ፊቼ መ/መ/ቅድስት ኪዳነምህረት መሰረተ ምግባር ሰ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Tafo
  • ፊቼ መ/መ/ቅድስት ኪዳነምህረት መሰረተ ምግባር ሰ/ቤት

ፊቼ መ/መ/ቅድስት ኪዳነምህረት መሰረተ ምግባር ሰ/ቤት ortodox tewahdo lijoch

††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††††...
07/08/2021

††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም †††
††† ቸር #እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ
# ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ # ጽድቅ መድረስ አይቻልም::
ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን # ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::
"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " # ፍልሠታ " ማለት የእመቤታችን ቅድስት # ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::
ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው # ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::
ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
*የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
*ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::
*የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::
††† በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::
††† # ጽንዕት_በድንግልና : #እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
*ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::*
††† ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ †††
††† እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው::
††† ቅዱስ ዮሴፍ ዘአርማትያስ †††
††† ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ (በመሲህነቱ) አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር::
††† ቅዱስ ኒቆዲሞስ †††
††† ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምሕር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል::
ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት::
እንዲህ እያሉ:-
"ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!"
*በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን በፊቼ መንበረ መድን ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን     እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ እያልን                ...
02/08/2021

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
በፊቼ መንበረ መድን ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን
እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ እያልን
በዘድሮ የፍልሰታ ፆም
ከነሐሴ 1-.ነሐሴ 16
ለ16 ቀናት የሚቆይ የዝማሬ እና የስብከት ወንጌል መርሐ ግብር
ከአዲስ አበባ በተጋበዙ መምህራን እና ዘማሪያን
-ጥዋት በኪዳን ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ትርጐሜ
ትምህርተ ወንጌል እና ዝማረ ከቅዳሴ በፊት
ከቅዳሴ ብሓላ 6:00pm 8:00Pm
የሰርክ ፀሎት ፡ትምህርት ወንጌል እና ዝማሬ እንዲሁም
የመፀሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወንጌል እና ዝማሬ መረሀ ግብር ለልጆች
Address Fitche
ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን በእግዚአብሔር ስም
ታስተላልፋለች እናተም በደጅዋ በረከቱን ለመካፈል
ታብቃቹ አሜን። ሁላችሁም ክርስቲያናዊ ግዴታ
በመወጣት ሼር ሼር በማድረ ከበረከቱ ተካፈሉ ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን # እንኳን_ለአቡነ_ሀብተማርያም_ክብሪ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁየኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ታሪክ ባጭሩአምስቱን መቅሰፍቶች የ...
02/08/2021

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
# እንኳን_ለአቡነ_ሀብተማርያም_ክብሪ_በዓል_በሰላም
_አደረሳችሁ
የኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ታሪክ ባጭሩ
አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም የነበረበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ ነው። አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ። ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡-
1. መብረቅ፣
2. ቸነፈር፣
3. ረሃብ፣
4. ወረርሽኝ፣
5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት።
እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው።
የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡23 ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡
1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6. በጾም ስለተጋደልክ፣
7. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡
የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ 115/116 ፡ 6 በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡ የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን፡፡
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

19/04/2021

Send a message to learn more

የቅዱሳት  ሥዕላት ቤተሰቦች  ከላይ እንደምትመለከቱት ቅዱሳት ሥዕላትን  በመጠቀም  ያለ አግባበ  በዚህ መልኩ  አልባሳት ላይ  በመጠቀም  ለገቢያቸው  ለሆዳቸው  ያደሩ  ሰዎች  በዚህ  መል...
31/03/2021

የቅዱሳት ሥዕላት ቤተሰቦች ከላይ እንደምትመለከቱት ቅዱሳት ሥዕላትን በመጠቀም ያለ አግባበ በዚህ መልኩ አልባሳት ላይ በመጠቀም ለገቢያቸው ለሆዳቸው ያደሩ ሰዎች በዚህ መልኩ አዘጋጅተውታል ሌሎች በየዋሀህነት እንዳይጠቀሙ ይሄንን መልእክት ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያን ሃላፊነቱ እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡
ስለ ቤተክርስቲያን የሚያስቡ እና ያገባኛል የሚል ሁሉ ለጓደኛቹ share በማድረግ እራሶ ተምረው ሌሎችን ለማስተማር ከታች ባለው ሊንክ ተጭነው join ይበሉና ስለ ቅዱሳት ስዕላት ክብር ይማሩም ያስተምሩም
👉👉 page
👉👉 like
እባኩት ሼር ጆይን ኣድርጉ

አቡነ ቀውስጦስ እያለቀሱ የተናገሩት ልብ የሚነካመልዕክት...እኔ እድሜዬ 83 ነው እዚህች ምድር ላይ ብዙ አልቆይምልጆቼ አደራ በርቱ ሃይማኖታችሁን ጠብቁ እነዚህን ሕጻናት ሳይልቤ ያዝናል ይጨ...
30/10/2020

አቡነ ቀውስጦስ እያለቀሱ የተናገሩት ልብ የሚነካ
መልዕክት...
እኔ እድሜዬ 83 ነው እዚህች ምድር ላይ ብዙ አልቆይም
ልጆቼ አደራ በርቱ ሃይማኖታችሁን ጠብቁ እነዚህን ሕጻናት ሳይ
ልቤ ያዝናል ይጨንቀኛል እግዚአብሔር ይጠብቃቹ በሃይማኖት
ያሳድጋቹ ከመከራም ሁሉ ይጠብቃቹ፥
ክርስቲያን በዚህ ዓለም ላይ መከራን ተቀባይ ነው ፤ ልጆቼ
በርቱ ሃይማኖታችሁን ጠብቁ አደራ ሃይማኖታችሁን እንዳትክዱ
በመናፍቃንም በከሃድያንም እንዳትሰረቁ ፥
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አብባ ትኖራለች እንጂ አትጠፋም ተተኪ
ትውልድም አታጣም ፤
ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር እየተሻረኩ ዛሬ ይህችን
ቤተክርስቲያን በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የሆነችውን
ጥንታዊትዋንና እውነተኛይቱን ለማጥፋት የተነሱ የተነሳሱ
ቢኖሩም እነርሱ ይጠፋሉ እንጂ ቤተክርስቲያን ኢትዮጵያ
አትጠፋም፥
ልጆቼ በሆነው ባልሆነው በቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን አትቀስሩ
አትለያዩ በአንድ ላይ ሁናቹ ለቤተክርስቲያን ቁሙ ፥
አላማችሁና ግባቹ መንግስተ ሰማያት ናትና
ልጆቼ ይጨንቀኛል (እያለቀሱ) አደራ እንዳትሰረቁ አይዞአችሁ
ኢትዮጵያ አትጠፋም
የብጹዕ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ በረከታቸውና አባታዊ
ምክራቸው በልቦናችን ይደርብን ቤተክርስቲያናችን ለመጠበቅ
ከሚመርጡት እውነተኛ ልጆች እንደ አንዱ ያድርገን ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶን ኢትዮጵያ አገራችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን
የኢትዮጵያና የቤተክርስቲያናችን ጠላቶችን አምላከ ቅዱሳን
ያስታግስልን አሜን፫

ፊቼ መበረ መድን ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት የሚሰጥበት ይህን በTeleg Gram ቻናል ማስታወቂያ:- ይህ ግሩኘ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምሰጥበትእና ቃለ ወንጌል የ...
22/10/2020

ፊቼ መበረ መድን ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት የሚሰጥበት ይህን በTeleg Gram ቻናል ማስታወቂያ:- ይህ ግሩኘ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምሰጥበትእና ቃለ ወንጌል የምታገኙበት  ይህ ሼር በማድረግ ያጋሩ

ማስታወቂያ:- ይህ ግሩኘ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምሰጥበትእና ቃለ ወንጌል የምታገኙበት talk me via - ()

ፊቼ መበረ መድን ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት የሚሰጥበት ይህን በTeleg Gram ቻናልማስታወቂያ:-                ይህ ግሩኘ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምሰጥ...
19/10/2020

ፊቼ መበረ መድን ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት የሚሰጥበት ይህን በTeleg Gram ቻናል
ማስታወቂያ:-
ይህ ግሩኘ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምሰጥበትእና ቃለ ወንጌል የምታገኙበት
ይህ ሼር በማድረግ ያጋሩ

ልጁ ከስር እባብ መኖሩን አያውቅም...ልጅቷ ልጁ ላይ ድንጋይእንደተጫነበት አታውቅም።***ልጅቷ:- "ልወድቅ ነው ወደ ላይም መውጣት አልቻልኩምምክንያቱም እባቡ ይነክሰኛል... ለምን እሱ ጉልበ...
04/10/2020

ልጁ ከስር እባብ መኖሩን አያውቅም...ልጅቷ ልጁ ላይ ድንጋይ
እንደተጫነበት አታውቅም።
***
ልጅቷ:- "ልወድቅ ነው ወደ ላይም መውጣት አልቻልኩም
ምክንያቱም እባቡ ይነክሰኛል... ለምን እሱ ጉልበቱን አጠንክሮ
ወደ ላይ አይጎትተኝም?!"
***
ልጁ:- "በጣም እያመመኝ ነው በምችለው አቅም ሁሉ ወደ ላይ
ልጎትታት እየሞከርኩ ነው... እሷ ግን ለመውጣት ለምን
አትሞክርም?!" ይላል።
***
ሽረኛው እባብ በመሃል እየሸረበ ያለውን አላወቀም፤ እርሷም
የተጫነበትን አላወቀችም፤
እባቡ ግን አንዳቸው ሌላቸውን እንዳይረዱ ስውር ስራውን
እየሰራ፤ ተሰውሮ መርዙን እየረጨ ነው።
***
The moral is here: ሰው ምን ያህል ጫና ውስጥ እንዳለ
አንረዳም። ሌላም ሰው አንተ ያለህበትን ህመም አይረዳልህም።
ስለዚህ ሌሎችን ከመውቀስ በፊት ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት
መሞከር፣ ራሳችንን በሌላው ሰው ቦታ አርገን ማሰብ
ያስፈልጋል።
(አስተማሪ ሆኖ ካገኙት ሼር Like Page አድርጉት!)

††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††...
01/10/2020

††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ግሼን ደብረ ከርቤ ††† ††† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::" ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል:: በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ:: የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል:: አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል:: ††† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል:: በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል:: በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው:: ††† ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ ††† ††† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው:: የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ:: ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛ

 # ለብዙ_ወጣቶች_ትምህርት_ይሆን_ዘንድ_ሁላችሁም_ሼር_ሼር_አድርጉትበዚህ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙትነው።የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱምሴት ል...
30/09/2020

# ለብዙ_ወጣቶች_ትምህርት_ይሆን_ዘንድ_ሁላችሁም_ሼ
ር_ሼር_አድርጉት
በዚህ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት
ነው።የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም
ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው።ቅዱስ
ጳውሎስ"ነገር ግን ሁሉ በእግባቡና በስርአት ይሁን'(1ኛ
ቆሮ14:40)እንዳለው ማንኛው ሰው ተፈጥሮዊ ስሜት ይንሮው
እንጂ እንደእንስሳ ሳይሆን በስአት መሄድ ይኖርበታል።አንድ ሰው
በሂወቱ ሀላፊነት ካልወሰደ በስተቀር ማንም ሀላፊነት
ሊወስዲለት አይችልም።ወንዱ ይሁን ሴቷ የእግዚአብሔር ህግ
ከማስቀደም ይልቅ ፋሺን እየተባለ ወንዱ በየቀኑ ሴቶችን እንደ
ልብስ እየቀያየረ፣ ሴቷም በየቀኑ ወንዶችን እንደ ልብስ
እየቀየረች ወደ ሞት ይነዳሉ። ይህ የዝሙት መንፈስ
የተጠናወተበት ሰው በስጋው ይሁን በነፍሱ የረከሰና የድያብሎስ
መኖርያ ይሆናል።አላስተዋልንም እንጂ አምላካችን ቅዱስ
እግዚአብሔር ስጋውን ቆርሶ ደሙን አስፍሶ በዋጋ የገዛን
በመሆናችን በራሳችን ላይ ከእግዚአብሔር ህግ ውጭ የማድረግ
ሳጣን የለንም።ስለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን
(1ቆር3:16)።ታድያ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ
ከተባልን የእግዚአብሔር መንፈስ መኖሪያ እንሆን ዘንድ ከዝሙት
መራቅ አለብን። አለበለዚያ ንስሀ ሳንገባ በዝሙት ተጠምደን
የምንኖር ከሆንን ግን ነፍሳችን ከእግዚአብሔር ፀጋ ተራቁታ ወደ
ሲሆል ትነዳለች።ዝሙት የነፍስና የስጋ በሺታ መሆኑን
የአማላካችን ቃል እንዲህ ይላል፦
--"ማንም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር
እርሱን ያፈርሰዋል፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ
ነውና፣ያውም እናተ ናችሁ"(1ቆር3:17)።
እስኪ ከመፀሀፍ ቅዱስ ስለ ዝሙት ምን እንደሚል አብረን
እንመልከት፦
--"እኔ ግን እላችሃለሁ ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ
አመነዝራ ያደርጋል የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ
ያመንዝራል"(ማቴ5:32)።
--"ከልብ ክፉ አሳብ፣መግደል፣ ምንዝርነት፣ዝሙት፣መስረቅ፣
በውሸት መመስከር፣ስድብ ይወጣዋልና"(ማቴ1519)።
--"ከዝሙት ሺሹ;ሰው የሚያደርገው ሀጢያት ሁሉ ከስጋ ውጭ
ነው፣ዝሙትን የሚስራ ግን በገዛ ስጋው ላይ ሀጢያት
ይሰራል"(1ቆሮ6:18)።ብዙ ጥቅስ ማውጣት እንችላለን ግን
ለትምህርት ይሆነን ዘንድ ይህ ይበቃናል።
ታዲያ ምን እናድርግ
--"እስክንሞት ድረስ የታመንህ ሁን የህይወት አክሊል
እሰጥሀለሁ"(ራእ.ዮሐ2:10)።እህቴ ወንድሜ ሆይ መፅሀፍ
ቅዱስ ላይ በማቴ6:33ላይ ይተፃፈውን ስትፈፅሙ አምላካችን
ሌላው ይጨመርበታን እንዳለ ከዝሙት ለመራቅ፣ለመተጋገዝና
ለመረዳዳት፣ዘር ለመተካት በአጠቃላይ ለትዳር የሚሆነን
እግዚአብሔር አይቶ ይሰጠናል።ንስሐ ገብተን የአምላካችን
ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን እንቀበል ዘንድ አምላካችን
ይፍቀድልን(ዮሐ6:53-56)!
እግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር ሰጥቶን ለዚህ ክብር ያብቃን
# አሜን shear ካነበቡ ቡሀላ like
በደንብ አንቡት አደራ አደራራራራ ከላይ ባለው ተማራችሁ? Like በማድረግ ግለፁ 👍 በቀጣይ የምናብራራው ጥያቄ ❓❓❓ 👉 ግብ አውናን ምንድን ነው?❓❓❓❓❓ የምናብራራ ይሆናል ተፅፎ አልቋል like 👍 አይቼ እፓስተዋለው። Like 👍like👍like👍 አበረታቱን ቢያንስ በlike 👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍 የሚለውን ጥያቄ ይብራራ? በlike ግለፁልን ፍላጎታችሁን ። የላይኩን ብዛት አይቼ የማብራራ ይሆናል ። ሼርርርር ይብራራ👍

Address

Vf
Tafo

Telephone

+251967992581

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፊቼ መ/መ/ቅድስት ኪዳነምህረት መሰረተ ምግባር ሰ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share