠሙ ችግሩን በመፍታት እንደገና ለማስጀመር ጥረት የተደረገ ቢሆንም የፕሮግራም መዛባትን በማስከተሉ የፈተናውን ሙሉ ፕሮግራም በአንድ ቀን ማሸጋሸግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ስለሆነም ሁሉም ፕሮግራሞች የዛሬን ጨምሮ ባሉበት ክፍለ ጊዜ ላይ ሆነው በተዋረድ በአንድ ቀን የተሸጋሸጉ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም ተፈታኞች መረጃው እንዲደርሳቸው እንዲደረግ እያሳሰብን ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

ማስተወሻ፡- ዛሬ ፈተና ጀምረው የነበሩ ተፈታኞች ነገ በተመሳሳይ ሰዓት እንደገና የሚፈተኑ ይሆናል።
ምንጭ:- የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት!

18/02/2026

#ማስታወቂያ

በመውጫ ፈተና ወቅት ከተፈታኞች የሚጠበቁ ነገሮች፤

1. ተፈታኝ ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የሞባይል ስልክ፣ ሚሞሪ ያለው የእጅ ሠዓት፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር፣ የተጭበረበሩ ሰነዶችና የራስ ያልሆነ መታወቂያ ይዞ መገኘት የለባቸዉም፡፡

2. ተፈታኝ ተማሪዎች ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል፡፡

3. ተፈታኞች ከ3ዐ ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት ክፍል መገኘት አለባቸው፡፡ አላስፈላጊ ውዝግብ መፍጠር የለባቸውም፡፡

4. ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አስፈፃሚን ትዕዛዝ ማክበር አለባቸው።

5. ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነው፡፡ እንዲሁም ራሳቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝና ለሚጠይቃችሁ ፈተና አስፈፅሚ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. በፈተና ወቅት የፈተና መልስ ለሌላ ተፈታኝ መስጠት ወይም ማሳየት ወይም ማስኮረጅ አይቻልም፡፡

7. በሌላ ስም፣ መለያ ቁጥር (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) መፈተን አይቻልም፡፡

ከላይ የተዘረዘሩተን እና ሌሎች የፈተና ስርዓቶችን የጣሰ ውጤቱ ተሰርዞ በዲሲፕሊን ጥሰት ይጠየቃል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።ፈተናው አንድ ሳምንት ብቻ የቀረው ሲሆን፤ አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎ...
18/02/2026

የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

ፈተናው አንድ ሳምንት ብቻ የቀረው ሲሆን፤ አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና መለማመጃ (Mock Exam) በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዕጩ ተፈታኞች የፈተናው የይለፍ ካርድ እና ፋይዳ መታወቂያ ማዘጋጀታችሁን እንዳትዘነጉ፡፡

Address

Logya

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Semara University Librarian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Semara University Librarian:

Shortcuts

Share