Mizan Aman College of Health Science-macohs

Mizan Aman College of Health Science-macohs #የጤና ስነ ምግባርን እና ጥራትን እናሳድጋለን!
nurture health ethics and quality!

ለሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን  የEffective Teaching Skill(ETS) እና Clinical Teaching Skill(CTS)  ስልጠና ተሰጠ።ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም: ሚ...
25/04/2026

ለሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን የEffective Teaching Skill(ETS) እና Clinical Teaching Skill(CTS) ስልጠና ተሰጠ።

ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም: ሚዛን አማን

ለሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን የEffective Teaching Skill(ETS) እና Clinical Teaching Skill(CTS) ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና መምህራኑ በሚያስተምሩበት ወቅት ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት እንዲሰጡ የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል።
ስልጠናው ከሚያዚያ 15 ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የቆዬ ሲሆን ስልጠናው ለአዳዲስ መምህራን እና ደረጃቸውን አሻሽለው ከትምህርት ለተመለሱት መምህራኖች ሲሰጥ ቆይቷል።
ሰልጣኞቹ ይህ ስልጠና መሰጠቱ እንዳስደሰታቸው ገልፅው እንዲህ አይነት ስልጠና በይበልጥ ለአዲስ ተቀጣሪ መምህራን አስፈላጊ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው እንዳስተላለፉት ይህ ስልጠና መሰረታዊ የማስተማር ስነ ዘዴ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ ሙያዊ ስልጠናዎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

በዓልን ከተማሪዎች ጋር  በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ::ሚያዚያ 4/2018ዓ.ም ሚዛን አማን:​​ልጆቻችን ተማሪዎቻችን ናቸው በሚል መርህ የሚመራው የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በዓ...
12/04/2026

በዓልን ከተማሪዎች ጋር በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ::

ሚያዚያ 4/2018ዓ.ም ሚዛን አማን:

​ልጆቻችን ተማሪዎቻችን ናቸው በሚል መርህ የሚመራው የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በዓልን ከተማሪዎች ጋር በሚል ሀሳብ : ላለፉት ሁለት አመታት ሲያከናውን እንደነበረው : ሁሉ : የዘንድሮውን የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል ከተማሪዎች ጋር በጋራ አክብሯል።

​በበዓሉ ዝግጅት ላይ የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ፣ የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

​የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ተማሪነት የነገውን ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመሆን የሚዘጋጁበት ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በጤናው ዘርፍ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች ጤናማ ዜጋን ለማፍራት የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

ከንቲባው አክለውም ተማሪዎች ከቤተሰብ ተለይተው በዓልን ሲያከብሩ የባይተዋርነት ስሜት እንዳይሰማቸው ይህንን መድረክ ያመቻቹ የኮሌጁን አመራሮችና ሰራተኞች አመሰግናለሁ፤ ከተማችንም ለተማሪዎች ሁሌም ቤታቸው ናት ብለዋል።

​የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ በበኩላቸው፣ የፋሲካ በዓል የይቅርታ፣ የመረዳዳትና የልግስና መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዝግጅቱ ተማሪዎች በበዓል ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና የአብሮነት እሴት እንዲጎለብት ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

​እንደ ኮሌጁ ዲን ገለጻ፣ በ2018 የትምህርት ዘመን በኮሌጁ 2 ሺህ 414 ተማሪዎች በ4 የትምህርት ዘርፎች በዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ይህ የበዓል ዝግጅት እንዲሳካ ​ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ከኪሳቸው በማዋጣት፣ ​መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ከደመወዛቸውና ከጉልበታቸው በመለገስ፣
​የከተማው ባለሀብቶችና ነዋሪዎችም በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

​የተማሪዎች ተወካይና የቢኤስሲ ነርሲንግ ተማሪ የሆነው አማኑኤል ከበደ፣ በኮሌጁ ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ በዓልን በጋራ ሲያከብሩ ታላቅ ደስታ እንደሚሰማቸው ገልጿል።

አብዛኛው ተማሪ ከሩቅ አካባቢ የመጣ በመሆኑ፣ እንዲህ አይነት መድረኮች ብቸኝነትን አስወግደው የኢትዮጵያዊነት እና የአብሮ መብላት እሴትን በተግባር እንደሚያሳዩ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

​የኮሌጁ የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ዲን አቶ ሽመልስ ወንድሙ በበኩላቸው፣ ከዓመት ዓመት የተሳታፊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ዝግጅቱ ህብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት እና ተማሪዎች የሚዛን አማን ከተማ አምባሳደር ሆነው እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ የትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ሚያዚያ 3/2018ዓ.ም ሚዛን አማን:ለውድ የክርስትና እመነት ተከታይ ተማ...
11/04/2026

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ የትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሚያዚያ 3/2018ዓ.ም ሚዛን አማን:

ለውድ የክርስትና እመነት ተከታይ ተማሪዎቻችን፤መምህራን፤የአስተዳደር ሰራተኞች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዓሉ የሰላም ፤ የፍቅር፤የደስታና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተግባራት የግምገማ መድረክ ተካሄደ።     መጋቢት 16/2018ዓ.ም ሚዛን አማን ​በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ወቅታዊ የመንግስት ተግባራት የግምገማ መድ...
25/03/2026

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተግባራት የግምገማ መድረክ ተካሄደ።
መጋቢት 16/2018ዓ.ም ሚዛን አማን

​በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ወቅታዊ የመንግስት ተግባራት የግምገማ መድረክ : የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በተገኙበት ተካሄዷል።

በግምገማ መድረኩ የኮሌጁ አጠቃላይ የመንግሥት ተግባራት አፈፃፀምን በተመለከተ ግምገማ የተደረገ ሲሆን : የኮሌጁ የበላይ አመራሮች ከመንግስት ስራ አፈፃፀም እና ወቅቱ ከሚጠይቀዉ የአመራር ቁመና አንፃር ግምገማ አካሂደዋል።

ባለፉት አመታት ከነበረው የተቋም የገፅታ ግንባታ ስራ በተመለከተ ፣ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ: አሰራርን ከመትከል እና ስራዎችን ከመከወን አንፃር የታዩ ስኬቶች እና የተስተዋሉ ውስንነቶች : በጥልቀት የተገመገሙ ሲሆን መድረኩ አመራሩን ከአመለካከት እና ከተግባር አንፃር አርሞ ቀሪ ስራዎችን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በመድረኩ እንደገለፁት : አመራሮቹ በተቋሙ ላይ እያሳዩ ያሉት ለውጥ የሚታይ እንዲሁም የሚበረታታ መሆኑን እና ለለውጥ ተነሳሽነቱ የሚደንቅ እንደሆነ ገልጸው : ወቅቱ የሚፈልገውን ፈጣን ለውጥ ከማምጣት ረገድ እና በተንሰላሰለ መንገድ ተቋሟዊ ስኬት ከማስመዝገብ አንፃር ወደፊት በሰፊው ተወስደው ሊሠሩ የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ አሳስበዋል።

በተጨማሪም : ኮሌጁ ዉስጥ ያለውን ህብረ ብሔራዊነትን እና ብዝሀነትን ከማስተናገድ አንፃር ያሉ ተግባራት በማበረታታት እና በማስቀጠል ረገድ የተጀመሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ረገድ በተወሰነ መልኩ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በቅንጅት በማረም : ኮሌጁን ከዚህ በበለጠ ወቅቱን የዋጀ በውጤቱ የተመሰገነ ተቋም በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ጨምረው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ግምገማውም የነበረው ዉጤት የሚበራታታ ውጤት እንደሆነ ገልፀው የኮለጁን አላማ ለማሳካት የአመራሩ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ቀሪ ስራዎችን ከውኖ ተቋምን የማሻገር ስራ ላይ በጋራ ለመረባረብ ስምምነት ላይ ተደርሷል::

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዒድ-አልፈጥር በዓል ከእስልምና እምነት ተከተይ ተማሪዎች ጋር  ተከበረ ።መጋቢት 11/2018 ዓ.ም ሚዛን አማን:በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዓልን ከ...
20/03/2026

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዒድ-አልፈጥር በዓል ከእስልምና እምነት ተከተይ ተማሪዎች ጋር ተከበረ ።
መጋቢት 11/2018 ዓ.ም ሚዛን አማን:

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዓልን ከተማሪዎቻችን ጋር በሚል ሀሳብ 1447ኛዉን የዒድ-አልፈጥር በዓል ከእስልምና እምነት ተማሪዎች ጋር በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።
በበዓሉ ላይ የኮሌጁ የስራ አመራር አባላቶች እንዲሁም ከእስልምና እምነት ውጭ የሚገኙ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ኮሌጁ እንዲህ አይነት በዓላትን ከተማሪዎች ጋር ማስለፍ ላለፉት ሦስት አመታት ሲከውን እንደቆየ የሚታወቅ ነው::

የበአልን ከተማሪዎቻችን ጋር ሀሳብ ዋነኛው አላማ : በአላትን ከአከባቢያቸው እና ከቤተሰብ ራቅ ብለው ለሚያከብሩ ተማሪዎች : በጊቢ ቆይታቸው የሚሰማቸውን የባይተዋርነት ስሜት ለማጥፋት እና የመተባበር መንፈስ ለመፍጠር የታሰበ እንደሆነ ተገልጿል።

በድጋሚ ለእስልምና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን መምህራን፣ አስ/ር ሰራተኞች እንዲሁም ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ለ1447ኛው ኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ኢድ-ሙባረክ!!

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ለ1,447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉየሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ...
19/03/2026

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ለ1,447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ለ ውድ የኮሌጆችን የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች ፤ መምህራን ፤ የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1,447 ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ።

በረመዳን ወቅት ተማሪዎቻችን ያሳዮት የመረዳዳት እና ትብብር ፡ የረመዳንን ዕሴት አጉልቶ ያሳየ በመሆኑ ይህንን አብሮነትና የመደጋገፍ ባህል አጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

በመጨረሻም አቶ ፀጋዬ አትርሴ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ኢ ድ ሙባራክ !

  የሚዛን አማን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ላይ ሰራተኞችን በቋሚነት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
18/03/2026



የሚዛን አማን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ላይ ሰራተኞችን በቋሚነት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ "50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን በወካይ  ቀን ተከብሮ ዋለ። መጋቢት 8/2018ዓ. ም ...
17/03/2026

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ "50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን በወካይ ቀን ተከብሮ ዋለ።

መጋቢት 8/2018ዓ. ም ሚዛን አማን
******

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ "50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የዓለም የሴቶች ቀን በወካይ ቀን ተከብሮ ዋለ:: በአለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ የተከበረው ማርች-8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን መጋቢት 7/2018 በወካይ ቀን ተከብሮ ውሏል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቤንች ሸኮ ዞን ሴቶችና ሕፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምርያ ተወካይ ወ/ሮ በለጡ ከበደ በመልዕክታቸው እንደገለፁት : ሴቶች ላይ በሥርዓተ ፆታ የሚደርሰውን ተፅዕኖ በመቀንስ ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪ ለማድርግ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመድረኩ ሁለት ሰነዶች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን : በመጀመሪያ የኮሌጃችን ምርምር እና ማህብርስብ አግልግሎት ም/ዲን ወ /ሮ መሰረት ገ/ማርያም በኮሌጁ የሕፃናት ማቆያ ለማቋቋም የሚረዳ ሰነድ ለታዳሚዎች ያቀርቡ ሲሆን: በሰነዱ የሕፃናት ማቆያ ለተቀሙ የሚኖረው ፋይዳ ተመላክቷል :: ሁለተኛውን የውይይት ሰነድ ያቀረቡት መ/ርት ቅድስት አለሙ የ50 ዓመት የሴቶች ቀንን ታሪካዊ ዳራ አስመልክቶ ሰፊ የውይይት ሀሳብ ያነሱ ሲሆን : በሁለቱም ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎበታል።

እንዲሁም ዝግጅቱን ለመታደም እና ለማድመቅ ሚዛን ምስገና አካዳሚ ሴት ተማሪዎች ተገኘተዉ የነበረ ሲሆን ፕሮግራሙ በተለየ እና በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመጨረሻም የኮሌጃችን ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን ወ/ሮ መሰረት ገ/ማርያም የመዝግያ ንግግር በማድረግ ተጠናቋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኢፍጣር መረሀግብር ተካሄደ ። መጋቢት 5/2018ዓ. ም ሚዛን አማን በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከእስልምና እመነት ተከታይ ተማሪዎች ጋር የኮሌጁ ኃላፊ...
14/03/2026

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኢፍጣር መረሀግብር ተካሄደ ።

መጋቢት 5/2018ዓ. ም ሚዛን አማን

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከእስልምና እመነት ተከታይ ተማሪዎች ጋር የኮሌጁ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በተገኙበት : የኢፍጣር መርሀግብር ተካሂዷል።

የኢፍጣር መርሀግብሩ ተማሪዎች በኮሌጅ ቆይታቸው ሊያዳብሩት የሚገባውን የአብሮነት እና የመተባበር መንፈስ ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለው ተግልጿል።

በኢፍጣር መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ባስተላለፉት መልዕክት : እንዲህ አይነቱ የመሰባሰብ ተግባር እንደ ተቋም በስፋት የሚሠራበት እንደሆነ እና ቀደም ሲልም በዓልን ከተማሪዎች ጋር በሚል ሀሳብ የተጀመረ በጎ ተግባር ተጠናክሮ ዛሬ ላይ እንዲህ አይነቱን ልዩ የኢፍጣር መርሀግብር ለማሰናዳት ተችሏል ያሉ ሲሆን። በቀጣይም የኢድ እና የፋሲካ በዓልን በዚህ መልክ ሁሉም የኮሌጁ ማሕበረሰብ ከተማሪዎች ጋር በጋራ ተሰባስቦ ማክበር እንደሚገባ ጨምረው ገልፀዋል።

በኢፍጣር መረሀግብሩ ላይ የተገኙ የእስልምና ተከታይ ተማሪዎች : በኮሌጁ የሚደረጉ በዓላትን በጋራ የማክበር ልምድ ሊቀጥል የሚገባ እንደሆነ እና የዛሬውም የኢፍጣር መርሀግብር መዘጋጀቱ እጅጉን እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

የጤና ባለሙያዎችን በብቃት ማፍራትና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ማስፋፋት ትኩረት እንዲሰጠው ተጠቆመ።የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ...
10/03/2026

የጤና ባለሙያዎችን በብቃት ማፍራትና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ማስፋፋት ትኩረት እንዲሰጠው ተጠቆመ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የ8 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሂዷል።

መጋቢት 1/2018ዓ. ም ሚዛን አማን

በመድረኩ የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ በኮሌጁ በትምህርት፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች በ8 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የሚያካትት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።

በሪፖርቱ መሠረት የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ1999 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በክልሉ ውስጥ ያለው ብቸኛው የመንግስት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነው። ኮሌጁ የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ለመፍታት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን በማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ኮሌጁ በ7 የዲፕሎማ ፕሮግራሞች እና በ4 የዲግሪ
ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እያሰለጠነ ሲሆን በኮምፕረንሲቭ ክሊኒካል ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ፣ የጤና መረጃ አያያዝ፣ ድንገተኛ ህክምና ቴክኒሻን፣ ፋርማሲ ቴክኒሻን እና ጤና ኤክስቴንሽን ዘርፎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅትም 377 የዲግሪ ተማሪዎችን እና 2037 የዲፕሎማ ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ 2,414 ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ኮሌጁ 172 መምህራንና 105 የአስተዳዳር ሰራተኞችን ጨምሮ በድምሩ 277 ሰራተኞች ያሉት ሲሆን 38 የመማሪያ ክፍሎችና 13 የሰርቶ ማሳያ ክፍሎች አሉት።

በ8 ወራቱ ውስጥ የትምህርት ዘመኑን አካዳሚክ ካላንደር ማዘጋጀት፣ የኮርስ ድልደላ እና የማስተማሪያ ክፍለ ጊዜ ማውጣት፣ የሰርቶ ማሳያ ክፍሎችን በስታንዳርድ መሰረት ማጠናከር፣ ለተግባር ልምምድ የሚወጡ ተማሪዎች የሎግ ቡክ ዝግጅት እና የፈተና ሂደቶችን ማጠናከር ያሉ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው የተገኙት ውጤቶች የጋራ ጥረት ፍሬ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የተማሪዎች ብቃት ላይ በልዩ ትኩረት መስራት፣ የመምህራን የሙያ ማሻሻያ ስልጠናን ማጠናከር፣ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ማስፋፋት እና ከጤና ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በክልሉ ዞኖች ላይ ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

እንዲሁም የኮሌጁ አገልግሎቶችን በሁሉም ዘርፍ ዲጂታላይዝ በማድረግ ተቋሙን ማዘመን እንዳስፈላጊ ገልፀው በተግባር ልምምድ ዘርፍ ኮሌጁ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለመስጠት ጤና ቢሮው ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ከተግባር ልምምድ አንፃር የሚያስፈልጉ ድጋፎች እንዲደረጉ በመጠየቅ አስተያየታቸውን አቅርበዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የላቀ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት እያደረገ ያለው ጥረት በክልሉ ጤና ቢሮ ተጎበኘ።መጋቢት 1/2018 ሚዛን አማን:​የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ ...
10/03/2026

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የላቀ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት እያደረገ ያለው ጥረት በክልሉ ጤና ቢሮ ተጎበኘ።

መጋቢት 1/2018 ሚዛን አማን:

​የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለውን የመማር ማስተማር ሂደትና የተግባር ማሰልጠኛ ክፍሎችን በሥፍራው ተገኝተው ጎበኙ።

​በጉብኝቱ ወቅት የቢሮ ኃላፊውን ጨምሮ የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ፣ የኮሌጁ ማኒጅመንት አባላት እንዲሁም የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ተገኝተዋል።

​​የቢሮ ኃላፊው አቶ ኢብራሂም ተማም በኮሌጁ የሚገኙ የሰርቶ ማሳያ ክፍሎችንና የተግባር ማስተማሪያ ግብዓቶችን ከተመለከቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሌጁ ተማሪዎች ወደ ሥራው ዓለም ከመሰማራታቸው በፊት በቂ ክህሎትና ተግባራዊ እውቀት እንዲጨብጡ እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

​ኃላፊው አክለውም ጥራትና ብቃት ያላቸውን የጤና ባለሙያዎች በስፋት ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ለክልላችን የጤና ሴክተር ዕድገት ወሳኝ መሠረት ነው ብለዋል።

​ኮሌጁ የንድፈ-ሀሳብ ትምህርቱን ከተግባር ጋር በማቀናጀት ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሰጠው ትኩረት ፣ በሰርቶ ማሳያ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ግብዓቶች ተማሪዎችን ለተጨባጭ የህክምና አገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ ያላቸው ከፍተኛ ፋይዳ አመላክቷል።

በተጨማሪም የመማር ማስተማር ሂደቱን ይበልጥ ለማዘመን የቤተ-መጻህፍት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የማገዝና ዲጂታላይዝ የማድረግ አስፈላጊነት ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

​የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ በበኩላቸው ኮሌጁ በክልሉ ያለውን የጤና ባለሙያ ፍላጎት በበቂ ሁኔታ ለመሙላትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የቢሮው ኃላፊ በቦታው ተገኝተው ያደረጉት ምልከታና የሰጡት ግብረ-መልስ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ትልቅ የሥራ መነሳሳት መፍጠሩንም አክለዋል።

​ይህ ጉብኝት የክልሉን የጤና ሴክተር በሰለጠነ የሰው ኃይል ለማጠናከርና በኮሌጁ እና በጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
‎Website፡ www.mahsc.edu.et
‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
‎Telegram: https://t.me/macohs2023

በቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በተግባር ልምምድ ላይ ያሉ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ያካሄዱት የፅዳት ዘመቻ በፎቶ:
06/03/2026

በቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በተግባር ልምምድ ላይ ያሉ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ያካሄዱት የፅዳት ዘመቻ በፎቶ:

Address

Southwest
Mizan Teferi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mizan Aman College of Health Science-macohs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Mizan Aman College of Health Science-macohs:

Shortcuts

Share