Wolaita Sodo Polytechnic College/ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Wolaita Sodo Polytechnic College/ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Call Directions Website

Wolaita Sodo Polytechnic College/ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Sodo Polytechnic College/ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ, College & University, Woliata Sodo , Ethiopia, Sodo.

22/08/2026
የኪንዶው የባህል አርበኛ አቶ ታከለ ታደሰ ልጆቻቸውን አስተምረው ከሸመገሉ በኋላ በፈረሰኞች ታጅበው በዲፕሎማ ተመረቁነሐሴ 16/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶየወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ...
22/08/2026

የኪንዶው የባህል አርበኛ አቶ ታከለ ታደሰ ልጆቻቸውን አስተምረው ከሸመገሉ በኋላ በፈረሰኞች ታጅበው በዲፕሎማ ተመረቁ

ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ

የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከግቤ 3 ጋር በመተባበር በሰጠው የኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ ስልጠና ላይ አቶ ታከለ ታደሰ በዲፕሎማ ተመርቀዋል።

አቶ ታከለ ልጆቻቸውን አስተምረው ከሸመገሉ በኋላም በውስጣቸው ያለው "እችላለሁ" ባይነት እና የጀግንነት ወኔ ሳይጠፋ ለዚህ ማዕረግ መብቃታቸው ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል።

ተመራቂው የወላይታን ባህላዊ ልብስ በመልበስና በፈረሰኞች ታጅበው ወደ ምረቃው ስፍራ በመምጣት የወላይታ ባህል ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል።

የተሰማቸውን ጥልቅ ኩራትና ደስታ በባህላዊ ቀረርቶ “ነና ያጌቴስ” በማለት የገለፁ ሲሆን፣ በፈረስ ጉግስ ያጀቧቸው ወዳጆቻቸውም “ሀጋው ሀሹ ጋቴስ” በማለት በባህላዊ ጭፈራ አጅበዋቸዋል።

አቶ ታከለ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወደ ሕዝቡ ይበልጥ በመቅረብ አስፈላጊውን ተግባራዊ ስልጠና በመስጠት እያከናወነ ላለው ጠቃሚ ተግባር ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል።

በመለሰ ኦልኮ

ከዛሬው የግቤ-3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሠልጣኞች ምረቃ በኃላ የግቤ-3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጉብኝት አካሂደዋል። በጉብኝቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የቴ/...
22/08/2026

ከዛሬው የግቤ-3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሠልጣኞች ምረቃ በኃላ የግቤ-3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጉብኝት አካሂደዋል።
በጉብኝቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የቴ/ሙ/ት/ሥ/ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ትግሮ፣ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን ኢ/ር ያዕቆብ ያስንንና የኮሌጁ ምክትል ዲኖች ጨምሮ በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።

‎🎓 እንኳን ደስ አላችሁ! 🎓‎ዕውቀትን ከክህሎት ጋር በማቀናጀት ለሀገር እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ብቁ ዜጎችን ማፍራት ቀጥሏል‎​📍ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ‎...
22/08/2026

‎🎓 እንኳን ደስ አላችሁ! 🎓
‎ዕውቀትን ከክህሎት ጋር በማቀናጀት ለሀገር እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ብቁ ዜጎችን ማፍራት ቀጥሏል
‎​📍ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ
‎​የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከግቤ 3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጋር በመተባበር በኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ ሙያ ያሰለጠናቸውን 130 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል።
‎
‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ፋንታዬ ቴክኒክና ሙያ የሀገርን ኢኮኖሚ ለማበልጸግ ትልቅ መሳሪያ መሆኑን ገልጸው፤ ተመራቂዎች ከኃይል ማመንጫ ጣቢያው በቀጥታ ያገኙትን የንድፈ ሀሳብና የተግባር ልምድ በመጠቀም፣ በግድቡ አካባቢ ያለውን ሰፊ የውሃና የአሳ ሀብት ለአዲስ የስራ ዕድል ፈጠራ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።
‎​
‎የኮሌጁ ዲን ኢንጂነር ያዕቆብ ያሲን በበኩላቸው "ተመራቂዎች የስራ ዕድል ጠባቂ ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸውንና ሌሎችን የሚጠቅሙ ስራ ፈጣሪዎች መሆን አለባቸው" ሲሉ አሳስበዋል። ተመራቂዎችም በኮሌጁ ባገኙት በቂ እውቀትና ክህሎት መደሰታቸውን ገልጸው ለሀገራቸውና ለወገናቸው ለውጥ በትጋት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
‎​
‎በዕለቱ የወላይታ ሶዶ ከተማ ምክትል ከንቲባና የከተማው ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ ትግሮ፣ የጣቢያው አመራሮች፣ ተመራቂዎች እና ወላጆች ተገኝተው የበዓሉ ደምቀት ሆናዋል።
‎
‎​ለተመረቃችሁት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ! ሀገራችንን በዕውቀትና በክህሎት እንገንባ! 🇪🇹👏
‎
‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎“ጥራት ያለው ስልጠና ለተግባራዊ እውቀት!”
‎
‎ለፈጣን፣ ታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች የገጻችንን Like እና Follow በማድረግ የኮሌጁ ቤተሰብ ይሁኑ።
‎https://www.facebook.com/profile.php?id=61586812102615
‎
‎ **oPolytechnicCollege
‎

‎🎓 እንኳን ደስ አላችሁ!‎ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግልገል ግቤ-3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 130 በላይ ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነው ⚡️‎‎​📍ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ...
22/08/2026

‎🎓 እንኳን ደስ አላችሁ!
‎ የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግልገል ግቤ-3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 130 በላይ ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነው ⚡️
‎
‎​📍ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ
‎​የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሀገራችን የኢነርጂ ልማት ውስጥ ትልቅ ሚና ባለው የግልገል ግቤ-3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ያሰለጠናቸውን 130 ብቁ ሰልጣኞች ለሁለተኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል።
‎​በመርሃ-ግብሩ ላይ የኮሌጁ የሥራ ሃላፊዎች፣ የስታፍ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተመራቂዎች ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
‎​ቁልፍ መረጃዎች፡
‎​📍 የግልገል ግቤ-3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ
‎​🎓 የተመረቁ ብዛት: 130 ሰልጣኞች
‎​🏆 2ኛ ጊዜ
‎​💡 የሀገራችንን የኃይል ማመንጫ ዘርፍ በብቃት የሚመሩና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚቀበሉ ባለሙያዎችን ማፍራት።
‎
‎​ለተመረቃችሁት ባለሙያዎች ሁሉ የኢንጅነሪንግ እና የቴክኖሎጂ ጉዟችሁ የተሳካ እንዲሆን እየተመኘን፤ ሀገርን በብቃት ለማገልገል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንደምትወጡ እንተማመናለን! 👏🇪🇹
‎
‎📌 ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎“ጥራት ያለው ስልጠና ለተግባራዊ እውቀት!”
‎
‎ለፈጣን፣ ታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች የገጻችንን Like እና Follow በማድረግ የኮሌጁ ቤተሰብ ይሁኑ።
‎https://www.facebook.com/profile.php?id=61586812102615
‎
‎ **oPolytechnicCollege
‎

የዲጂታል ትምህርት ሥርዓትን ለማጠናከር አስፈላጊ ስምምነት ተፈረመ!‎‎​📍ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ኢትዮ ቴሌኮም የትምህርት ማኔጅመንት ሲስ...
21/08/2026

የዲጂታል ትምህርት ሥርዓትን ለማጠናከር አስፈላጊ ስምምነት ተፈረመ!
‎
‎​📍ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ
‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ኢትዮ ቴሌኮም የትምህርት ማኔጅመንት ሲስተም (Education Management System – EMS) እና የቴሌብር ኦንላይን ክፍያ አገልግሎት ለመተግበር ስምምነት ፈጸሙ።
‎
‎ይህ ስምምነት የኮሌጁን አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ሂደቶች ወደ ዲጂታል አሠራር በማሸጋገር የተማሪ መረጃ፣ ምዝገባ፣ ክፍያ፣ የትምህርት አፈጻጸም፣ ፋይናንስ፣ ሰው ኃይል፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ ስቶርና ኢንቬንተሪ እና ሪፖርት አዘገጃጀትን በአንድ የዲጂታል ሥርዓት ለማስተዳደር ያስችላል።
‎
‎በተጨማሪም፣ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያዎቻቸውን በቴሌብር ኦንላይን መክፈል የሚችሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።
‎
‎ሥርዓቱ ከቴሌብር ጋር የሚያገናኝ የክፍያ ኢንተግሬሽን እና API አገልግሎት የሚያካትት ሲሆን፣ የተማሪ ራስ-አገልግሎት፣ የኦንላይን ክፍያ፣ የአካዳሚክ መረጃ እና የሪፖርት አገልግሎቶችንም ያካትታል።
‎
‎ይህ ትብብር የኮሌጁን ዲጂታል ሽግግር፣ የአገልግሎት ቀልጣፋነት፣ የመረጃ ጥራት እና የክፍያ ግልጽነት ለማሻሻል አስፈላጊ ሚና ይኖረዋል።
‎
‎📌 ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎“ጥራት ያለው ስልጠና ለተግባራዊ እውቀት!”
‎
‎ለፈጣን፣ ታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች የገጻችንን Like እና Follow በማድረግ የኮሌጁ ቤተሰብ ይሁኑ።
‎https://www.facebook.com/profile.php?id=61586812102615
‎
‎ **oPolytechnicCollege
‎

‎📢 ማስታወቂያ‎‎የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳምንታዊ የካይዘን (Kaizen) መርሃ ግብር ማክሰኞና ዓርብ የሚከናወን መሆኑ ይታወቃል።‎‎በመሆኑም ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች በመርሃ ግብሩ ...
20/08/2026

‎📢 ማስታወቂያ
‎‎የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳምንታዊ የካይዘን (Kaizen) መርሃ ግብር ማክሰኞና ዓርብ የሚከናወን መሆኑ ይታወቃል።
‎
‎በመሆኑም ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች በመርሃ ግብሩ ላይ በጊዜ ተገኝታችሁ እንድትሳተፉ ኮሌጁ ያሳስባል።
‎
‎🤝 “ካይዘን ለተሻለ ሥራ፣ ለተሻለ ተቋም!”
‎

ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሆቢቻ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከጉቱቶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ‎‎​📍ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ‎ወላይታ ሶዶ ፖ...
20/08/2026

ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሆቢቻ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከጉቱቶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ
‎
‎​📍ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ
‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሆቢቻ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ዕድሎችን ለማስፋት፣ ተማሪዎችን በተግባራዊና ቴክኒካዊ ክህሎቶች ለማብቃት እንዲሁም ለትምህርትና ለሥራ ዓለም ዝግጁ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።
‎
‎ስምምነቱ በLeaders in Teaching Ethiopia (LiTE) Program ትግበራ አካል ሲሆን፣ ከImagine1day International Organization ጋር በመተባበር የተከናወነ ነው። የትብብሩ ዋና ዓላማ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የTVET ትምህርትና የስልጠና ዕድሎችን እንዲያውቁ፣ ተገቢ የሙያና የትምህርት ምርጫ እንዲያደርጉ እና በሥራ ዓለም የሚፈለጉ ተግባራዊና ቴክኒካዊ ክህሎቶችን እንዲያገኙ ማስቻል ነው።
‎
‎በስምምነቱ መሠረት የሙያ ግንዛቤና የአቅጣጫ ስልጠናዎች ይዘጋጃሉ፤ ለተማሪዎች አጭር ጊዜ የተግባር ክህሎት ስልጠናዎች ይሰጣሉ፤ ተማሪዎች የTVET ወርክሾፖችንና የስልጠና ተቋማትን እንዲጎበኙ ይመቻቻል፤ እንዲሁም የሥራ ፈጠራ፣ ፈጠራና ተቀጣሪነት ክህሎቶች እንዲዳብሩ ይደረጋል።
‎
‎ይህ ትብብር በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና በTVET ተቋማት መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ ተማሪዎች ከትምህርት ወደ ሙያ፣ ከሙያ ወደ ሥራ እና ወደ ሥራ ፈጠራ የሚያደርጉትን ሽግግር ለማቀላጠፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል። በተለይም ወጣቶች በሚፈለጉ የሙያ ክህሎቶች እንዲታነጹና ለሥራ ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጠንካራ መሠረት ይጥላል።
‎
‎ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎“ጥራት ያለው ስልጠና ለተግባራዊ እውቀት!”
‎
‎ለፈጣን፣ ታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች የገጻችንን Like እና Follow በማድረግ የኮሌጁ ቤተሰብ ይሁኑ።
‎
‎ **oPolytechnicCollege
‎

በተለያዩ ምክንያቶች ስጓተት የቆየው የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአውቶሞቲቪ ጋራዥ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ሊበቃ ነው።‎‎​📍 ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ ‎...
20/08/2026

በተለያዩ ምክንያቶች ስጓተት የቆየው የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአውቶሞቲቪ ጋራዥ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ሊበቃ ነው።
‎
‎​📍 ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ
‎​በተለያዩ ተግዳሮቶችና ምክንያቶች ተይዞ ለረጅም ጊዜ ስጓተት የቆየው የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአውቶሞቲቪ ጋራዥ ግንባታ፣ አሁን ላይ አዲስ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የአመራር ጽናት ታክሎበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
‎
‎​የኮሌጁ ዋና ዲን ኢ/ር ያዕቆብ ያስን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር፣ የቆመውን የልማት ስራ ያለምንም መጓተትና ማስተጓጎል በሂደት ላይ እንዲሆን ጽኑ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። የዚህ ጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት ውጤት የሆነውና ሲጓተት የነበረው ግንባታ ዛሬ ላይ ዳግም ሕይወት ዘርቶ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።
‎
‎​ይህ ተነሳሽነት ተቋማችን ለቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጥራት ማሻሻል የገባውን ቃል ኪዳን እውን ከማድረግ ባለፈ፣ አመራሩ ለሕዝብ ልማትና ዕድገት ያለው የማይናወጥ ጽናት ማሳያ ነው። ልማት በቁርጠኝነት፣ ስራ ደግሞ በውጤት እንደሚለካ ማሳያ ነው።
‎
‎የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
‎ጥራት ያለው ስልጠና ለተግባራዊ እውቀት!
‎
‎​ለፈጣን እና ታማኝ መረጃዎች የገጻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
‎ገጻችንን Like እና Follow ያድርጉ!
‎ **oPolytechnicCollege
‎

Address

Woliata Sodo , Ethiopia
Sodo
4620

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo Polytechnic College/ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share