ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት Ortodox

 #በመጽሓፍ ቅዱስ ውሰጥ አሰደንጋጭ ባለ ታሪኮችና ድርጊቶቻቸው❗🙆1. አዳምና_ሔዋን፦ የመጀመሪያዎቹ ሰዎችና በእነርሱ አለመታዘዝ የሰው ዘር ሁሉ በስቃይ መኖሩ።🙆2. አቤልና_ቃኤል፦ ወንድማማቾ...
22/06/2025

#በመጽሓፍ ቅዱስ ውሰጥ አሰደንጋጭ ባለ ታሪኮችና ድርጊቶቻቸው❗🙆

1. አዳምና_ሔዋን፦ የመጀመሪያዎቹ ሰዎችና በእነርሱ አለመታዘዝ የሰው ዘር ሁሉ በስቃይ መኖሩ።🙆

2. አቤልና_ቃኤል፦ ወንድማማቾች፣ በመሥዋዕታቸውና ቃኤል አቤልን በመግደሉ ይታወቃሉ።❗😭

3. ማቱሳላ፦ በጣም ትልቁን የእድሜ ቁጥር የያዘው ሰው (969)።🙆

4. ሄኖክ፦ በ365 ዓመቱ መነጠቁና እስካሁን በሕይወት መኖሩ።❗

5. ኖኅ፦ ከጥፋት ውኃ የሚተርፍበትን መርከብ በመሥራቱ፣ እና የሰው ዘር የቀጠለበት ሰው መሆኑ።❗🙆

6. አብርሃም፦ በእምነቱና በመታዘዙ፤ የግርዛት ሕግን በመቀበሉ።❗🙆

7. ይስሐቅ፦ መሥዋዕት ለመሆንና ለመታረድ ፈቃደኛ የሆነ ታዛዥ ልጅ በመሆኑ።❗

8. ያዕቆብ፦ ለበረከትና ለብኩርና በመታገሉ፣ በአፍቃሪነቱና የ12 ነገደ እስራኤል አባት መሆኑ።❗

9. ዮሴፍ፦ ሕልመኛነቱ፣ ሕልም ፈቺነቱ፣ ታማኝነቱና ያገኘው ሥልጣን።❗

10. ሙሴ፦ የመጀመሪያው የእስራኤል መሪና ሕግ ተቀባይ፣ ሥርዐት ሠሪ።🙆

11. አሮን፦ የሙሴ ወንድምና የመጀመሪያው ሊቀካህን።❗🙆

12. ማርያም፦ የሙሴ ታላቅ እህት፣ ነቢይትና ዘማሪ።❗

13. ኢያሱ፦ ወደ ተስፋይቱ ምድር እስራኤልን ያስገባና ርስት ያከፋፈለ።❗

14. ጌዲዮን፦ በሦስት መቶ ወታደር የምድያማውያንን ሠራዊት ድል በማድረጉ።❗

15. ሳምሶን፦ ፀጉሩ ላይ ባለው ኃይልና በደሊላ መታለሉ።❗

16. ዲቦራ፦ ነቢይትና ፈራጅ።❗

17. ሩት ፦ ሞዐባዊትና የታመነች ሴት❗🙆

18. ሳሙኤል፦ በስእለት የተወለደ የሀና ልጅ፣ የታመነ ነቢይና መስፍን።🙆❗

19. ሳዖል፦ ከብት ፍለጋ በሄደበት ድንገት የተቀባና የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማቱ ንግስና የተወሰደበት የመጀመሪያው የአይሁድ ንጉሥ።❗

20. ዳዊት፦ በዘማሪነቱ፣ በንግስናው፣ በንስሐ ሕይወቱና ጎልያድን በመጣሉ።❗

21. ሰሎሞን፦ በጥበበኛነቱና የመጀመሪያውን የእግዚአብሔር መቅደስ የሠራ በመሆኑ።❗🙆

22. ኤልያስ፦ እስካሁን ያልሞተና የተነጠቀ፣ ሰማይን የዘጋ፣ እሳት ያወረደ ታላቅ ነቢይ በመሆኑ።❗🙆

23. ኤልሳዕ፦ የኤልያስ ደቀመዝሙር፣ ብዙ ተአምራትን ያደረገ።❗🙆
24. ኢዮብ፦ ጻድቅና የመከራ ሰው፤ በትእግስቱ የሚደነቅ ሰው።😭❗

25. መልከ_ጼዴቅ፦ ንጉሥም ካህንም የሆነ፣ ከአብርሃም አስራትን የተቀበለ፣ የኢየሱስ ምሳሌ የሆነ ሰው።😭

26. ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤልና ዳንኤል፦ ታላላቅ ነቢያት ።❗

27. ሆሴዕ፦ የእስራኤል ነቢይና አመንዝራዋን ሴት እንዲያገባ በጌታ የታዘዘ ሰው።❗

28. ዮናስ፦ የዋሁ ነቢይና ከእግዚአብሔር የኮበለለው፣ በዓሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀን ያደረው፣ የጌታ ኢየሱስ ምሳሌ የሆነ ሰው።❗

29. መርዶክዮስ፦ የአስቴር አጎትና ታላቅ የእምነት ሰው፣ የመጽሐፈ አስቴር ጸሐፊ።❗🙆

30. ነህምያ፦ የእስራኤልን ቅጥር የሠራ ታላቅ መሪ።❗🙆

31. ዕዝራ፦ አንባቢ፣ የሕጉ ተርጓሚና ፀሐፊ።❗

32. ሎጥ፦ የአብርሃም የወንድም ልጅ፣ ከሰዶምና ከገሞራ ጥፋት ያመለጠ፣ ከልጆቹ አሞንና ሞዐብን የወለደ።🙆❗

page follow,like,share በማድረግ ይተባበሩ።❗

 #ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ የሚገባን ነጥቦች❗🙋❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው። ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ• 66 መጽሐፍት• ...
22/06/2025

#ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ የሚገባን ነጥቦች❗🙋

❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
• 66 መጽሐፍት
• 1,189 ምዕራፎች
• 31,173 አንቀፆች
• 810,697 ቃላት
• 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።

❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
• በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
• በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
• አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።

❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።

❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።

❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል።

❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
ይኸውም፦
• መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት።

• የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።

• የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ
"ድመት" ብቻ ናት።
ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
ስለ እምነት 500 ጊዜ
ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።

,
..✍️
page follow ያድርጉ❗

“ሴት ሆይ!”**** ****1) በምንም ምክንያት ባልሽ ላይ ጮክ ብለሽ አትናገሪ፡፡ ምክንያቱም ባል ላይ መጮህ የመናቅ ምልክት ነዉና፡፡ (ምሳሌ 15፣1)…2) የባልሽን ድክመት ለቤተሰቦችሽም ...
23/05/2025

“ሴት ሆይ!”
**** ****
1) በምንም ምክንያት ባልሽ ላይ ጮክ ብለሽ አትናገሪ፡፡ ምክንያቱም ባል ላይ መጮህ የመናቅ ምልክት ነዉና፡፡ (ምሳሌ 15፣1)

2) የባልሽን ድክመት ለቤተሰቦችሽም ሆነ ለጓደኞችሽ ከቶም አትግለጪ፡፡ ምክንያቱም መልሶ ወዳንቺ ነገሩ ይመጣልና፡፡ አንቺ የእያንዳንዳችሁ ጠባቂ ነሽ፡፡ (ኤፌ 5፣12)

3) ከባልሽ ጋር ስትነጋገሪ የተለየ የአካል እንቅስቃሴንና ምልክትን አትጠቀሚ፡፡ ባልሽ እነዚያን እንቅስቃሴዎችሽን እንዴት እንደሚተረጉም አታዉቂም፡፡ ኃይለኛ እና ቁጡ ሴት ደስተኛ ቤት አይኖራትም፡፡ (ምሳሌ 15፣13)

4) ባልሽን በፍጹም ከሌሎች ወንዶች ጋር አታመሳስይዉ፡፡ የሌሎች ወንዶች ህይወት ምን እንደሆነ ከባልሽ በቀር አታዉቂም፡፡ ባልሽን ከሌሎች ጋር በማነጻጸር በራስ መተማመኑን ከነጠቅሽ ላንቺ ያለዉን ፍቅር ከልቡ ያጠፋዋል፡፡

5) የባልሽን ጓደኞች ህመም አታስታሚ ምክንያቱም ትጠያቸዋለሽና፡፡ የነሱን ህመም ሊያስታም የሚገባዉ ራሱ ባልሽ ሊሆን ይገባል፡፡ (ምሳሌ 11፣22)

6) ባልሽ ወዶሽ እንዳገባሽ እንዳትረሺ፡፡ አንቺ ሰራተኛዉ ወይም ሌላ አየደለሽምና የሚስትነት ኃላፊነትሽን ተወጪ (ዘፍ 2፣24)

7) ማንንም ባልሽ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አትፍቀጂ፡፡ሌሎች ያሻቸዉን ሊያደርጉ ይችላሉ ባልሽ ግን ያንቺዉ ኃላፊነት ነዉ፡፡ (ኤፌ 5፣33)

😎 ባልሽ ባዶ እጁን ወደቤት ቢመጣ አትዉቀሺዉ ይልቁንም አረታችዉ፡፡

9) ከቶም አባካኝ አትሁኚ፡፡ የባልሽ ላብ የማያባክኑት እጅግ ዉድ ነዉና፡፡

10) ለግብረ ስጋ ግንኙነት በፍጹም ያመመሽ በማስመሰል ባልሽን አትከልክይዉ፡፡ ባልሽ እስከ ፈለገዉ ሁኚለት፡፡ ለባል የግብረ ስጋ ግንኙነት መሰረታዊ ነዉ፡፡ አንቺ ግን በተደጋጋሚ ከለከልሺዉ ከሌላ ሴት ጋር እንዲወሰልት በር ትከፍቺለታለሽ፡፡ ወንድ በፍፁም የስጋ ግንኙነትን ለረጅም ጊዜ ተቋቁሞ መዝለቅ አይችልምና፡፡ (መኃልይ 7፣12)

11) ባልሽን ከዚህ ቀደም ከሌላ ወንድ ጋር (ከቀድሞ ፍቅረኛሽ ጋር) ግንኙነት አድርገሽ ምታዉቂ ከሆነ ግንኙነት ካደረግሺዉ ሰዉ ጋር የሱን የስጋ ግንኙነት በፍጹም አታነጻጽሪ፡፡ የሄ ትዳርሽ በቀድሞ ግንኙነትሽ ከቶ አይካካስምና፡፡ (መኃልይ 5፣9)

12) ለባልሽ በአደባባይ መልስ አትስጪዉ፡፡ እሱ በአደባባይ ተናግሮሽ ቢሆንም እንኳን ነገሩን በልብሽ ያዥዉ፡፡ (ምሳ 31፣23)

13) ባልሽ ላይ በልጆቻችሁ ፊት አትቆጪ ወይም አትቋቋሚዉ፡፡ ብልህ ሴት ይህን አታደርግምና፡፡ (ኤፌ 4፣31)

14) ባልሽ በሚሰነዳዳበት ጊዜ ታሰማምሪዉ እና ሚያስፈልገዉን ታሟይለት ዘንድ አትዘንጊ፡፡ (ምሳ 12፣4)

15) ጓደኞችሽ ለባልሽ እጅግ እንዲቀርቡት አታድርጊ፡፡

16) በመዋቢያ እና በመጣጠቢያ ክፍልሽ ከቶ አትቻኮይ፡፡ ዉበትሽን ጠብቂ፡፡ ባልሽ በሌሎች ቆነጃጅት ተከቦ ሊዉል ስለሚችል እንዳይሰናከል ሁሌም ዉብ ሁኚ፡፡ (1ሳሙ 25፣3)

17) ወላጆችሽ ወይም ቤተሰቦችሽ ወይም ጓደኞችሽ የህይወትሽ ወሳኝ እንዲሆኑ አትፍቀጂላቸዉ፡፡ እነሱ ስላንቺ ትዳር ዉሳኔ እንዲሰጡ አትጠብቂያቸዉ፡፡ ማድረግ ካለብሽ ካለማንም ጣልቃ ገብነት በራስሽ አድርጊዉ፡፡ (ሉቃ 21፣16)

18) ገንዘብን የፍቅርሽ መሰረት አታድርጊዉ፡፡

19) ባሎች ትኩረት የምትሰጥንና በትኩረት የምታደምጥን ሚስት እንደሚፈልጉ በፍጹም እንዳትዘነጊ፡፡ ለሱ የሚሆን ጊዜ በፍጹም እንዳታጪ፡፡ መልካም ንግግር የደስተኛ በቶች መሰረት ነዉ፡፡ (ገላት 6፣9)

ከእፎይ🙏

"መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሳያውቀው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይወሰንና ሳይፈቀድ የትኛውንም ቋሚ ንብረት በማስያዝ ብድር መበደር የተከለከለ ነው።ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት ፱/፳፻፲...
19/05/2025

"መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሳያውቀው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይወሰንና ሳይፈቀድ የትኛውንም ቋሚ ንብረት በማስያዝ ብድር መበደር የተከለከለ ነው።
ቅዱስ ሲኖዶስ

ግንቦት ፱/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
"መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሳያውቀው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይወሰንና ሳይፈቀድ የትኛውንም ቋሚ ንብረት በማስያዝ ብድር መበደር የተከለከለ ነው።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ሕንጻና የብድር ውል በተመለከተው በያዘው አጀንዳ ቁጥር ፯ በስፋት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል።
በሥራ ሂደት የተፈጠሩትን የሕግና የመዋቅር ጥሰቶች በማረምና በማስተካከል የቅድስት ቤተክርስቲያንን ጥቅምና ክብር በማስጠበቅ ሁሉም ተቋማት ሕግንና መመሪያን ጠብቀው እንዲሠሩ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፡-
1. በዩኒቨርሲቲው መዋቅራዊ አስተዳደር መሠረት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም ሆነ የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሥራ ተጠሪነቱ ለዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ እንደመሆኑ መጠን ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ የሥራ ዕቅዱን ለሥራ አመራር ቦርድ አቅርቦ በማስገምገም ካጸደቀ በኋላ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቅርቦ ሲፈቀድ ወደ ትግበራ መግባት ሲገባው የሥራ አመራር ቦርዱም ሆነ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ባላጸደቀው ፕሮጀክት በቋሚ ሲኖዶስም ሆነ በምልዓተ ጉባኤ ሳይፈቀድለት ከፍተኛ ብድር መበደሩ ተገቢ ስላልሆነ ዩኒቨርሲቲው ከዓባይ ባንክ አክስዮን ማኅበር ጋር የገባው የብድር ውል ስምምነት እንዲቋረጥ፤

2. ዩኒቨርሲቲው ከዓባይ ባንክ አክስዮን ማኅበር ጋር በገባው የውል ስምምነት መሠረት በመጀመሪያ ዙር የወሰደውን ብድር ብር 166‚045‚410.91 (አንድ መቶ ስልሳ ስድስት ሚሊዮን አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ዐሥር ብር ከዘጠና አንድ ሣንቲም) በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ አድርጎ በብድር ማስያዣነት ያስያዛቸውን የሁለቱንም ሕንጻዎች እግድ በማስነሳት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎችን በመረከብ ተመላሽ እንዲያደርግ፤

3. ዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ሕንጻ መገንባቱ የሚደገፍና ለዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ በመሆኑ የጀመረውን የማስፋፊያ ሕንጻ ግንባታ ከውስጥ ገቢው ላይ በጀት በመመደብ ግን

ሰይጣን ለሦስት አረጋውያን አባቶች ተገልጦ እንዲህ አላቸው፡ "ካለፈው ዘመን የሆነን ነገር የመለወጥ ሥልጣን ብሰጣችሁ... ምንን ትለውጡ ነበር?"1. የመጀመሪያው አባት በታላቅ መንፈሳዊ ቅናት...
19/05/2025

ሰይጣን ለሦስት አረጋውያን አባቶች ተገልጦ እንዲህ አላቸው፡ "ካለፈው ዘመን የሆነን ነገር የመለወጥ ሥልጣን ብሰጣችሁ... ምንን ትለውጡ ነበር?"

1. የመጀመሪያው አባት በታላቅ መንፈሳዊ ቅናት እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- "አዳምና ሔዋን በኀጢአት እንዳይወድቁ እከለክልህ ነበር፤ በዚህም የሰው ልጅ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር እንዳይለይ አደርግ ነበር።"

2. ሁለተኛው፣ በምሕረት የተሞሉ አባት እንዲህ አሉ፡- "አንተ ከልዑል እግዚአብሔር መንገድ እንዳትስት እከለክልህ ነበር፤ በዚህም ራስህን ለዘለዓለማዊ ኩነኔ እንዳትዳርግ አደርግ ነበር።"

3. ነገር ግን ሦስተኛው፣ ከሁሉም ይልቅ በየዋህነት የሚኖሩት አባት፣ ለሰይጣኑ መልስ አልሰጡም። ይልቁንም፣ በጉልበታቸው ተንበርክከው፣ ትእምርተ መስቀልን አማትበው እንዲህ አሉ፡- "ከአንተ ከርጉም ሰይጣን በአምላኬ በእግዚአብሔር እጠበቃለሁ!" ብለውም ከመዝሙረ ዳዊት የድኅነት ቃል አነበቡ። ሰይጣኑም በድንጋጤ ጮኾ ከዚያች ሰዓት የተሰወረ ሆነ።

የመጀመሪያዎቹ ሁለት አረጋውያን አባቶችም ተደንቀው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡- "አባታችን፣ ለምንድነው እንዲህ ያደረጉት?"

እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፡-
"በመጀመሪያ፣ ጠላታችን ሰይጣንን እንዴት እንደምናሸንፈው መንገዱን እያወቅን ከእርሱ ጋር በውይይት ጊዜያችንን ማጥፋት የለብንም።
ሁለተኛ፣ በምድር ላይ ያለፈውን መለወጥ የሚችል አንድም ፍጡር የለም።
ሦስተኛ፣ የሰይጣኑ ዓላማ እኛን መፈተን ሳይሆን፣ ልባችንን ካለፈው ነገር ጋር አስሮ የወደፊቱን ሕይወታችንን ለንስሐና ለመልካም ሥራ እንዳንጠቀምበት እግዚአብሔር ከሰጠን ከዚህ የአሁኑ ወርቃማ ጊዜ ሊያዘናጋንና ሊያስት ነው።"

ኣዎ! ያለፈው ነገር፡ በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ የታለፈ ነውና በጸጸት አንዋጥበት። የሚመጣውም ዘመን፡ በእግዚአብሔር ጥበብና አምላካዊ ዕውቀት የተያዘ ነውና በአጉል ተስፋና ፍርሃት አንጨነቅ። አሁን ያለንበት ጊዜ ግን፡ በእጃችን የተሰጠን፣ ለንስሐ፣ ለጸሎትና ለመልካም ምግባር ልንተጋበትና ለሰማያዊ መንግሥት ልንዘጋጅበት የሚገባን ውድ ጊዜ ነው።

እወዳችኋለሁ
(06/09/2017 ዓ.ም )
©️ተዋነይ - Tewanay

👉ዕጣን ምንድነው? ለምን ይጨሳል? መቼ ተጀመረ?መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል      #ሼር                                ✍️✍️✍️✍️ዕጣን በበረሃ ከሚበቅል እንጨት ወይም ዛፍ...
03/04/2025

👉ዕጣን ምንድነው? ለምን ይጨሳል? መቼ ተጀመረ?
መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል #ሼር
✍️✍️✍️
✍️ዕጣን በበረሃ ከሚበቅል እንጨት ወይም ዛፍ የሚለቀም ሙጫ ነው:: በቤተ መቅደስ እንዲታጠን በእግዚአብሔር ታዘዘ።

✍️እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው :- ‘’ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫም ውሰድና ….. በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው ከዚያም አንተን በምገናኝበት በመቅደሱ ውስጥ በታቦቱ ፊት ታኖረዋለህ:: እርሱም የቅዱሳን ቅዱስ ይሁንላችሁ::’’ ስለዚህ በሙሴ ዘመን ተጀመረ::

✍️ስለ እጣን የመፅሀፍ ቅዱስ ማስረጃ:-
ዕጣን የምስጋና እና የእርገተ ጸሎት ምሳሌ ነው፡፡ ከጸሎታችንም ጋር ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል፡፡ “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ ራእ. 8:4፡፡

✍️ነቢዩ ዳዊት ስለ ዕጣን እንዲህ ብሏል ”አቤቱ ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደሰርክ መስዕዋት ትሁን ::’’ መዝ 140:2) ጌታችን ሲወለድ ሰብአ ሰገል ከገበሩት ውስጥ አንዱ ዕጣን ነው:: ማቴ 2:11

✍️‘’በዕጣንም ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በዉጭ ቆመዉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ‘’ሉቃ 1:10
✍️‘’መጽሀፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንሰሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ: እያንዳዳቸዉም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ፡፡’’ራእ 5:8

✍️‘’ሌላም መለአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊአዊ አጠገብ ቆመ: በዙፋኑም ፊት ባለዉ በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረዉ ብዙ እጣን ተሰጠዉ::’’ ራእ 8:3ፍርድህን ለያዕቆብ: ህግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ: በፊትህ ዕጣንን: በመሰዊያህም የሚቃጠል መስዕዋት ይሠዋሉ፡፡’’ዘዳ 33:10
‘’ጽንሃ’’ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ ወይም ማጠኛ ነው።

✍️ሦስት ሰንሰለቶች አሉት:: ሰንሰለቶቹ ሶስት መሆናቸው የሚስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው። በሰንሰለቶቹ ላይ ቢያንስ አስራ ሁለት (12) ቢበዛም ሃያ አራት (24) ሻኩራዎች ይኖሩታል።

✍️‘’ሻኩራ’’ ማለት ሶስቱ ሰንሰለቶች ላይ ያሉት ክብ ነገሮች ናቸው::
✍️የሻኩራዎቹ ቁጥር አስራ ሁለት (12) መሆኑ የሐዋሪያት ምሳሌ ነው።

✍️ሃያ አራት (24) መሆኑ ደግሞ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው ።
✍️ከስሩ እጣኑ የሚቀመጥበት ሙዳይ የመሰለ ክፍል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሲሆን: መለኮት ከሥጋዋ ሥጋ ነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ያመለክታል።
✍️ፍሙ የጌታችን የመለኮትነቱ ምሳሌ ሲሆን እጣኑ እንደሚቃጠልና መዓዛው ሁሉን እንደሚያውድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ብዙዎች ኃጢያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ አቅርቦ ዓለሙን ሁሉ ማዳኑን ያሳያል ።

✍️የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት: የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን ምልጃ አይለየን::

  👏የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቤተክርስቲያን እንዳትፈርስ ዛሬ በዋለው ችሎት  ውሳኔ አስተላልፏል  ይህቺ ቤተክርስቲያን በዳውሮ ሀገር ስብከት በታርጫ ዙርያ ወረዳ የምትገኝ ስድስት  አባወራዎች ብ...
06/02/2025

👏
የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቤተክርስቲያን እንዳትፈርስ ዛሬ በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል

ይህቺ ቤተክርስቲያን በዳውሮ ሀገር ስብከት በታርጫ ዙርያ ወረዳ የምትገኝ ስድስት አባወራዎች ብቻ ያሉባት የገጠር አጥቢያ የቦዲ ኢየሱስ የእኛው ቤተክርስቲያያናችን ነች !!

ይህችን ቤተከርስቲያን የወረዳው መንግስት በራሳችሁ ወጭ አፍርሳችሁ ቦታውን ለትምህርት ቤት ግንባታ ፈልገናል አስርክቡል ታቦታችሁን አውጡልን የተባለች የእኛው ቤተመቅደስ ነች !!

በዚህች ቤተክርስቲያን ለአገልግሎት ስፈልግ ውስን ቅን የቤተክርስቲያን ሰወች በራሳቸው ወጭ ከሌላ ቦታ ማስቀደሻ እየለገሳት የምትገለገል የእኛው ቤተ መቅደሳችን ነች ።

የዚህች ቤተክርስቲያን ጉዳይ በከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ቆይቶ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ዛሬ ለቤተክርስቲያን ተወስኗል !!

Via------ Lije Tesfu - ልጅ ተስፉ

"እንዘ ተሐቅፊዮ ለህፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ"ቀይም ነጭም አበባ የሆነ ልጅሽ እንደታቀፍሽው ወደኛ ነይ🙏
27/10/2024

"እንዘ ተሐቅፊዮ ለህፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ"

ቀይም ነጭም አበባ የሆነ ልጅሽ እንደታቀፍሽው ወደኛ ነይ🙏

በአሚነ ዚአሃ ለማርያም ንገኒ(በእውነት ለእሷ ለማርያም እንገዛለን)ሰኔ 21(፳፩)ህንፀተ ቤታ።እንኳን አደረሰን።መልካም በዓል።
27/06/2024

በአሚነ ዚአሃ ለማርያም ንገኒ

(በእውነት ለእሷ ለማርያም እንገዛለን)
ሰኔ 21(፳፩)ህንፀተ ቤታ።እንኳን አደረሰን።

መልካም በዓል።

ሆሣዕና ማለት"ሆሣዕና በአርያም"እየተባለ ከሚዘመረው ከቅዱስ ያሬድ ዜማ የተወሰደ ሲሆን ሆሣዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሆሻዕናህ"የሚል ሲሆን ትርጉሙም"እባክህ አሁን አድን"ማለት ነው።   ...
28/04/2024

ሆሣዕና ማለት"ሆሣዕና በአርያም"እየተባለ ከሚዘመረው ከቅዱስ ያሬድ ዜማ የተወሰደ ሲሆን ሆሣዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሆሻዕናህ"የሚል ሲሆን ትርጉሙም"እባክህ አሁን አድን"ማለት ነው።

ሆሳዕና🤲

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየአቤቱ ፀሎትየን ስማኝ ጩሆቴም በፊት ይድረስ🤲
11/03/2024

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ

አቤቱ ፀሎትየን ስማኝ ጩሆቴም በፊት ይድረስ🤲

ሁሉንም አጥቸ አንድ አንተን ላግኝህ፥ዋናየ ነህና ብዙ ማተርፍብህ🤲
06/03/2024

ሁሉንም አጥቸ አንድ አንተን ላግኝህ፥ዋናየ ነህና ብዙ ማተርፍብህ🤲

Address

Lif
Mojo

Telephone

+251910860365

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share