Amaxxammaate

Amaxxammaate Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amaxxammaate, College & University, Badewacho, Shone.

08/12/2025

መዳን በ ኢየሱስ ብቻ🙏

04/04/2022
24/03/2022
24/03/2022

የሀዲያ መብት ተሟጋቾች ትንሹንም ሆነ ትልቁን ድል ማጣጣም አለባቸው

በ2018 በጥቂት ግለሰቦች የተጀመረው የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ትግል ከብዙ ጥረት በኃላ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል፡፡ የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ትግል ሲጀመር አብዛኛው ህዝብ የትግሉን አላማ አልተረዳም ነበር፣ አንዳንዶች እንዲያውም የሀዲያ መብት ተሟጋቾችን ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት ናችሁ እያሉ ሲረግሟቸውም ነበር። የሀዲያ መብት ተሟጋቾች ግን ሁሉንም ፈተና ተቋቁመው ትግሉን በሀዲያ ከቤራ የሚል ስያሜ ሰጥተው በስፋት ተንቀሳቀሱ። በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን በመፍጠር እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው ቀጠሉ። ቀስ በቀስ ጥቂት የሀዲያ ወጣቶች እና አንዳንድ ምሁራን ትግሉን መቀላቀል ጀመሩ። የሀዲያ ሚዲያ ኔትዎርክ ፈር ቀዳጅ የሚዲያ መድረክ ሆኖ ተመሠረተ። ሌሎች ሀዲያ ተኮር የሚዲያ መድረኮችም ስራ ጀመሩ። ትግሉ በዋነኛነት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ለይ ተቀጣጠለ። የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት አላማና ጥቅም ለሀዲያ ህዝብ በስፋት አስተማሩ፡፡ ጥቂት የሀዲያ መብት ተሟጋቾች ባደረጉት ጥረት የሀዲያ ምክር ቤት በህዳር 2018 የሀዲያን የክልልነት ጥያቄ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

የሀዲያ መብት ተሟጋቾች ትግል እየተጠናከረ ሲመጣ በክልልና በፌዴራል ደረጃ ያሉ ከፍተኛ የሀዲያ በስልጣናት አንጃ በሀዲያ ከቤራ እቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሳመት ጀመሩ። በሀዲያ ከቤራ እንቅስቃሴ የተደነገጡ እነዚህ ባለስልጣናት በሀዲያ መብት ተሟጋቾች ላይ ግልፅ ጦርነት ከፈቱ። የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ትግልን ይደግፉ የነበሩ የሀዲያ ዞን አመራሮችን በጅምላ ከሃላፊነታቸው አንስተው የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄን ለመቀልበስ ታማኝ የሆኑ ግለሰቦችን በምትኩ ሾሙ። የሀዲያ መብት ተሟጋቾች የሚመሩ የከቤራ ኣባላትን ማሳደድ ጀመሩ። በሀዲያ ላይ የአስቸኮይ ግዜ አዋጅ አሳውጀው ከዚህ በፍት ምንም የሰላም ችግር በሌለበት የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በእያንዳንዱ የሀዲያ ወረዳ እንድሰፍር አስደረጉ፡፡ እነዚያ የሀዲያ ባለስልጣናት የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ትግልን ድጋፍ ለማሳጣት የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ በአንድ የሀዲያ ጎሳ የበላይነት ለማስጠበቅ በጥቅት የጎሳ አባላትና አመራሮች ብቻ የሚደረግ እንቅስቃሴ በማስመሰል የውሸት ፕሮፓጋንዳ ማስፋፋትን ቀጠሉ። በዚህ ከፋፋይ ፕሮፓጋንዳ የተነሳ የሀዲያ ክልል ጉዳይ በአንዳንድ የሀዲያ ማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንድያጣ አደረጉ። ሆኖም የሀዲያ መብት ተሟጋቾች ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ብቻ በጥበብ ማካሄዱን ቀጠሉ። ቀስ በቀስ በሙስና የተዘፈቁ ባለስልጣናት የሚነዙት የውሸት ፕሮፓጋንዳ ውሸት መሆኑ በመላው የሀዲያ ህዝብ ታወቀ። ቀስ በቀስ የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ጎሳ ሳይለይ የሁሉም ሀዲያ ህዝብ ጥያቄ ሆነ፡፡ አሁን የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ሁሉም የሀዲያ ህዝብ በጋለ ስሜት እየጠየቀው ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ የሀዲያ ህዝብ በሁሉም ስብሰባዎች እና ዝግጅቶች ቅድሚያ አጀንዳ አድርጎ የሚያነሳው ጥያቄ ነው፡፡

ስለዚህ የሀዲያ መብት ተሟጋቾች የሀዲያ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ በሀዲያ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ እንዲያገኝ በማስቻሉ ትልቅ ክብር ይገበዋል። የሀዲያ መብት ተሟጋቾች ያላሰለሰ ጥረት በተገኘው አበራታች የህዝብ ድጋፍ ልኮሩና ልደሰቱ ይገባል። የተቀመጠው ግብ ላይ እስክንደርስ ድረስ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥል!

22/03/2022
11/02/2022

Egna yetim baminim inam endetim bininoor "mateyyooma" ayilayyim tigetachin inam tiratachin lw "matayyooma" naw

02/02/2022

wel come

Address

Badewacho
Shone
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amaxxammaate posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share