Mattu University

Mattu University Education

We Are Dedicated to Serve the Community

Background
Mattu University is one of Ethiopian Public Universities established in Oromia Region in Ever Green Environment

Beeksisa
30/04/2026

Beeksisa

29/04/2026
29/04/2026

ለአዳዲሶቹ ዋና አድናቂዎቼ ታላቅ ምስጋና! Ansaar Yoseef, Bultu Toli, ILuukoo, Halake Mbm Skb, Barkot Barkuat, Asraru Dawud, Duop Gatluak, Tajudin Mamude, Anesoo Oromoo, Mulataa Rafise, Wondifraw G. Silassie, Samy MT, Biyya Makkobil, Mahammed Abdi, Abreham Alemu, Alex Kanyesus, Ketbek Mosses Lual, John Mitiku, Yohanis Alemu, Yohannes Ayele, Margat Alemu, Chuol W Kong, Diriba Fikadu Gamta, Degefa Fikadu DF, Abdi Shemsu, Zikru Eshetu, Keno Mulugeta, Burka Gelana, Ayantu Tafese, Zerihun Zeleke Nosso, Cheruu Mar, Alemayehu Abera, Nazif Amza, Wakgari Dejene Tasisa, Worku Bedada Waktola, Oumer Kassaw, Bizualem Olb, Begashaw Taye, Diggaa Saaqo, Adisu Tefera, Chane Legesse, Lemlem Wendimu Abs, Tamirat Tadele Bekele, Mc Marco Chuol, Wondu Meb Adeba, Chuol Guek Gach, Top Wechjock Luak, Addisu Melaku, Temam Bediru, Dame Tol Jeb

29/04/2026
28/04/2026
ለመቱ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ።    ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (ህዓአግ)      ============+=========="የከፍተኛ አመራሩ አርአያነት ለፀረ-ሙስና ትግል ያለዉ ፋይዳ...
28/04/2026

ለመቱ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ።

ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (ህዓአግ)
============+==========
"የከፍተኛ አመራሩ አርአያነት ለፀረ-ሙስና ትግል ያለዉ ፋይዳ!" በሚል ርዕስ ለአመራሮች ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የመቱ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት መ/ር ሳቢት ዜይኑ በንግግራቸው የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከሚሰራቸው ዋና ዋና ስራዎች አንዱ አመራሮች እና ሰራተኞች በህጎች፣ አዋጆች፣ መመርያዎች እና አሰራሮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖሯቸው ቀጣይነት ያለው ስልጠና ማመቻቸት መሆኑን ገልጸው ይህኛው ስልጠናም አመራሮች ሙስና ን መከላከል በሚቻልበት ስልቶች ላይ ግንዛቤ አግኝተው አርዓያ መሆን እንዲችሉ ማድረግ ነው ብለዋል።

ስልጠናውን የሰጡት በጂማ ዪኒቨርሲቲ የህግ ክፍል ከፍተኛ ተማራማሪ እና መምህር የሆኑት ዶ/ር የሱፍ ኢብራሂም በፌደራል መንግስት ተቋማት ዉስጥ በጥናት የተለዩ የአሰራር ስብራቶችን በብዙ ተጨባጭ ምሳሌዎች አስደግፈው አንስተው በማማብራት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመጠቆም አመራሮች የሙስና መከላከልን ሥራ አስቀድመው በመተግበር አርዓያ መሆን የሚችሉበትን ስልጠና ተሰጥተዋል።

We're dedicated to serve the community!

መቱ ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ህብረት ጋር በመሆን የኢሉ አባቦርን የተፈጥሮ ገፀ-በረከቶች፣ ታሪክ፣ ባህልና እሴቶችን የሚያስተዋውቅ የዉይይት መድረክ አዘጋጀ። መድረኩ በዩኒቨርሲቲዉ ...
26/04/2026

መቱ ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ህብረት ጋር በመሆን የኢሉ አባቦርን የተፈጥሮ ገፀ-በረከቶች፣ ታሪክ፣ ባህልና እሴቶችን የሚያስተዋውቅ የዉይይት መድረክ አዘጋጀ።

መድረኩ በዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የታሪከ ተመራማሪና መምህር የሆኑት አቶ ተመስገን ኮርጄ እንዲሁም አቶ ጅብሪል ሀሰን ስለአከባቢዉ ተፈጥሮ ፀጋዎች፣ ባህል፣ ቅርሶችና እሴቶች ለመድረኩ ተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል። ጥያቄዎችና ሀሳቦችም ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

በቀጣይ ከኢሉ አባቦር ዞን ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸዉ ጎን ለጎን የዞኑን ፀጋዎች፣ ታሪክ፣ ቅርስ ወዘተ አውቀዉ ወደየአከባቢያቸዉ ሲመለሱ የዩኒቨርሲቲዉና የዞኑ አምባሳደር የሚሆኑበት ምክረ-ሀሳብ ተዘጋጅቷል።

We're dedicated to serve the community!

26/04/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በልዩ ሁኔታ የሚመዘግባቸውን መራጮች ምዝገባ ማከናወን ጀመረ
-----------------------------------------------------------------
እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየው ምዝገባ ማንን ይመለከታል?
1. የሀገር ውስጥ ተፈናቃዩች፣
2. በዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች
3. በካምፕ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና በካምፕ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ቦርዱ ባቋቋማቸው ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች የሚመዘገቡ ሲሆን፤ ለመመዝገብም
• በአቅራቢያቸው በሚገኙ ቦርዱ ባቋቋማቸው ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች በአካል መቅረብ
• ማንነትን የሚያረጋግጥ ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ደግሞ ቦርዱ ለተማሪዎቹ ባዘጋጀው ልዩ የመመዝገቢያ ድረ-ገጽ የሚመዘገቡ ሲሆን፤ ለመመዝገብም
• ለምዝገባ በዩኒቨርስቲው ኔትዎርክ ላይ መሆን
• ስልክ ወይም ኮምፒውተር (ላፕቶፕ/ ዴስክቶፕ)
• ብሔራዊ መታወቂያ
• ብሔራዊ መታወቂያ ሲያወጡ የወጣበት የስልክ ቁጥር
------------------------------------------------------------------------
የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የድረ-ገጽ ላይ ምዝገባ ሂደት ቅደም ተከተል:-

1. በመራጭነት ለመመዝገብ የሚያስችለውን የመመዝገቢያ ድረ-ገጽ https://uni.mirchaye.nebe.org.et (በማንኛውም ብራውዘር በመጠቀም ማስገባት)፣

2. ቀጥሎ በሚመጣላችሁ ገጽ ላይ ለእናንተ የሚስማማዎትን ቋንቋ ይመርጣሉ፣

3. በመቀጠል “በፋይዳ አማካኝነት ወደ መለያ” የሚለውን ይጫናሉ፣

4. የፋያዳ ገጾ ሲመጣ ከፋይዳ መታወቂያችሁ ላይ 16 አኅዝ ያለውን ቁጥር (FAN) ማስገባት እና ከፋይዳ በስልክዎ የሚላከውን ባለ ስድስት አኅዝ የአንድ ጊዜ የማረጋገጫ ቁጥር (OTP) ያስገባሉ፣

5. ከፋይዳ ያገኛችሁት መረጃ ትክክል ከሆነ “ይቀጥሉ” የሚለውን በመጫን “መገለጫዎን ይጨርሱ” በሚለው ገጽ ውስጥ ስም፣ የአባት ስም፣ የአያት ስም በማስገባት በአካባቢው የሥራ ቋንቋ ይመዘግባሉ። የአካል ጉዳት ካለ ከዝርዝሩ በመምረጥ አፊዳቪት በመፈረም “ያስገቡ” የሚለውን በመጫን ቋሚ የመራጭነት መታወቂያዎን ያገኛሉ፤ ይህ መታወቂያ ቋሚ የመራጭነት መታወቂያዎ ሲሆን፤ መታወቂያዎን በስላክዎ አውርደው ወይም አትመው ሊይዙት ይገባል፣

6. ቋሚ የመራጭነት መታወቂያ አገኙ ማለት ምዝገባዎ ተጠናቅቋል ማለት አይደለም፤ በመሆኑም “7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይመዝገቡ” የሚለውን ትጫናሉ፤

7. በመቀጠል ድምፅ የምትሰጡበትን የምርጫ ጣቢያ ለማግኘት በመኖሪያ አድራሻዎ ወይም የሚገኙበትን ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ ካለ ከሚመጣልዎ ዝርዝር ውስጥ ይመርጣሉ፣
8. ከመረጡት ወረዳ ወይም ቀበሌ ሥር ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር ውስጥ ለእርሶ የሚቀርቦትን ለማግኘት “ይፈልጉ” የሚለውን በመጫን በመረጡት አድራሻ ሥር የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ያገኛሉ፣

9. በመቀጠል ካገኙት ዝርዝር ውስጥ ለእርሶ የሚቀርቦትን በመምረጥ በመረጡት ምርጫ ክልል በኗሪነት ያሎትን ቆይታ በዓመት እና በወር ያስገባሉ፣
10. በመቀጠል ተማሪ መሆናችሁን የሚገልጸውን የተማሪ መታወቂያችሁን የፊት እና የጀርባ ገጽ ያያይዛሉ፣

11. በመቀጠል ያስገቡትን መረጃ ትክክለኛነት የአፊዳቪት ሣጥን ውስጥ በመፈረም “ያረጋግጡ” የሚለውን በመጫን ለምርጫው ራሶትን ይመዘግባሉ፣

12. በመቀጠል ለድምፅ መስጫ ቀን ይዘው የሚመጡትን ለአንድ ጊዜ የሚያገለግል የምርጫ ካርድ ከሲስተሙ ያገኛሉ።

#ይመዝገቡ #ይሣተፉ

ትልቅ ዓርአያነት ያለዉ ተግባር .... የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ      "ታማኝነት ለራስ ነው!"ስሙ ተማሪ  ደበላ ከበደ ፍሪሳ ይባላል። በመቱ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጄክት ማኔጅመንት የድህረ ምረቃ ...
25/04/2026

ትልቅ ዓርአያነት ያለዉ ተግባር .... የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
"ታማኝነት ለራስ ነው!"

ስሙ ተማሪ ደበላ ከበደ ፍሪሳ ይባላል። በመቱ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጄክት ማኔጅመንት የድህረ ምረቃ ተማሪ ነው። ደበላ በ2015 ዓ.ም ከመቱ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል፤ በዚሁ ዩኒቨርስቲ በነፃ የ2ኛ ዲግሪ የመማር እድል አግኝቷል። ተማሪ ደበላ መልካም ባህሪ ያለው ሰው ሲሆን በጓደኞቹ ዘንድም በዚህ ባህሪይው ይወደዳል። በተጨማሪም፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቱን ሲማር በነበረበት ወቅት በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ውስጥ ዋና ፃፊ እና በዩኒቨርስቲው ውስጥ በተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች ውስጥ በመሳተፍ ብዙ አርዓያነት ያላቸውን ስራዎች ሰርቷል። ተማሪ ደበላ “ታማኝነት ለራስ ነዉ!” ይላል። ይህንን አቋሙን የሚያረጋግጥ ተግባራዊ ስራ ሰርቷል።

ደበላ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ/Facebook አረብ ሀገር በስራ ላይ ያለች ስሟ ገነት ኡርጌ የተባለች ሴት ከሁለት ወር በፊት የፌስቡክ የተከታዮች ቁጥር ለመጨመር አስባ ለእሱ Facebook Follow challenge ሰጥታው ነበረ። እሱም የተሰጠውን የፌስቡክ Follow Challenge አሸንፏል ነበር። በዚህ ምክንያት ባለፈው ከሁለት ወር በፊት ቻሌንጁን በማሸነፉ የንግድ ባንክ ሂሳቡን ልኮ ነበር። በመሆኑም ገንዘቡ አንድ በዱባይ በሚኖር ሰው አማካኝነት ለደበላ ተልኮለት ነበር።

አሁን ደግሞ ገነት ለቤተሰቧ ገንዘብ ለመላክ አስባ ለዚያ ሰው ብር ትልካለች፤ ሰውዬው ደግሞ ደበላ የእሷ ቤተሰብ መስሎት በስህተት በዕለተ ሀሙስ 15/08/2018 ዓ.ም 92,444.00 (ዘጠና ሁለት ሺህ አራት መቶ አርባ አራት) ለደበላ ያስተላልፋል። ነገር ግን ደበላ የገንዘቡ ባለቤት የእኔ እንደሆነ እንዲናገር ለ24 ሰዓታት ከጠበቀ በኋላ፣ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነቃ እና ማህበራዊ ሚዲያውን/ Facebook ለማየት ስልኩን ሲከፍት፣ ወደ ባንክ አካውንቱ የገባው የተሳሳተ የገንዘብ መሆኑን የሚያሳይ መልእክት/Inbox ደረሰው። ይሁን እንጂ ደበላ ለምረቃ ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም እምነት የሚጣልበት ሰው መሆን እንደሚሻል አምኖ ገንዘቡን ለመመለስ ወሰነ።

በዚህም ምክንያት ደበላ ታማኝነቴ የእኔ ነው በማለት በዕለተ አርብ 16/08/2018 ዓ.ም ይህንን ብር ሁሉንም 92,444.00 (ዘጠና ሁለት ሺህ አራት መቶ አርባ አራት) ለተላከለት ሰው ለሻይ ብሎ እንኳን ሳያስቀር ብሯን መልሷል።

ስለዚህ ደባላ ደጋግሞ “ታማኝነት ለራስ ነው!” ይላል ገንዘቡን ለምን እንደመለሰ ሲጠየቅ። በእርግጥ ነው፣ መታመን ለራስ ነው፣ ለሌሎች አይደለም። ነገር ግን ለሌሎች ምሳሌ መሆን ከሰዎች ምስጋናና አክብሮትን ቢያስገኝም ከፈጣሪ ግን ታላቅ በረከትን ያሰጣል። መልእክታችን ይህ ተምሳሌት በሁሉም ዘንድ መለመድ አለበት እንላለን።

መቱ ዩኒቨርሲቲም እንደ ደበላ ከበደ ፍሪሳ ያሉ በዕዉቀትና በመልካም ስነ-ምግባር የታነፁ ዜጎችን እያፈራ በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል።

We're dedicated to serve the community!

Gocha Fakkeenyummaa Guddaa Qabu: Barataa Yuunivarsiitii MattuuAmanamummaan koo kanuma koo ti!Barataa Dabalaa Kabbadaa Fi...
25/04/2026

Gocha Fakkeenyummaa Guddaa Qabu: Barataa Yuunivarsiitii Mattuu

Amanamummaan koo kanuma koo ti!
Barataa Dabalaa Kabbadaa Firrisaa jedhama. Barataa digrii lammaffaa Muummee Pirojekti Maanaajimentii Yuunivarsiitii Mattuuti. Barataa Dabalaan barnootaa isaa digirii jalqabaas Yuunivarsiitii Mattuutti gosa barnoota Ikkoonomiksiin bara 2015 ALI eebbifamee asumatti carraa barnootaa bilisaa digirii lammaffaa argatee barachaa jira.

Barataa Dabalaan nama amala qabeessaa fi hiryoota isaa biratti jaallatamuu dha. Kana malees, yeroo digirii isaa jalqabaa barachaa turetti barreessaa gamtaa barattootaa fi koreewwan barattootaa adda addaa keessatti qooda fudhachuun hojii fakkeenyummaa qaban hedduu hojjetaa tureera.

Maaliree, barataa Dabalaan “Amanamummaan koo kanuma koo ti.” jechuun hojii fakkeenyummaa isaa daran cimsu hojjete.
Dubbiitu akkas ture, namni Dabalaan akka tasaa karaa toora miidiyaa hawaasaa/Facebook wal beeku Shamarree Gannat Urgee kan jedhamtu biyya Arabaa irraa ji'a lama (2) dura Follow Challenge/ followers guddisuu karaa Facebook isaa waan isaaf laattee innis challenge sani injifatee ture.

Sababa saniif qarshii Facebook follow challenge akka galchitu Account CBE/ herreega baankii daldalaa isaa ergee ture. Yeroo sani qarshiin isaas karaa nama biyya dubaayi jiru tokkoon galeefii ture. Namni sun namoota adda addaaf qarshii jijjiree erga.

Namni sun garuu guyyaa Kamisaa yookiin 15/08/2018 qarshii kuma sagaltamaa oli (92,444) miseensa maatii ishee se'ee qarshii mucayyoo dogogoraan Account Dabalaa irratti galcheef. Mucayyoon sun garuu maatii isheef ture kan ergi jetteenii turte namichaan.

Dabalaan amanamummaan waan hundaa naaf caala jechuun guyyaa kaleessaa /Jimaata 16/08/2018 qarshii kana hunda isaa deebiseera osoo kan shaayi jedhee illee hin hanbisiin.

Kanaaf, Dabalaan deebisee deddeebisee “Amanamummaan koo kanuma koo ti!” jedha. Dhugaa dha amanamuun ofiif malee namaaf mitii. Garuu namaaf fakkeenya ta’uun immoo badhasa galataa fi kabajaa namoota biraa; Waaqa biraa immoo eebba guddaa isaa namaaf laata. Fakkeenyummaan kunis hunda biratti baballachuu qabaan dhaamsa keenya.

Yuunivarsiitiin Mattuus barattoota beekumsa fi naamusa gaarii akkasiitiin dhaloota qaree baasaa jiraachuu isaatti ni boona.

We're dedicated to serve the community!

Address

Ethiopia
Mattu
318

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mattu University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share