Mesele Sorsa

Mesele Sorsa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mesele Sorsa, College & University, Sodo.

14/03/2026

🚨🚨 ARSENAL SCORES!!! GYOKERES!!! GYOKERES!!! GYOKERES!!! 1-0 ARSENAL!!!

GUNNERS WANT TO WIN THE PREMIER LEAGUE!!! 🤍❤️

40 ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረ ድንቅ አባት🙏እግዚአብሔር ለትልቅ ስራ ያጨው እስራኤልን ከ215 ዓመታት ባርነትና ከ430 ዘመን ስደት በኋላ መርቶ ሀገራቸው ...
24/12/2025

40 ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረ ድንቅ አባት🙏

እግዚአብሔር ለትልቅ ስራ ያጨው እስራኤልን ከ215 ዓመታት ባርነትና ከ430 ዘመን ስደት በኋላ መርቶ ሀገራቸው ያስገባ ታላቁ ነቢይ ነው፡፡ 40 ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረ ድንቅ አባትም ነው፡፡ የአምስት ዓመት ሕጻን ሳለ በሁሉም ዘንድ እጅግ የሚፈራውን ፈርኦንን በጥፊ መታው፡፡ ለንጉሳቸው ትልቅ ቦታ በሚሰጡት ግብጻውያን ዘንድ ድርጊቱ ሕጻን ቢሆንም የሚያስገድል ነበር፡፡ ይሁንና ከውሃ አጊኝታ ልጇ አድርጋ የምታሳድገው የፈርኦን ልጅ ቴርሙት ሕጻን ስለ ሆነ ክፉና ደጉን አይለይም፣ እሳት እንኳ በፊቱ ቢቀመጥ አንስቶ ይበላል ብላ ተከራከረች፡፡ እንደተባለውም የጋለ ፍም ከፊቱ ሲቀመጥ አንስቶ በመጉረሱ ምላሱ ኮልታፋ ቢሆንም ነፍሱ ግን ከሞት ተርፋለች፡፡ ከ12 የያእቆብ ልጆች የእስራኤል ነገዶች አንዱ ከሆነው ከሌዊ ወገን የሚወለደው ሊቀ ነቢያት ሙሴ የስሙ ትርጓሜ “ከውሃ የተገኘ” ማለት ነው፡፡

ቅዱስ ዻውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ በምዕራፍ 11÷24 እንዳለው “በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና” አንድ ግብጻዊ እስራኤላዊ ወገኑን ሲመታ ቢያየው ገድሎ አሸዋ ውስጥ ቀበረው፡፡ በፈርኦን ቤተ መንግስት ቢያድግም ወገኖቹ እስራኤልን አልረሳም፡፡ እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው የወገኖቹን ታሪክና ማንነቱን ትነግረው ነበርና 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ፡፡ በግብጻዊው ላይ ያደረገው ነገር እንደተሰማ ሲያውቅም ወደ ምድያም ሸሸ:: በምድያምም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ፣ ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ልጆች አፈራ:: በ80 ዓመቱ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው፡፡ ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው፡፡

አንደበቱ ኮልታፋ ቢሆንም ወንድሙ አሮን በንግግር እያገዘው ግብጻውያንን በዘጠኝ መቅሰፍትና በአስረኛ “ሞተ በኩር” መትቶ እስራኤላውያንን ነጻ አውጥቷል፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ውስጥም ትልቁን የመሪነት ሚና የተወጣ ሲሆን፣ ባሕር ከፍሎ በደረቅ ያሻገራቸው፣ ለህዝቡ መና ከደመና ያወረደ፣ አለት ከፍሎ ውሃ ያፈለቀ፣ ሌቱን በብርሃን ምሰሶ ቀኑን በሰባት ደመናት ጋርዶ የመራቸው፣ ጠላቶቻቸውን የደመሰሰላቸው እግዚአብሔር መሳሪያው እንዲሆን የመረጠው ታላቅ አባት ነው፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳው እስራኤላውያን ነጻ ስላወጣቸው አላከበሩትም፤ ይልቁንም ደግመው ደጋግመው አስከፍተውታል፡፡ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ “አሰርቱ ትዕዛዛትን” ይዞ ከተራራው ሲወርድ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አሳዝነው ጠበቁት፡፡

ወንድሙ አሮንን አስገድደው ጣኦት አሰርተው ሲያመልኩ፣ ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ በደስታም ሲጨፍሩ ነው ያገኛቸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር “እነርሱን ላጥፋቸውና በሌላ ታላቅ ሕዝብ ዘንድ ልሹምህ” ሲለውም፣ “እነርሱን ከምታጠፋቸው እኔን ከጻፍከኝ ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለ ታላቅ አባት ነው፡፡ በጽላቱ ጣኦቱን መትቶት ሲሰበርም በድጋሚ ጽላቱን በእጁ ሰርቶ አምጥቶ በእግዚአብሔር ጣቶች 10ቱ ትዕዛዛት ተጽፈዋል፡፡ በረከቱ ትደርብንና በየትኛውም ምቾት ውስጥ ብንሆን፣ ክብራችን ከፍ ቢልም ወገንንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አለመርሳት ከአባታችን ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ እንማራለን፡፡

እግዚአብሔር በረከትን እዲያበዛልን፣ ሕይወታችን እንዲባረክ፣ መውጣት መግባታችን የደስታ እንዲሆን በልባችን እንዳሰብን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታ

ጄኖአ ፓትሪክ ቬራን አሰናበተ*********የጣልያኑ ክለብ ጄኖአ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራን ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።ፈረንሳዊው የቀድሞ አማካይ በባለፈው የውድድር አመት የጣሊያኑን ቡድን ተረክቦ...
01/11/2025

ጄኖአ ፓትሪክ ቬራን አሰናበተ
*********

የጣልያኑ ክለብ ጄኖአ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራን ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።

ፈረንሳዊው የቀድሞ አማካይ በባለፈው የውድድር አመት የጣሊያኑን ቡድን ተረክቦ ከወራጅ ቀጠናው በማውጣት በሴሪኤው እንዲቆይ ቢያደርግም በዘንድሮ አመት ግን በሊጉ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ሳይችል ለመሰናበት ተገዷል።

ጄኖአ በውድድር አመቱ ካደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች በስድስቱ ሲሸነፍ በሶስቱ አቻ ተለያይቶ በሶስት ነጥብ በሴሪኤው ግርጌ ላይ ተቀምጧል።

የቀድሞ የመድፈኞቹ ስኬታማው አማካይ ከዚህ ቀደም ኒውዮርክ ሲቲ፣ ኒስ፣ ክርስታል ፓላስ እና ስትራስቡን ማሰልጠኑ ይታወሳል።

18/08/2025

ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት የሚጠይቀው የደመወዝ ማሻሻያ፦
*****************************

ከመስከረም 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡ በዚሁ ማሻሻያ መሠረት፦

1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ
ይደረጋል፡፡
2. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።
3. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም
ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡
4. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000
እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሰጠውን መግለጫ በኮሜንት መስጫው ውስጥ ያገኙታል፦

15/06/2025
27/03/2025

Address

Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesele Sorsa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share