01/05/2022
የብልጌት ንግግሮች 😃
1.በትምህርት ቤት ቆይታዬ በጥቂት የትምህርት ዓይነቶች ወድቄ ነበር ፡፡ ጓደኛዬ ግን ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶች በብቃት አልፎአል ፡፡ አሁን እሱ በማይክሮሶፍት ኩባንያ መሃንዲስ ነው ፡፡ እኔ ደግሞ የኩባንያው ባለቤት ነኝ ፡፡
2.በእጅህ ገንዘብ ሲኖር ራስህን ትረሣለህ ፡፡ በእጅህ ምንም ገንዘብ ሳይኖርህ ሲቀር ዓለም ማን እንደሆንክ ይረሳሃል ፡፡ ሕይወት ማለት እንደዚህ ነው ፡፡
3.ደሃ ሆነህ ብትወለድ ጥፋቱ ያንተ አይደለም ፡፡ ደሃ ሆነህ ብትሞት ግን ጥፋቱ ያንተ ነው ፡፡
4.ትዕግስት የስኬት ቁልፍ መሠረት ነው ፡፡
5.ስኬትን ማክበር መልካም ነው ፡፡ ከሁሉ የበለጠ አስፈላጊው ነገር ግን ከውድቀት ምርጡን ትምህርት በማስተዋል መውሰድ ነው ፡፡
6.ደስተኛ ያልሆኑ ደንበኞችህ ዋናዎቹ አስተማሪዎችህ ናቸው ።
7.ከባዱን ስራ እንዲሠራ ሠነፉን ሠራተኛ መረጥኩኝ ፡፡ ምክንያቱም ሠነፍ ሠራተኛ ከባዱን ስራ ለመስራት ቀላል መንገድ መፍጠር ይችላል ፡፡
8.በዓለም ሳለህ ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር ፡፡ እንደዛ ካደረግክ ራስህን እየሠደብክ ነው ፡፡
9. ‹‹ ጥሩ ልታደርገው ያልቻልከውን ነገር ቢያንስ ጥሩ እንዲመስል አድርገው ፡፡
10.ብዙ ሠዎች በዓመት ውስጥ ለሚሰሯቸው ስራዎች ራሳቸውን ከመጠን በላይ በመገመት ያቅዳሉ ፡፡ በአስር ዓመት ውስጥ ለሚሰሯቸው ስራዎች ግን ከአቅም በታች ያቅዳሉ ፡፡
11.ንግድ ጥቂት ህጎችና እልፍ ስጋቶች ያሉት የገንዘብ ጨዋታ ነው ፡፡
12.ስኬት ወራዳ አስተማሪ ነው ፡፡ ምርጥ ሠዎችን ማጥፋት ወደማይችሉት ቀሽም አስተሳሰብ ውስጥ ይከታቸዋል ፡፡
13.የንግድ ስራህ በኢንተርኔት ካልታገዘ ንግድህ ከጨዋታ ውጪ ይሆናል ፡፡
═══════❁✿❁ ═══════