Wolkite university law students association WULSA

Wolkite university law students association WULSA This is a channel Where you can access a sort of legal information from wolkite university law students association for more detail information!

04/07/2022

የሀገራችን መገናኛብዙሃን (media) ስራቸው የተምታታባቸው ይመሰለኛል ። በመሠረቱ ስቋቋሙ ነጻ ገለልተኛ ተማኝ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ ግልፀኝነት /transparency / እርግጠኝነት /certainty /ና ተገማችነትን predictablity/ን ለጠቅላላው ህዝብ ለመፍጠር ነው። ለዛ ነው አራተኛ የመንግስት ክንፍ ተብሎ የሚጠሩት። የኛ ሀገር ሚዲያዎች ግን ብሔርንና ወገንን ተኮር አድርጎ ማላዘን ስራቸው ሆናዋል። ይህ ወገን ተኮር ተቆርቋርነት /Activism / እንጂ የሚዲያ ምግባር አይደለም ።✌️

በዚህ ክረምት በተመረጡ የህግ ኮርሶች ላይ ክለሳ እንሰጣለን ። በህግ ትምህርት ላይ ያላችሁ ተማሪዎች በብዙ የምታተርፉበት ገጾ ስለሆነ ላይክ ሼር ፎሎ በማድረግ የህግ እውቀትና ልምዶን ያስፉ።
03/07/2022

በዚህ ክረምት በተመረጡ የህግ ኮርሶች ላይ ክለሳ እንሰጣለን ። በህግ ትምህርት ላይ ያላችሁ ተማሪዎች በብዙ የምታተርፉበት ገጾ ስለሆነ ላይክ ሼር ፎሎ በማድረግ የህግ እውቀትና ልምዶን ያስፉ።

02/07/2022

For all 2022 law graduate class 🎓Your luck is always shine i am very happy for your winning congratulations my dear Friends i wish get more success🏆🎓 ! ❤️ in the name of WULSA

11/06/2022

በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና በአክስዮን ማኅበር መካከል ያላቸዉ መሰረታዊ አንድነት እና ልዩነት
1. አባልነት/Membership: -
✔ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልጉ ሁለት/2/ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ አክሲዮን ማኅበር ደግሞ ለመጀመር ቢያንስ አምስት/5/ አባላት ያስፈልጋሉ ፡፡
✔በአክሲዮን ማህበር ውስጥ በከፍተኛው የአባላት ብዛት ላይ ገደብ የለም ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቢበዛ 50 አባላት ብቻ ሊኖሩት ይችላል ፡፡
2. ዳይሬክተሮች/ Directors፡ -
✔ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአንድ ወይም በብዙ ሥራ አስኪያጆች የሚተዳደር ሲሆን አክሲዮን ማኅበሩ ደግሞ አነስተኛ ቁጥራቸው ሦስት በሚሆኑ ዳይሬክተሮች የሚተዳደር ነው ፡፡
3. ፕሮስፔስተስ/ Prospectus: -
✔ አንድ አክሲዮን ማኅበር ለአክሲዮኖቹና ለዕዳ ወረቀቶቹ ደንበኝነት እንዲመዘገብ ህዝቡን መጋበዝ ይችላሉ ፣ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ካፒታሉን ለማሳደግ ወደ ሕዝብ መሄድ አይችልም ፡፡
4. አነስተኛ ምዝገባ /Minimum subscription:-
✔በአክሲዮን ኩባንያ ውስጥ ሁሉም ካፒታል መፈረም አለባቸው እና ከምዝገባ በፊት የካፒታልው 25% መከፈል አለበት። ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሙሉ በሙሉ በተከፈለ ካፒታል ይመዘገባል ፡፡
5. የማህበሩ ዋና ገንዘብ / capital፡-
✔ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ገንዘብ ከ15,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡ በአክሲዮን ኩባንያ ደግሞ መነሻ ካፒታሉ ከ50,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡
6. የተገደበ ሀላፊነት/Limited liability: -
✔ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሆነ በአክስዮን ማህበር በማህበሩ ባዋጡት/ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ሀላፊነት አላቸዉ፡፡ ማህበርተኞቹም ለማህበሩ ግዴታዎች አላፊ የሚሆኑት ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም በተገደበው የኃላፊነት ደንብ መሠረት የኩባንያው አበዳሪዎች በድርጅቱ በራሱ ንብረት ላይ ብቻ የይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ የተገደቡ ሲሆን የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በግል በያዙት ንብረት ላይ ምንም ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ የላቸውም ፡፡
7. የህግ ስዉነት/Legal personality፡-
✔ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርም ሆነ አክስዮን ማህበር የራሳቸዉ የሕግ ሰዉነት ያላቸዉ ሲሆን በስማቸዉ የመክሰስ ሆነ የመከሰስ እንዲሁም ማንኛዉንም ስራ የመስራን ሰፊ መብት ተጎናፀፈዋል፡፡
8. የአክስዮኖችን ማስተላለፍን በተመለከተ/Transferable shares፡-
✔አክስዮን ማህበር ምንም እንኳን በማኅበሩ አንቀጾች ውስጥ የአክሲዮን ነፃ ዝውውርን መገደብ ቢቻልም (አንቀጽ. 333 (1) የአክሲዮን ኩባንያ አጠቃላይ መርሆዎች በነፃነት የሚተላለፉ በመሆናቸው በአክሲዮን ገበያ ሊሸጡ ወይም ሊገዙ ይችላሉ ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአባላቱ መካከል በነፃነት የሚተላለፉ ሲሆን ለሌሎች ግን እንደ አክስዮን ማህበር እንደፈለጉ በነፃነት የሚተላለፍ አይደለም ምክንያቱም ሲመሰረትም ቤተሰባዊ እና ቅርርብን መሰረት ተደርጎ የሚመሰረት ማህበር በመሆኑ ነው፡፡
☞ሰናይ ጊዜ
© Yilkal
👇

🟩
🟨
🟥

07/06/2022
13/05/2022

We serve the Community

17/03/2022

have a nice night

11/03/2022

እንኳን ደስ አላችሁ!!!
💪💪💪🏆🏆🏆🎖🤩🤩🤩

በብቃትና በላቀ ትጋት የሚታወቀው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረትን በፕሬዝዳንትነት እንዲመራ ተመረጧል።
***************************

የቀድሞ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት እና የኢት/ከ/ት/ተ/ተ/ህብረት ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ኦሊ በዳኔ የስራ ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት በሟሟያ ምርጫ ተመርጦ የነበረው ስራ-አስፈፃሚ የስራ ጊዜውን በመጨረሱ ህብረቱ በትላንትናው እለት በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተካሄደው 41ኛ የኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት መደበኛ ጉባዔ ላይ ምልዐተ ጉባዔው ለቀጣይ ሁለት አመታት ህብረቱን የሚመሩ አዳዲስ ስራ-አስፈፃሚዎችን በመመሪያው መሰረት አወዳድሮ መርጧል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት እያደረገ ባለው 41ኛ መደበኛ ጉባዔ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ሚካኤል ያቦነሽ የኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።

በመሆኑም ውድ ተማሪዎቻችን እና መላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ድሉ የሁላችንም ውጤት ስለሆነ ለውጡን የሚያስቀጥል በላቀ ትጋት የሚታወቀው ህብረታችን ትላንትናና ዛሬ ነገም ቢሆን ከውድ ተማሪዎቻችንና ከግቢያችን ማህበረሰብ ጋር በአርያነት የመሪነት ጉዞውን በስኬት የሚቀጥል ይሆናል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ ለ5ኛ የኢት/ከ/ት/ተ/ተ/ህብረት በስራ-አስፈፃሚነት የቆየ ሲሆን በተከታታይ ለሁለት ጊዜ ደግሞ በፕሬዝዳንትነት ማገልገሉ የሚታወስ ነው።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት




"OUR REWARD IS STUDENT'S HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook 👉 Wolkite University Student Union

Telegram 👉https://t.me/wkusu
ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ👇
EMAIL
[email protected]

11/03/2022

Address

Gubreye
Welk'it'e

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite university law students association WULSA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Wolkite university law students association WULSA:

Share