Woldia University

Woldia University Woldia University is found in North Wollo, Amhara region, Ethiopia. It's one of the public universities which established in 2012.

አስደሳች ዜና ለስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ! የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረብ አቀፍ ኤፍ ኤም 89.2 ሬድዮ ጣቢያ የተመረጡ እግር ኳሶችን በቀጥታ ኮመንተሪ ጋር ይዞላችሁ ቀርቧል! ዛሬ ቅዳሜ ⚽️...
22/08/2026

አስደሳች ዜና
ለስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ!
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረብ አቀፍ ኤፍ ኤም 89.2 ሬድዮ ጣቢያ የተመረጡ እግር ኳሶችን በቀጥታ ኮመንተሪ ጋር ይዞላችሁ ቀርቧል!
ዛሬ ቅዳሜ
⚽️ LIVE COMMENTARY
⚽️ Hull City vs Manchester United

ከቀኑ 8:00
በ Woldia University FM 89.2

በጋዜጠኛ እስቲበል መንግስቱ

22/08/2026

📢 የNGAT ተፈታኞች ትኩረት!

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ (Woldia University) የNational Graduate Admission Test (NGAT) ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናውን በተመለከተ የወጡ አስፈላጊ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው።

📅 የቀን እና የሰዓት መረጃ

የፈተና ክፍል ማወቂያ ቀን: ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም (ከቀኑ 8:00 ጀምሮ) በዋናው መግቢያ በር ላይ ይለጠፋል

የመፈተኛ ቦታ: በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ

የፈተና መስጫ ቀን: ዕሮብ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ)

⚠️ ማሳሰቢያ
1. ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልፅ ሕጋዊ መታወቂያ እና ፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID) ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ።

2. የተከለከሉ ቁሳቁሶች: ወደ ፈተና ጣቢያ ሞባይል ስልክ ይዞ መምጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

🎓 WOLDIA UNIVERSITY | ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

"Open Mind, Open Eyes"

«በየዓመቱ የምናከብረው የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላቶች የሴቶች ነፃነት፣ የህዝቦች አብሮነትና የጋራ ማንነት መገለጫችን ናቸው!» የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬነሃሴ...
21/08/2026

«በየዓመቱ የምናከብረው የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላቶች የሴቶች ነፃነት፣ የህዝቦች አብሮነትና የጋራ ማንነት መገለጫችን ናቸው!» የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ

ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዘወልድ ባህል ማዕከልና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ከወልድያ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር «ባህላችን ድልድያችን፣ አንድነታችን መድረሻችን» በሚል መሪ ቃል የአሸንድዬ ሶለል እና የቡሄ በዓላትን በዛሬው ዕለት በወልድያ ከተማ የባህል አዳራሽ በፓናል ውይይት በደመቀ ሁኔታ አክብሯል።‎

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ነጻነት አምበሳው የባህልና ቱሪዝም ሀብቶች ከሆኑት መካከል በየአመቱ በወርሃ ነሃሴ አጋማሽ የሚከበሩት የልጃገረዶች የነጻነት በዓላት አሸንድዬ፣ ሶለልና ሻደይ ናቸው ብለዋል፡፡

የማህበረሰቡን ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች በሳይንሳዊ ጥናቶች በማበልጸግ ባህላዊ ይዘታቸውን ጠብቀው ሳይበረዙና ሳይከለሱ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግና ለማስተዋወቅ፣ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተቀናጅቶ መስራቱ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ በዓላቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትስስራቸውን ጠብቀው የቱሪዝም መስህብ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ የምናከብረው የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓላት የሴቶች ነፃነት፣ የህዝቦች አብሮነትና የጋራ ማንነት መገለጫችን ናቸው ያሉት ‎የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ሲሆኑ እንዲህ ዓይነቶቹ የፓናል ውይይቶች ባህላዊ እሴቶችን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍና የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት በርካታ ዓመታት ይህን የባህል ፌስቲቫል በአጋርነት እያገዘ እንደሚገኝ የተናገሩት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዘወልድ የባህል ማዕከል ዳይሬክተር መምህር ውቤ ታደገ በበኩላቸው እንደነዚህ ዓይነት የማህበረሰብ እሴቶች እንዲጠበቁ፣ እንዲለሙና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው በሳይንሳዊ ጥናት አስደግፎ በመሰነድ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ ተቋሙ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ‎

በወልድያ ከተማ በተካሄደው በዚህ የፓናል ውይይት ላይ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን መምህርት እድላም ንጉሴ እና መምህርት ህይወት ፈንታው አማካኝነት ‎የሻዳይ፣ አሸንድዬና ሶላል ፌስቲቫል ታሪካዊ አመጣጥ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም የቀረበውን ጥናታዊ ጽሁፍ መነሻ በማድረግ በርካታ ሃሳብ አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ተካሂዷል፡፡

‎በተመሳሳይ በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ የሚከበሩትን የቆቦ ሶለል እና የላሊበላ አሸንድዬ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በየቦታዎቹ የፓናል ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራኖችም በቦታው በመገኘት ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎችን አቅርበዋል።

ዘገባው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ነው፡፡
-------------------------------------------
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ!›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
For latest updates, please follow the university official pages: Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebook፡ https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel =https://t.me/Woldia_University
Linkedin = https://t.me/Woldia_University/2985
Tiktok = https://www.tiktok.com/.university?_r=1&_t=ZS-95j0halspeP
P.O.Box = 400Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

Partial View of Woldia University
20/08/2026

Partial View of Woldia University

በቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስር እየተተገበሩ የሚገኙ 22 ፕሮጀክቶች ላይ የሂደት ግምገማ ተካሄደ‎‎ነሃሴ 13/2018 ዓ.ም ‎‎በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ...
19/08/2026

በቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስር እየተተገበሩ የሚገኙ 22 ፕሮጀክቶች ላይ የሂደት ግምገማ ተካሄደ

‎ነሃሴ 13/2018 ዓ.ም

‎በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ከአሁን በፊት በመተግበር ላይ የሚገኙ 22 ፕሮጀክቶች በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮችንና የደረሱበትን ሁኔታ በምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት የካውንስል አባላትና በፕሮጀክት ፈጻሚዎች አማካኝነት ከነሃሴ 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሂደት ግምገማ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርየ በለጠ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር የሚፈቱና ህይወቱን የሚያሻሽሉ ተግባር ተኮር የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

‎እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የተቀመጠላቸውን ግብ እንዲያሳኩና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ውጤት እንዲያመጡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

‎የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ቢሆን በበኩላቸው ፕሮጀክቶቹ የታለመላቸውን ዓላማ መምታት እንዲችሉ ሂደቱን እየገመገሙና የማስተካከያ እርምት እየሰጡ ያሉበትን ደረጃ እያወቁና እያሳወቁ መሄዱ ለፕሮጀክቶቹ መሳካትና ውጤታማነት ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‎በሂደቱ ላይ ፕሮጀክቶቹ የሚያጋጠሟቸውን ማነቆዎች ከወዲሁ በመቅረፍ በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት በማጠናቀቅ ለተጠቃሚ ማህበረሰቡ ለማስተላለፍ ግምገማው ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

‎በመድረኩ ላይ ከተነሱ ችግሮች መካከል በማህበረሰቡ ዘንድ ቶሎ አምኖ ያለመቀበል፣ ተቋማት ፕሮጀክቶቹ በመተግባር ላይ እያሉ ያለመተባበር፤ ጊዜያቸውን ከጨረሱ በኋላም ተቀብሎ ለማስቀጠል ኃላፊነት አለመወሰድና የኔነት ስሜት አለመሰማት እንዲሁም አጋር አካላት አለመኖር የሚሉት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።

‎በቀረቡት የስራ አፈጻጸም የሂደት ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን የግምገማ ሂደቱ በቀጣይም በባለድርሻ አካላት አማካኝነት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

‎ዘገባው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ነው፡፡
‎-----------------------------------------
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ!›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
For latest updates, please follow the university official pages: Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebook፡ https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel =https://t.me/Woldia_University
Linkedin = https://t.me/Woldia_University/2985
Tiktok = https://www.tiktok.com/.university?_r=1&_t=ZS-95j0halspeP
P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

የዩኒቨርሲቲውን የውስጥ ገቢ አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ ‎ ‎ነሃሴ 12/2018 ዓ.ም ‎ ‎የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት ከሚበጀትላቸው በጀት በተጨማሪ የውስ...
18/08/2026

የዩኒቨርሲቲውን የውስጥ ገቢ አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
‎ ‎
ነሃሴ 12/2018 ዓ.ም ‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት ከሚበጀትላቸው በጀት በተጨማሪ የውስጥ የገቢ አቅማቸውን በማሳደግ እራሳቸውን እንደሚደጉሙ ይታወቃል፡፡ ‎

‎የወልድያ ዩኒቨርሲቲም ከዓመት ዓመት የውስጥ የገቢ አቅሙን ለማሳደግ እና እራሱን በበጀት ለመደገፍ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት የዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ ማመንጫ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዋጋየ ሞላ ናቸው፡፡ ‎ ‎

ባሳለፍነው በጀት ዓመት 4.8 ሚሊዮን ብር አካባቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከተለያዩ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ካሉ ጸጋዎች ከ5.1 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 106.8% ማሳካት መቻሉን የገለጹት ስራ አስፈጻሚዋ በያዝነው በጀት ዓመትም ከ6.7 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‎

‎ዩኒቨርሲቲው በባለፈው በጀት ዓመት የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ በተደረገው ከፍተኛ ጥረትና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲሁም ባከናወናቸው ስራዎች ከእቅድ በላይ ማሳካት ተችሏልም ብለዋል፡፡

‎በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲውን የተለያዩ የውስጥ ሀብቶችና አገልግሎቶችን በማስፋት አቅም በፈቀደ መጠን ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል ያሉ ሲሆን ዕቅዱን ከግብ ለማድረስና ገቢን ለማሳደግ የተለያዩ መሰናክሎች ሊኖሩ ቢችልም የውስጥ አሰራርን በማሻሻልና የቁጥጥር ስርዓትን ዘርግቶ በማጠናከር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ‎

‎በያዝነው በጀት ዓመትም የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት አዳዲስ የገቢ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና የዩኒቨርሲቲውን የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለውስጥ ገቢ ማደግ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ እሱንም በስፋትና በአግባቡ ጥቅም ላይ የማዋል ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ‎

በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ክፍሎችና ከውጭ አጋር ተቋማት ጋር ያለውን የትብብር ስራ በማጠናከርና ክትትል በማድረግ ዕቅዱን በየጊዜው እየገመገሙ የተሻለ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው በማለት ለዕቅዱ መሳካትም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ድጋፍና ትብብር ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ‎

‎ዘገባው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ነው፡፡
------------------------------------------
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ!›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
For latest updates, please follow the university official pages:
Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebook፡ https://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel =https://t.me/Woldia_University
Linkedin = https://t.me/Woldia_University/2985
Tiktok = https://www.tiktok.com/.university?_r=1&_t=ZS-95j0halspeP
P.O.Box = 400Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና ባለሙያዎች የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠና ተሰጠነሀሴ 9/2018 ዓ.ም ​በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) በትብብር የተዘ...
15/08/2026

ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና ባለሙያዎች የኢንተርፕረነርሺፕ ሥልጠና ተሰጠ

ነሀሴ 9/2018 ዓ.ም
​በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) በትብብር የተዘጋጀ የሥራ ፈጣሪነት ሥልጠና (Entrepreneurship Training Workshop - ETW) ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና ባለሙያዎች ተሰጠ።

​ስልጠናው ከነሀሴ 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ለ34 የተመረጡ መምህራንና ከሚመለከታቸው ክፍሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች ነው የተሰጠው።

ሥልጠናውን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር በላይ መንግስቴን ጨምሮ በአራት ሀገር አቀፍ አሠልጣኞች ተሰጥቷል።

ዓላማውም የሥራ ፈጣሪነት ሥነ-ምግባር ማሳደግ ፣ የባህሪ (Behavioral) ለውጥ ማምጣት እና አጠቃላይ የሥራ ፈጠራና (Business ecosystem) መረዳት መሆኑን በኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት የንግድ ልማት አማካሪ (National Trainer) እንዲሁም የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ወንደሰን ነገዱ ገልጸዋል።

በ​ሥልጠናው በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማ በሆኑ 10 Competencies (ብቃቶች) እና 30 Behavioral Indicators (ባህሪያት) ላይ ያተኮረ ሲሆን ሰልጣኞች በተግባር የተደገፉ የቢዝነስ ሃሳቦችን በመፍጠርና በመሸጥ Self-responsibility (የራስ ኃላፊነት) የመውሰድ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አስተባባሪው ገልጸዋል።

​አቶ ወንደሰን አክለውም ሰልጣኞቹ ያገኙትን እውቀት ለመማር-ማስተማርና ለCommunity Service ከመጠቀማቸው ባለፈ ወደፊት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በሚደረግ ስምምነት መሠረት ወደ Basic TOT (Training of Trainers) እና National Trainer ደረጃ ማደግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎችም ከስልጠናው ብዙ ነገር አግኝተናል። ሰልጥነን መቀመጥ ሳይሆን ይህንን መሬት ላይ አውርደን ችግሮቻችንን ቀስ በቀስ በመቀነስ ራሳችንን ልንለውጥ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ለተሳታፊዎች የማበረታቻ ሽልማትና በኢንስቲቲዩቱ የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት በማበርከት ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ነው ፡፡
-------------------------------------------
‹‹አእምሮ ሲከፈት፤ ዓይኖች ማየት ይችላሉ!›› ‹‹ Open Mind, Open Eyes!››
For latest updates, please follow the university official pages: Web site: https://www.wldu.edu.et/
Facebookhttps://www.facebook.com/WoldiaUniversity
Telegram Channel =https://t.me/Woldia_University
Linkedin = https://t.me/Woldia_University/2985
Tiktok = https://www.tiktok.com/.university?_r=1&_t=ZS-95j0halspeP
P.O.Box = 400Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ!ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ለዋናው ግቢ፣ ለቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት እና ለመርሳ ግብርና ካምፓስ መምህራኖችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋ...
14/08/2026

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ!

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ለዋናው ግቢ፣ ለቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት እና ለመርሳ ግብርና ካምፓስ መምህራኖችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Upcoming event announcement
14/08/2026

Upcoming event announcement

ማስታወቂያ!የፌዴራል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ምዝገባን ይመለከታል
12/08/2026

ማስታወቂያ!
የፌዴራል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ምዝገባን ይመለከታል

ማስታወቂያ

የ ኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሚሰጥባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ተመዝግባችሁ ለመማር ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

✍️ ነጻ የትምህርት እድሉ የሚሰጣቸው ጥቅሞች
👉 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን
👉 የመኝታና የምግብ አገልግሎት
👉 የተሟላ እና ልዩ ሥርዓተ ትምህርት የሚከተል ጥራት ያለው ትምህርት
👉 ምቹ የመማሪያ አካባቢ
✍️ትምህርት የሚሰጥባቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
✍️ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል
👉 ቡኢ ልዩ አዳሪ
👉 ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ
👉 ጋምቤላ ልዩ አዳሪ
👉 ወሊሶ ልዩ አዳሪ
👉 ቦንጋ ልዩ አዳሪ
✍️ 9ኛ ክፍል ብቻ
👉 አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ
👉 ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ
👉 አሶሳ ልዩ አዳሪ
👉 ባህር ዳር ልዩ አዳሪ
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✍️ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት 85 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
👉 ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት

✍️ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
👉በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነት 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች።
✍️ የምዝገባ ሁኔታ
👉 ባሉበት በበየነ መረብ ( Online) ይመዝገቡ፡_ https://sbs.moe.gov.et/apply
✍️ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ፖርታል በኦንላይን መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል
✍️ ምዝገባው እስከ ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
✍️ ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል
✍️ የመመልመያ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ባሉን ክፍት ቦታዎች በሚመደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው።

Address

North Wollo
Woldia
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woldia University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Woldia University:

Shortcuts

Share