Wolaita Sodo PolyTechnic College/ወላይታ ሶዶ-ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ

Directions

Wolaita Sodo PolyTechnic College/ወላይታ ሶዶ-ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Sodo PolyTechnic College/ወላይታ ሶዶ-ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ, College & University, Mi`irab Abaya.

 ፦
21/10/2025

፦

አስደሳች ዜና ለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ፦
21/10/2025

አስደሳች ዜና ለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ፦

መልካም ዜና ለስኮላርሺፕ ዕድል  ፈላጊዎች የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው ኦፕስዋት OPSWAT Academy ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት አካሂዷል፡፡...
12/09/2025

መልካም ዜና ለስኮላርሺፕ ዕድል ፈላጊዎች

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው ኦፕስዋት OPSWAT Academy ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት አካሂዷል፡፡
በዚህም መሰረት በሳይበር ደንነነት (Cyber Security) ላይ ያተኮረ የስኮላርሺፕ ዕድል ለኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና ሠራተኞች ሰጥቷል፡፡ ይህንን ዕድል ለመጠቀም፡-
1. የአይሲቲ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂና መሰል ዘርፎች ላይ የተማሩ ወይም በመማር ወይም በሥራ ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ስልጠናው እስከ 6 ወራት ባለው ጊዜ ሊጠናቀቅ የሚችል ሲሆን ስልጠናው የሚሰጠው በኦንላይን ዘዴ ነው፡፡
3. በስኮላርሺፑ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ በኢንስቲትዩቱ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት በኩል ፍላጎት መሰብሰብ የሚገባ በመሆኑ https://forms.office.com/r/tcKunL9zL0 በሚለው ሊንክ ገብታችሁ እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡
4. መረጃው ከተሰበሰበ በኋላ በአጭር ቀናት ውስጥ ቀጣይ ሂደቱን የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡

የወላይታ ሶዶ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ድን ኢ/ር ያዕቆብ ያስን የ2018ዓ.ም ዘመን መለወጫ/ እንቁጣጣሽ በዓልን አስመልክቶ የተላለፈ  የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!!በቅድሚያ የተወደዳችሁ መላው ...
10/09/2025

የወላይታ ሶዶ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ድን ኢ/ር ያዕቆብ ያስን የ2018ዓ.ም ዘመን መለወጫ/ እንቁጣጣሽ በዓልን አስመልክቶ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!!

በቅድሚያ የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ መላው የኮሌጆችን ሠራተኞች እና ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለ2018 አዲሱ ዓመት/ የእንቁጣጣሽ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን ።

መላው የኮሌጆችን ማህበረሰብም በተቀናጀ መልኩ እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብራዊ አንድነቱን አጠናክሮ በማስቀጠል ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ እየቀየረ የተቋሙን ራዕይ ማሳካት በሚያስችል ቁመና አይቀሬ ወደ ሆነው የለውጥ እና የዕድገት ጉዞ እየገሰገሰ ይገኛል።

የተከበራችሁ የኮሌጆችን አሰልጣኞች እና የአስተዳደደር ሠራተኞች እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በሙሉ እንደተለመደው በአዲሱ አመት በተቋማችን ሁለንተናዊ እና ቀጣይነት ያለውን ዕድገት ማስመዝገብ እንድንችል እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ እንዲንሰራ በኮሌጆችን ስም ጥሪያችን እናቀርባለን ፡፡

ኢ/ር ያዕቆብ ያስን በመጨረሻም አሉ አዲሱን የ2018 ዓ.ም ዘመን መለወጫ/ እንቁጣጣሽ በዓልን ስናከብር፣ በፍጹም ወንድማማችነት፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ መንፈስ
እንድናከብረው ለማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል።

አዲሱ ዓመት የጤና፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!

በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!
መልካም አዲስ ዓመት!!

📸
ብቁና ተነሳሽነት ያለው ስራ ፈጣሪ ዜጋን እንፈጥራለን !!

የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በኮሌጁ ቅጥር ጊቢ የክረምት በጎ የደም ልገሳ፣ችግኝ ተከላ እና ማዕድ ማካፈል አካሄዱወ.ሶዶ፣ጳጉሜ 4/2017ዓ.ም ወ/ሶ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/መ"በመትከል ማንሰራራት"በሚል ...
09/09/2025

የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮሌጁ ቅጥር ጊቢ የክረምት በጎ የደም ልገሳ፣ችግኝ ተከላ እና ማዕድ ማካፈል አካሄዱ

ወ.ሶዶ፣ጳጉሜ 4/2017ዓ.ም ወ/ሶ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/መ

"በመትከል ማንሰራራት"በሚል በሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት በጎ ደም ሊገሳና የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ እና ማዕድ ማካፈል ተካሂዷል።

መረሀ ግብሩን ያሰጀመሩት የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙየ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ሀላፊ አቶ ግርማቸው ከፍያለው በንግግራቸው በሐገር ደረጃ እየተተገበረ የሚገኘውን የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ መረሀግብር ተግባራዊ ከማድረግ ረገድ ሁሉም ኮሌጆች አቅደው ወደ ተግባር የገቡ መሆኑንም ገልፀዋል።

በሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቂጥር ግቢ ውስጥ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብርም የዚህ ተግባር አካል ስለመሆኑም ያነሱት ሀላፊው ሌሎችም ኮሌጆች ያሉዋቸውን ክፍት ቦታዎች ከማይበላ ዛፍ ወደሚበላ ዛፍ የመቀየር ሐገራዊ ኢኒሼቲቭ ተግባረዊ ኢንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በተለይም የዛሬዋን ቀን ለየት የሚያደርገው የኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ብስራት የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን፤ የቀጠናውን የኃይል ሚዛን የሚቀይር ግዙፍ ፕሮጀክት ምረቃ ዕለት መሆኑ ዛሬ የምገባ ፕሮግራሙ ተካፋይ የሆኑ እናቶችና አካል ጉዳተኞች ከራሳቸው አልፈው ሌሎችን የሚመግቡ የሚሆኑበት የማብሰሪያ ቀን ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያን የማንሠራራት ምዕራፍ ጅማሮ በማብሰር ወደ አዲስ ከፍታ በድል የሚያሸጋግረን ነው ብለዋል፡፡

የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ኢ/ር ያዕቆብ ያሲን በበኩላቸው በኮሌጁ ቂጥር ጊቢ ውስጥ የክሊስተር ኮሌጅ ዲኖች መላው የአስተዳደር ሠራተኞችን ባሰተፈ መልኩ የአረንጓዴ አሻራ መረሀ-ግብር የችግኝ ተከላ መካሄዱን ተናግረዋል።

የኮሌጁ ዲን አክለው ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ችግኞችም እንዲፀድቁ አስፈላጊውን እንክብካቤ ከማድረግ ረገድ ኮሌጁ በትኩረድ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት የበጎነት መገለጫ ነው ያሉት ኢ/ር ያዕቆብ ያለንን ማካፈል የወግ ባህላችን አንዱ አካል ሆኖ የዘለቀ ዕሴት መሆኑን በመግለፅ ይህ በጎ ተግባር ከበዓላት ሰሞን ባሻገር አጠናክረን በቀጣይነት የመስጠት ፣የመረዳዳትና የመደጋገፍ ዕሴታችንን ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፣የደም ልገሳ እና ማዕድ ማጋራት መረሀ ግብሩ ላይ የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምኀህርት ስልጠና መምሪያ ሀላፊ አቶ ግርማቸው ከፍያለው እንዲሁም የማናጅመንት አባላት ፣የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና እና ምክትል ዲኖቼ ፣የኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞችና የክላስተር ኮሌጅ ዲኖች ተሳትፈዋል።

‎"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ‎የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞዎችና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብልፅግና ፓርቲ...
03/09/2025

‎"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ
‎የብልፅግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞዎችና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብልፅግና ፓርቲ የህብረት አባላት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
‎
‎ ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም
‎ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃ ተቋማት ቴክኒካል ድጋፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ  ክልሎች የሚገኙ የውሃ ተቋማት የቴክኒካ...
01/09/2025

በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃ ተቋማት ቴክኒካል ድጋፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ የውሃ ተቋማት የቴክኒካል ድጋፍ እና የምዘና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት የመጡ ቡድኖች በወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በውሃ ዲፓርትመንትና በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዲፓርትመንት ላይ ዳሰሳ ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ፤
‎
‎ወላይታ ሶዶ፦ ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
‎በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃ ተቋማት ቴክኒካል ድጋፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ የውሃ ተቋማት የቴክኒካል ድጋፍ እና የምዘና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት የመጡ ቡድኖች በወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በውሃ ዲፓርትመንትና በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዲፓርትመንት ላይ ዳሰሳ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
‎
‎በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃ ተቋማት ቴክኒካል ድጋፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ የቴክኒካል ድጋፍ የሚሰጥና የዘርፉ ባለሙያዎች ወደ ምዘና እንድገቡ ድጋፍ የሚያደርግ የሥራ ክፍል ነው፡፡
‎
‎ስለሆነም የስራ ክፍሉ በ2018 በጀት ዓመት ለማከናወን ካቀዳቸው ሥራዎች መካከል አንዱ የውሃ ተቋማት ያለባቸውን ክፍተት እና የሙያ ብቃት ምዘና ፍላጎት በዳሰሳ ጥናት በመለየት ክፍተትን የሚሞላ ድጋፍ ለማድረግ በአራት ክልሎች (በኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ ፣በደቡብ ክልሎች የሚገኙ በውሃ ዘርፍ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት፣የዞንና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፈሳሽ አገልግሎት እና የሙያ ብቃት ምዘና ኤጀንሲዎች ) የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ወደ ሥራ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
‎
‎የዳሰሳ ጥናቱ ዓላማ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የውኃ ተቋማት ነባራዊ ሁኔታ እና የድጋፍ ፍላጎት በዳሰሳ ጥናት በመለየት በተለዩ ክፍተቶች መሠረት የቴክኒካል እና የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ድጋፍ ለማድረግ በዕቅድ ውስጥ በማካተት መደገፍ ነው ::
‎
‎የዳሰሳ ጥናቱ አስፈላጊነት በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር በሀገሪቱ በውኃ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት ክፍተታቸውን በመለየት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያደርግላቸው ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ስለሆነም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የውሃ ተቋማት ያሉበት ሁኔታ የተሟላ መረጃ መያዝ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ሲሉ የዳሰሳ ጥናት ቡድን ገልፀው በቀጣይ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ተቋሙን በሚደግፉበት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ በመግባባት ተጠናቅቋል፡፡

የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ለ2018 ዓ.ም የዝግጅት ምዕራፍ ሥራ ያለበትን ደረጃ በወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተገመገመ፤‎‎ወላይታ ሶዶ፦ ነሐሴ 26/2017 ዓ...
01/09/2025

የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ለ2018 ዓ.ም የዝግጅት ምዕራፍ ሥራ ያለበትን ደረጃ በወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተገመገመ፤
‎
‎ወላይታ ሶዶ፦ ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
‎
‎የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ለ2018 ዓ.ም የዝግጅት ምዕራፍ ሥራ ያለበትን ደረጃ በወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተገመግሟል፡፡ የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ የሠልጣኝ አሰልጣኝ ልማት ቡድን መሪ አቶ በረከተአብ ያዳ ስለ ግምገማው ዓላማ ሲናገሩ ተግባሮቻቸንን ማሳካት የምንችለዉ ባለድርሻ አካለት ጋር በቅንጅት በመሥራት፤ በተለይም ደግሞ ህብረተሰባችንን ስለክህሎት ልማትና ስለስልጠና ተቋማት ጠቀሜታን በሚመለከት ግንዛቤያቸዉን የማሳደግ ሥራን በመሥራት የህብረተሰቡም እምቅ አቅም አሟጠን መጠቀም ስንችል ነዉ፡፡ ስለሆነም ይህ ቼክ-ሊስት የኮሌጆቻችንን ተቋማዊ ዝግጅታቸዉን ከመደገፍ ባሻገር ህብረተሰባችንንና ባለድርሻ አካላትን በሙሉ ማነቃነቅ እንዲያስችል ዓላማ ያደረገ ነዉ፡፡ አክለውም አቶ በረከተአብ ያዳ የ2017 ዓ/ም ሀገራችንን/የክልላችን በክህሎት ልማት ሥራችን በአዲሱ የለዉጥ አምጪ እሳቤ መነሻ፤ በአራቱ ዋና ዋና ግቦች መነሻ ታቅደዉ የነበሩ ዝርዝር ግቦችን ከማሳካት ረገድ የተመዘገቡ ዉጤቶችን በማስቀጠል፤ በጉድለት የተገመገሙና አዲስ የትኩረት መስኮችን ጨምሮ በ2018 የበጀት ዓመት ለማሳካት ተለጥጦ የተያዘዉን ዕቅድ በላቀ ዉጤታማነት በመፈጸም ሪፎርሙን ለማጽናት የሚረዳ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ማረጋገጥ የሚያስችል የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራትን ማሳካት ነዉ፡ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
‎
‎የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዝግጅት ምዕራፍ እየሠራቸው ያሉ ሥራዎች አበረታች መሆኑን የግምገማ ቡድን ገልፀው በቀጣይ በጉድለት በታዩ ጉዳዮች ጠንክረው በመሥራት ማሻሻል እና በጥንካሬ በተለዩ ጉዳዮች ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቅቋል፡፡
‎
‎

የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለ24ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 737 ተማሪዎችን አስመረቀ ነሐሴ 17/2017 ዓ.ምተመራቂዎች ከስራ ጠባቂነት ተላቀው ስራ በመፍጠር የሀገራ...
23/08/2025

የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለ24ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 737 ተማሪዎችን አስመረቀ

ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም

ተመራቂዎች ከስራ ጠባቂነት ተላቀው ስራ በመፍጠር የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ እንዲያፋጥኑም ጥሪ ቀርቧል

በምረቃ መርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ እና የዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ ግርማቸው ከፍያለው ተመራቂዎች በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሠረት ወቅቱና የገበያ ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በተማሩበት ዘርፍ ተሰማርተው ራሳቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ለዛሬው ቀን እንዲበቁ በምክር፣ በሞራል፣ በገንዘብ ያልተቆጠበ ድጋፍና ጥረት ያደረጉ ቤተሰቦችም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የኮሌጁ ዲን ኢንጂነር ያዕቆብ ያሲን በበኩላቸው ኮሌጁ ከሀገራዊ ፍላጎቶችን ባሻገር ወቅቱን ታሳቢ ያደረጉ አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት የሀገራችን የተማረ የሰው ኃይል ፍላጎት ለሟሟላት እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ ፈጣን የሆነ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ለማረጋገጥ እና የዘርፉን የማስፈጸም አቅም ከፍ ለማድረግ አፅንኦት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

ተቋሙ ለ24ኛ ዙር በቀንና በማታ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ከደረጃ 1 እስከ 5 ያሰለጠናቸውን 737 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ማስመረቁንም የኮሌጁ ዲን ተናግረዋል።

ከመደበኛ የስልጠና መርሃ ግብር ባሻገር ከ5000 በላይ ለሚሆኑ ሴት ሠልጣኞችን ለ21 ቀናት የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪትን አስመልክቶ ሥልጠና መስጠቱንም አብራርተዋል።

አስተያየት የሰጡ ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው በቆይታቸው በቂ ዕውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ህዝብና ሀገራቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በትምርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

የወላይታ ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ1990 ዓ/ም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ባሻገር ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳትና በማምረት ለሀገር ብልፅግና ዕውን መሆን የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 24 ዙር  ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል ።******ወላይታ ሶዶ፦ነሐሴ 17/ 2017 ዓም የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 24 ዙር   ያሰለጠና...
23/08/2025

የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 24 ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል ።
******
ወላይታ ሶዶ፦ነሐሴ 17/ 2017 ዓም የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 24 ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ፣የወላይታ ዞን ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊና የአስተዳዳሪው ተወካይ አቶ ግርማቸው ከፍያለው፣ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ዲን ኢንጂነር ያዕቆብ ያሲን የዞኑ መልካም አሰተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሸቱ ታደሰ ጨምሮ የከተማ የዞን የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተመራቂዎች እና የተመራቄ ቤተሰቦች እየተሳተፉ ናቸው ።

ለ24ተኛ ዙር የምርቃ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!!!የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሠልጣኞችን ያስመርቃል፡፡ሁሉም ዝግጅቶች ተጠናቅቆ ወድ ተመራ...
22/08/2025

ለ24ተኛ ዙር የምርቃ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!!!
የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሠልጣኞችን ያስመርቃል፡፡
ሁሉም ዝግጅቶች ተጠናቅቆ ወድ ተመራቂዎችን ይጠብቃል፡፡

Loading......

Address

Mi`irab Abaya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo PolyTechnic College/ወላይታ ሶዶ-ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share