16/12/2025
አቡጊዳ!
በወልድያ ዩኒቨርስቲ ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል ተማሪዎች እየተዘጋጀ በወልድያ ዩኒቨርስቲ ኤፍ ኤም 89.2 ማህበረሰብ አቀፍ ራዲዮ ጣቢያ የሚቀርበው የእርስዎ ለእርስዎ የሆነው ፕሮግራም ነው።
አቡጊዳ
ከትንሿ ኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲያችን እስከ አለም አቀፍ ሁነቶች ጥልቅ ጉዳዮችን እየዳሰሰ በአዝናኝ አቀራረብ የመረጃ ጥምዖን የሚቆርጠው አቦጊዳ የራዲዮ ፕሮግራም በወልድያ ዩኒቨርስቲ ኤፍ ኤም 89.2 ማህበረሰብ አቀፍ ራዲዮ ጣቢያ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 9:00 እንዲሁም ረቡዕ በድጋሚ ከቀኑ 9:00 ላይ ወደ እርስዎ ይደርሳል።
አቡጊዳ!
በሁላችንም የጋራ ጉዳዮች ሁለንተናዊ ዳሰሳዎችን በመቃኘት እርስዎን ከአለም ጋር ያገናኛል ...
አቡጊዳ የዩኒቨርስቲያችን አሁናዊ ቁመና ከታሪካዊ ዳራዎች ጋር በጥልቀት ይዳሰሳል ... መማር ማስተማር ፣ የጥናትና ምርምር ጉዳዮች ከማህበረሰቡ አገልግሎቶች ጋር ይቃኛሉ።
ሀገራዊ አንድምታዎች ይዳሰሳሉ.... ደግሞም እርስዎን ወደ አለም አሻግረን አለማቀፋዊ ሁነቶችን በአቦጊዳ ማዕዳችን በበረከት እንቆርሳለን።
አቡጊዳ የመረጃ ቋታችን ንፉግነት የለም!
ሁሉም በአንድ በአቡጊዳ
ምርጫው አድርገውን አብረውን ስለሚሆኑ ከልብ እናመሰግናለን!
አቡጊዳ የመረጃ ማዕድዎን የሚቆርሱበት ትክክለኛ ምርጫ!
በወልድያ ዩኒቨርስቲ ኤፍ ኤም 89.2 ማህበረሰብ አቀፍ ራዲዮ ጣቢያ
ጉዳይ ያሉት ጉዳያችን ነው!
አቡጊዳ