ሞጣ Poly Technic ኮሌጅ/Motta Poly Technic College

ሞጣ Poly Technic ኮሌጅ/Motta Poly Technic College ሞጣ ፖሌቴክኒክ ኮሌጅ

ማስታወቂያ
10/08/2026

ማስታወቂያ

በሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች ለተማሪዎች የተደረገ የበጎ አድራጎት ድጋፍ! ✨የኮሌጃችን ማህበረሰብ ዛሬ በ13/11/5018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራውን ካሳረፈ በኋላ፣...
21/07/2026

በሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች ለተማሪዎች የተደረገ የበጎ አድራጎት ድጋፍ! ✨
የኮሌጃችን ማህበረሰብ ዛሬ በ13/11/5018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራውን ካሳረፈ በኋላ፣ በከተማችን ለሚገኙና የጽህፈት መሣሪያ እጥረት ለሚገጥማቸው ህጻናት ተማሪዎች ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የውይይትና የገቢ ማሰባሰብ መርሃ-ግብር አካሂዷል።

በዕለቱ በሰራተኞቻችን ታላቅ ቅንነትና ተነሳሽነት የሚከተሉት ድጋፎች
ተገኝተዋል፦
የጽህፈት መሣሪያዎች፦ 2 ደርዘን ባለ 32 ሉክ ደብተር፣ 4 ደርዘን ባለ 50 ሉክ ደብተር፣ 6 እስክሪብቶ እና 1 ፓኮ እርሳስ ለመስጠት ቃል ተገብቷል።
የገንዘብ ድጋፍ፦ በዕለቱ 3,660.00 ብር በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበ ሲሆን፣ 11,919.00 ብር ቃል ተገብቷል።

ይህ በጎ ተግባር በዕለቱ በመድረኩ ላይ ባልተገኙ አሰልጣኞችና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፎ ይበልጥ እያደገ እንደሚሄድና የድጋፍ መጠኑ ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።
ከስድስቱም ቀበሌዎች ለተውጣጡ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት የነገ ተስፋቸውን ለማገዝ የምታደርጉት ይህ ተግባር ለሁላችንም ኩራት ነው—የተቋማችን ሰራተኞች በሙሉ ለዚህ ክቡር ተግባራችሁ ምስጋና ይገባችኋል!
አንዱዓለም የስጋት የኮሌጁ ዲን

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደማቅ የሰልጣኞች ምርቃት ማግስት .....🌱 የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አረንጓዴ አሻራ እና የልማት ስራዎች! 🍋☕️የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ13/11/2018 ዓ.ም በኮሌ...
20/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደማቅ የሰልጣኞች ምርቃት ማግስት .....
🌱 የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አረንጓዴ አሻራ እና የልማት ስራዎች! 🍋☕️
የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ13/11/2018 ዓ.ም በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው 1.5 ሄክታር መሬት ላይ 1000 የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር በስኬት አካሂዷል።

በዕለቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በድምሩ 64 የኮሌጁ አሰልጣኞች እና አስተዳደር ሰራተኞች (58 ወንዶች እና 6 ሴቶች) በከፍተኛ መነሳሳት ተሳትፈዋል።

የተተከሉ የፍራፍሬ ዓይነቶችም፦ ሎሚ፣ ብርቱካን እና ቡና ሲሆኑ፣ ተከላው በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

የተተከሉ ችግኞች እንዳይጠፉና ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማድረግ እያንዳንዱ አሰልጣኝ እና የአስተዳደር ሰራተኛ በአማካኝ 20 የሚሆኑ የተለያዩ የፍራፍሬ ተክሎችን በኃላፊነት ተረክቦ እኔዲኔከባከብ በሀላፊነት ተሰጥቶታል።

ሰራተኞቹ ፍራፍሬዎች በተተከሉባቸው ቦታዎች ላይ እንደ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ቲማቲም፣ ቀይ ስር እና የመሳሰሉ ቀሊል የጓሮ አትክልቶችን በመትከል ራሳቸውን እያገዙ ይገኛሉ።

ባለፈው ክረምት በ40 ፈቃደኛ ሰራተኞች የተጀመረው ይህ ውጤታማ ተግባር፣ በዚህ ዓመት 24 አዳዲስ ሰራተኞች መሬት ተረክበው በመቀላቀላቸው በአጠቃላይ የ64 ሰራተኞች የጋራ የልማት እንቅስቃሴ ለመሆን በቅቷል።
ይህም የተተከሉ አትክልቶች ሳይደርቁ እንዲጸድቁና ዘላቂ እንዲሆኑ ለማድረግ አመችና አማራጭ የሌለው ስልት ሆኖ ተገኝቷል።
"ለአረንጓዴና ምርታማ ግቢ በጋራ እንሰራለን!"
የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም ሰልጣኞች በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ፤ የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ስልጠናቸውን በጥራት ያጠናቀቁ ወ 75 ሴ 140 ድ 215 ሰልጣኞቹን...
18/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም ሰልጣኞች በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ፤
የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ስልጠናቸውን በጥራት ያጠናቀቁ ወ 75 ሴ 140 ድ 215 ሰልጣኞቹን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባና የትምህርትና ስልጠና ቦርድ ሰብሳቢ፣ የቦርድ አባላት፣ የሁለቱም ወረዳ የስራ አመራሮች፣ አጋር ድርጅቶች፣ ውጤታማ ኢንተርፕራይዞች፣ ተመራቂዎችና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ። በታላቅ ድምቀት በተካሄደው በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ሰልጣኞች በኮሌጁ በቆዩባቸው ጊዜያት የቀሰሙትን የክህሎትና የስራ ፈጠራ ስልጠና ተጠቅመው ራሳቸውን ችለው ሌላውን ስራ የሚቀጥሩ ባለቤቶች እንዲሆኑና የስራ ፈላጊነት ሰለባ እንዳይሆኑ ለተመራቂዎች አደራ ተብሏል።
የኮሌጁን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የኮሌጁ ዲን አቶ አንዱዓለም፤ ከትምህርትና ስልጠና፣ ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን፣ ከመሰረተ ልማት፣ ከተቋም ግንባታ እንዲሁም ከፋይናንስ አሰራርና ከውስጥ ገቢ አቅም ማሳደግ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትንና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር አስረድተዋል። በዕለቱ ከተመረቁት 215 ሰልጣኞች መካከል የሴት ተመራቂዎች ቁጥር መጨመሩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለሴቶች የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ከተመራቂዎቹ ውስጥ 170 (79.07%) የሚሆኑት በሙያ ብቃት ምዘና (COC) ተመዝነው የበቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 45 ምሩቃንም በቀጣይ በሚሰጠው ምዘና ብቁ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ዲኑ አክለውም ኮሌጁን ከዘመኑ ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ በእርጅና ምክንያት የፈረሱ ወርክሾፖች ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲጠገኑ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንዲሰሩ እንዲሁም የመሰብሰቢያ አዳራሽና የኢንኩቤሽን ማዕከል እንዲገነቡ ጠይቀው፤ ተቋሙን ማሳደግ የጋራ ሀብትና ኃላፊነት በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ፣ ወረዳው፣ ባለሀብቱና ማኅበረሰቡ በጋራ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ተመስገን ዘዉዴ ባስተላለፉት መልዕክት ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ በዲኑ ለቀረቡት የመሰረተ ልማትና የተቋም ግንባታ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል። ከንቲባው ኮሌጁ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን አሸናፊም እንዲሆን አስተዳደራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ከመግባታቸውም በላይ፣ እነዚህን የልማት ጥያቄዎች ሌሎች የሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች የልማት አካላትና አመራሮች በኃላፊነት ወስደው እንዲደግፉና ምሩቃኑን በማገዝ ረገድ የየድርሻቸውን እንዲወጡ ጥብቅ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም ለተመረቁ ሰልኞች የስራ ዕድል የፈጠሩ የከተማዋን ድርጅቶች በእጅጉ አመስግነው፣ ሌሎችም ይህንን በጎ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
ከንቲባው አክለውም፥ መንግስት ባለው ውስን መዋቅር ሰራተኛ መድቦ የሚያሰራ ቢሆንም፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በባህሪው ተቀጣሪነትን የማያበረታታና ራስን መቻል ላይ ያተኮረ በመሆኑ፣ ተመራቂዎች ይህንን ተጨባጭ እውነት ተገንዝበው ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ የራሳቸውን የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ባለቤቶች እንዲሆኑ አሳስበዋል።
በታላቅ ድምቀትና ደስታ በተጠናቀቀው በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ማጠቃለያ ላይ፣ በዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የኮሌጁ አሰልጣኞችና የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍን በአግባቡ ተቀብለው ለተገበሩ ኢንተርፕራይዞች፣ ኮሌጁን በቅርበት ለደገፉ አጋር አካላትና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች የእውቅናና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ስልጠናቸዉን ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን ሀምሌ 11/2018ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ያስመርቃልተመራቂዎች በሙሉ "እንኳን ደስ አላችሁ!"Congratulati...
15/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ስልጠናቸዉን ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን ሀምሌ 11/2018ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ያስመርቃል
ተመራቂዎች በሙሉ "እንኳን ደስ አላችሁ!"
Congratulation!
"በእውቀትና በክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል ለሀገር ብልጽግና እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር!"

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ፤የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ እና የ90 ቀናት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ። (ሐምሌ 07 ቀን 2018 ዓ.ም) የሞ...
14/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ፤የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ እና የ90 ቀናት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።
(ሐምሌ 07 ቀን 2018 ዓ.ም)
የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ያለፈውን በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ለመገምገም እና የአዲሱን በጀት ዓመት የሥራ አቅጣጫ ለመቀየስ ያለመ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የትውውቅ መድረክ አካሄደ።

የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ
የኮሌጁ ዲን በሆኑት በአቶ አንዱአለም ይስጋት አማካኝነት ባለፈው በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና የልማትና የሥልጠና ተግባራትን ያካተተ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል።
በሪፖርቱ ላይ በዋናነት ትኩረት የተደረገባቸውና የተገመገሙት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

የመደበኛና አጫጭር ሥልጠናዎች አሰጣጥ እና የሰልጣኞች ቅበላ አፈፃፀም፣

የሰልጣኝ የቁጠባ ባህል ማሳደግ፣

የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ የትብብር ሥልጠናዎች እና የማሽን ጥገና ሥራዎች፣

የኮሌጁን የቴክኒክና ሙያ ተደራሽነት የሚያሳዩ የ2017 ዓ.ም የምሩቃን የሥራ ስምሪት ሁኔታ፣

የአካባቢውን ማኅበረሰብና ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ የተከናወኑ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት፣

የኮሌጁን ሀብት በአግባቡ ለመምራት የተከናወኑ የግዥ፣ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር፣ የሰው ሀብት ልማት እንዲሁም የውስጥ ኦዲት ሥራዎች፣

የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር የተከናወኑ የአገልግሎት አሰጣጥና የቅሬታ ሰሚ ተግባራት።

የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ እና የ90 ቀናት ዕቅድ
የኮሌጁ ዲን አቶ አንዱአለም ያለፈውን ዓመት አፈፃፀም በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ፣ በአዲሱ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ምዕራፍ ሊተገበር የታለመውን የ90 ቀናት የተቀናጀ የሥራ ዕቅድ እና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን ለመድረኩ ተሳታፊዎች አስተዋውቀዋል።

ዕቅዱን መሠረት በማድረግ ከመድረኩ ተሳታፊዎች፣ ከቡድን መሪዎችና ከሥልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች የተለያዩ ገንቢ ሐሳቦች፣ የሥራ አጋዥ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የማጠቃለያ መልዕክት
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ አንዱአለም ይስጋት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዲኑ በንግግራቸው፦

"ባለፈው በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በአዲሱ በጀት ዓመት በማረም፣ ኮሌጃችንን የተሻለ ለማድረግ ሁላችንም በቅንጅትና በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅብናል"

በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻም መድረኩ በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙነት

13/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፕሮጀክትን መሠረት ያደረጉ ስልጠናዎችን በመስጠት ሰልጣኞችን የሙያ ኮሌጁን ደግሞ የውበት ባለቤት እያደረገ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት በኮንስትራክሽን የስልጠና ዘርፍ እየተገነባ የሚገኘው ፋውንቴን ከዚህ ደረጃ ደርሷል፡፡

10/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኢንደስትሪያል ስልጠና ክፍል በ2018 ዓ.ም በአሰልጣኝ ልመንህ ወንዴ የተሰራ እና የተሸጋገረ ‹‹Printed circuit board holder with lamp የኤሌክትሮኒክስ ሰርኪዩት መያዣ ከማብሪያ/ማብራሪያ መብራት ጋር ››ቴክኖሎጅ፡፡
ይህም ቴክኖሎጅ (Dc voltage dublet የቀጥታ የኤሌክትሪክ ፍሰት (DC) ቮልቴጅ እጥፍ አድራጊ» ወይም «የዲሲ ቮልቴጅ እጥፍ ማድረጊያ ሰርኪዩት)(,gvolte solare battery charger የፀሐይ ብርሃን ባትሪ ቻርጀ ) ያካተተ ነው፡፡
ቴክኖሎጅው በሞጣ ከተማ በአቶ ገበያው አብየ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ዘርፍ ከተሰማራ ኢንተርፕራይዝ ላይ ተሸጋግሯል፡፡

07/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በብረታ ብረት ስልጠና ክፍል በ2018 ዓ.ም በአሰልጣኝ አብዱ ጋሻው የተሰራ የተሸጋገረ ‹‹ክብ ፌሮ በማጠፊያ ›› ቴክኖሎጅ፡፡
ቴክኖሎጅው በሞጣ ከተማ በአቶ እንድሪስ ሙሀመድ በብረታብረት ዘርፍ ከተሰማራ ኢንተርፕራይዝ ላይ የተሸጋገረ ነው፡፡
ክብ ፌሮ በማጠፊያ ቴክኖሎጅ፡-
በቀላሉ ፌሮን ክብ አድርጎ ለማጠፍ የሚያስችል ሲሆን ጊዜንና ጉልበትን የሚቆጥብ ፤በመዶሻ መቀጥቀጥን የሚያስቀር እና በፈለግነው ዲያሜትር መጠን የሚጠቀልል ነው፡፡

06/07/2026

የሞጣ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በልብስ ስፌት ስልጠና ክፍል በ2018 ዓ.ም በአሰልጣኝ ወ/ሮ እመቤት ሞላ የተሸጋገረ ‹‹የልብስ ስፌት መፈለልቀቂያ እና የልብስ ማቀዝቀዣ ›› ቴክኖሎጅ፡፡
ቴክኖሎጅው በሞጣ ከተማ በአቶ አንደበት አበበ በልብስ ስፌት ዘርፍ ከተሰማራ ኢንተርፕራይዝ ላይ የተሸጋገረ ነው፡፡
የልብስ ስፌት መፈለልቀቂያ ቴክኖሎጅ፡-
ልብስ ሰፊዎች በሚሰፉበት ጊዜ የስፌት መገጣጠሚያ ቦታዎች እንዳይጨማደዱ ለማድረግ በጥፍራቸው ይጠቀሙ ስለነበር በእጃቸው እና በልብሱ ላይ ጉዳት ይደርስ ነበር፡፡የልብስ ስፌት መፈለልቀቂያ ቴክኖሎጅ ይህንን ጉዳት ቀርፏል፡፡
የልብስ ማቀዝቀዣ ቴክኖሎጅ፡-
ልብስ በሚተኩሱበት ጊዜ ጨርቁ በሙቀት የመቃጠልና የመበላሸት ችግር ያጋጥም ነበር፡፡የልብስ ማቀዝቀዣ ቴክኖሎጅ ልብሱ እንዲበርድ በማድረግ ይህንን ጉዳት ያስቀራል፡፡

Address

Motta

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሞጣ Poly Technic ኮሌጅ/Motta Poly Technic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share