05/09/2026
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት የማስተርስ ድግሪ ተማሪዎቹ “Plagiarism and Academic Integrity in the AI Era’’ በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠና ሰጠ፡፡
***************************
(ነሃሴ 29 /2018 ዓ.ም)
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት የማስተርስ ድግሪ /ሁለተኛ ድግሪ/ ተማሪዎቹ “Plagiarism and Academic Integrity in the AI Era’’ በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማም የሌሎች ሰዎችን የምርምር ስራ/ፅሁፍ/ ሙሉ በሙሉ ወስዶና የራስ ስራ አስመስሎ ማቅረብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊከሰት የሚችል ጉዳይ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥን አላማ ያደረገ ስልጠና ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ እንዳሉት በአሁን ወቅት በሀገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ችግር ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሰውን የምርምር ፅሁፍ/ስራ/ እንደ የራስ ስራ አድርጎ ማቅረብ ፣የአንድን የምርምር ስራ ውጤት በራስ ጥረት እንደመጣ የራስ ሃሳብ የራስ ግኝት አድርጎ ማቅረብ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ይህ ደግሞ የአካዳሚክ ስረቆት በመሆኑ ወንጀል ነው ብለዋል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ይህንን የአካዳሚክ ስርቆት አጥብቆ የሚከላከል የትምህርት ተቋም በመሆኑ የምታቀርቡት የምርምር ስራ /ፅሁፍ/የራሳችሁ ሃሳብ ፣በራሳችሁ ጥረት የመጣ እንጂ ሙሉ በሙሉ ከሰው ስራ የተወሰደ እና የሚመጣ ስራ ያስጠይቃል ተቀባይነትም አይኖረውም ብለዋል:: ተማሪዎችም በዚህ ዙሪያ ግንዛቤ ወስዳችሁ ራሳችሁንም ፣ትምህርት ክፍላችሁንም እንዲሁም ተቋሙን ከተጠያቂነት መጠበቅ እንዳለባችሁ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡
በመቀጠልም ስልጠናው በዶ/ር ተስፋዬ ተፈሪ የዩኒቨርሲቲው የቤተ-መጽሀፍተና ዶክመንቴሽን ዳይሬክተር ተሰቷል፡፡
Madda Walabu University Public and International Relations Office
For More Information Use the following links:
Facebook: https://web.facebook.com/MaddaWalabuUniversityPages/
LinkedIn: https://www.linkedin.com/com.../madda-walabu-university-page
Telegram: https://t.me/Maddawalabuofficial
X/Twitter: https://x.com/MWU_University
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCT1iYKbYMFSfNxOq1U
E-mail: [email protected]. Se