Wolkite University Student Union

Wolkite University Student Union this is the official page for Wolkite University Student's Union Our reward is student's happiness!

43ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት መደበኛ ጉባኤ “ጠንካራ የተማሪዎች አደረጃጀት ለተሻለች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ተካሄደ፡!
26/03/2024

43ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት መደበኛ ጉባኤ “ጠንካራ የተማሪዎች አደረጃጀት ለተሻለች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ተካሄደ፡!

‘’ክብር እና ፍቅር ለአረጋዊያን እና ለህፃናት!’’
07/01/2024

‘’ክብር እና ፍቅር ለአረጋዊያን እና ለህፃናት!’’

የ6ኛው ዙር የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት************************************በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የተማሪዎች መብት እና ጥ...
27/12/2023

የ6ኛው ዙር የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት
************************************

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የተማሪዎች መብት እና ጥቅማቸውን የሚያስከብሩላቸውን የህብረት አመራሮች የሚመርጡበት እና ዴሞክራሲን ከወዲሁ የሚለማመዱበት መመሪያ በሀገር አቀፍ ህብረቱ ተገምግሞ በቀድሞ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በፀደቀው መመሪያ መሰረት በፓርላማው(በጠቅላላ ጉባዔው) አባላት የድምፅ ምርጫ እና በተለያዩ ምዘናዎች ባስገኙት ነጥብ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት፦
👉 በፕሬዚደንትነት ተማሪ ያሬድ ላቀው
👉 በም/ፕሬዚደንትነት ተማሪ ዳዊት ሰይፋ እና
👉 በዋና ፀኃፊነት ተማሪ ይታደስ ደመቀ ሆነው ህብረቱን የሚመሩ ይሆናል።

ማስታወሻ:-
👉 በምርጫው ዙርያ ማንኛውም አይነት ቅሬታ ያለው አካል ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በተከታታይ ባሉ 3 የስራ ቀናት በፅሁፍ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑንን እናሳውቃለን።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

 በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታ...
23/11/2023



በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2014 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል (Withdrawal) በመሙላት ላቋረጣችሁ የዳግም ቅበላ (Readmission) ተማሪዎች በሙሉ፡-

የምዝገባ ጊዜ ህዳር 20-21/2016 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 24/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
--> ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

1ኛ. መሰናዶ ያጠናቀቃችሁበትን ሰርተፍኬት፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር እና አራት 3x4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ፤
2ኛ. አንሶላ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ እናሳስባለን፡፡

ማስታወሻ፦
--> ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

 #ማስታወቂያ ፦የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲስኮ እና ሁዋዌ ኔትዎርክ አካዳሚ በተለያዩ ዓለማቀፍ የኔትዎርኪንግ፣ ጥገና እና ሴኩዩሪቲ የስልጠና መስኮች ተማሪዎችን ለማሠልጠን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ስለሆ...
27/10/2023

#ማስታወቂያ



የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲስኮ እና ሁዋዌ ኔትዎርክ አካዳሚ በተለያዩ ዓለማቀፍ የኔትዎርኪንግ፣ ጥገና እና ሴኩዩሪቲ የስልጠና መስኮች ተማሪዎችን ለማሠልጠን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ስለሆነ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሦስት
የትምህርት ቀናት ወደ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመሔድ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል:።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

 #ማስታወቂያ ፦     ውድ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር የ4ተኛ አመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎች በቅድሚያ እንኳን  #ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን ከዚህ በፊት ...
05/10/2023

#ማስታወቂያ



ውድ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር የ4ተኛ አመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎች በቅድሚያ እንኳን #ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን ከዚህ በፊት በተደረገው የጥሪ ማስታወቂያ መሠረት መግቢያ መስከረም 26 እና 27 ሲሆን በዋናው ግቢ (ጉብርየ) እና በወልቂጤ ካንፓስ (ክላስተር) ተማሪ የሆናችሁ ነባር ተማሪዎች ከዚህ በታች በሚገኘው ማስፈንጠሪያ(Link) በመግባት የተመደባቹበትን የማደርያ ህንፃ ቁጥር(Block No.) እና የማደሪያ ክፍል ቁጥር(Dorm No.) ሙሉ የመታወቂያ ቁጥር (ID.No) በትክክል በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ወደ አረንጓዴው እና ሰላማዊ ወደ ሆነው ግቢያችን የምታደርጉት ጉዞ መልካም እንዲሆንና በዚህ አመት በግቢያችን የምታሳልፉት ጊዜ ያማረና የሰመረ፣ ቆይታችሁም ትዝታ የተሞላበት፣ ተስፋችሁ የሚለመልምበት ብሎም የተሳካ ውጤት የምታመዘግቡበት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

ድልድሉ ይፋ የተደረገበት ማስፈንጠሪያ(Link)👇
https://t.me/WKUDormitoryBot

!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በዓሉን ለምታከብሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 498ኛው የነብዩ መሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ እ...
27/09/2023

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በዓሉን ለምታከብሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 498ኛው የነብዩ መሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የደስታ፣ ሰላም እና የበረካ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

☪መልካም በዓል!!!🌙

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

 #ማስታወቂያ    ፦           የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የቅድመ-ምረቃ እንዲሁም የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ዓመታዊ የትምህርት የጊዜ...
16/09/2023

#ማስታወቂያ



የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የቅድመ-ምረቃ እንዲሁም የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ዓመታዊ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ (Academic Calendar) ከዚህ በታች የተገለፀ ሲሆን በፕሮግራሙ መሰረት ተገቢውን ዝግጅት ከወዲሁ እንድታደርጉ እያሳወቅን፤ የ2ኛ አመት ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 21 እና 22 ሲሆን ከዚያ በላይ ያሉ የግቢያችን ነባር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ መስከረም 26 እና 27 መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በየኮሌጃችሁ ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እያሳሰብን፤ በሬሚዲያል ት/ት ውጤታችሁን አሻሽላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ጥሪ በቅርቡ የሚገለፅ መሆኑን እናሳውቃለን።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

.      🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼  እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት              በሰላም አደረሳችሁ!       🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼አዲሱ አመት የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የበረከት...
12/09/2023

. 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት
በሰላም አደረሳችሁ!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

አዲሱ አመት የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የበረከት፣ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ እንዲሁም የውቢቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሀዘን ጊዜዋ አብቅቶ መልካም መፃይ እድሏ የሚረጋገጥበት እንዲሁም ውድ የግቢያችን ተማሪዎች ያቀዳችሁትን ሁሉ የምታሳኩበት፣ የስኬት እና የውጤት ዓመት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
መልካም አዲስ አመት!!!
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

 #ማስታወቂያ ፦👇
08/08/2023

#ማስታወቂያ

፦👇

የሀዘን መግለጫ!******************************በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ውስጥ የጋዜጠኝነትና...
04/08/2023

የሀዘን መግለጫ!
******************************

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ውስጥ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህር የነበሩት ታደሰ አበበ ገብረሀና (ረ/ፕ/ር) በሀገር አቀፍ ፈተና ላይ በፈታኝነት በተመደቡበት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተወለዱ በ38 ዓመታቸው ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

አበበ ገብረሀና ከ20/01/2002 ዓ.ም ጀምሮ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ተቀጥረው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በ2009 ዓ.ም ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተዘዋውረው በመምህርነት፤ ከ06/03/2009 እስከ 11/03/2013 ዓ.ም ድረስ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል በኃላፊነት እንዲሁም ከ19/06/2013 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ምክትል ዲን በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡

መምህር ታደሰ ባለትዳርና የሶስት ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን በስራቸው ትጉህ፣ ታታሪና ታማኝ ሰራተኛ ከመሆናቸውም በላይ በባህሪያቸው ቅን፣ ለሰው አሳቢ፣ ለተማሪዎቻቸው ተቆርቋሪ እንዲሁም ሰውን ተናግረው የማያስቀይሙ እና በፍፁም ትህትና የተሞሉ ነበሩ፡፡

በዚህ ድንገተኛ ህልፈት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ እጅጉን አዝኗል፡፡ በመሆኑም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራር እና ማህበረሰቡ በጥቅሉ በመምህሩ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ዩኒቨርሲቲው የገለፀ ሲሆን የወልቂጤ ዩኒቨረሲቲ የተማሪዎች ህብረትም ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው፣ ለተማሪዎቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ መፅናናትን ይመኛል።

ነፍስ ይማር!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

 #ማስታወቂያ :-  በቅድሚያ በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረውና ለአዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ለሚሆናችሁ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የመፈተኛ ቀን መዳረሻ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ወደ ወልቂጤ...
23/07/2023

#ማስታወቂያ

:-

በቅድሚያ በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረውና ለአዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ለሚሆናችሁ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የመፈተኛ ቀን መዳረሻ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምታደርጉት ጉዞ መልካም እንዲሆንና ቆይታችሁም ትዝታ የተሞላበት፣ ተስፋችሁ የሚለመልምበት ብሎም የተሳካ ውጤት እንድታስመዘግቡ እየተመኘን ሁላችሁም ወደ ግቢ ስትመጡ መያዝ ያለባችሁን አስፈላጊ ነገሮች ብቻ እንድትይዙ እያሳስብን፤ የብሄራዊ ፈተና የመለያ ቁጥር (Admission Number) በማስገባት የማደሪያ ክፍል ድልደላ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የመኝታ ክፍል ድልደላ ቦት {WKU Dormitory Placement( https://t.me/WKUDormitoryBot)} ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ማስታወሻ፦
=>የብሄራዊ ፈተና የመለያ ቁጥራችሁ (Admission Number) ከዜሮ(0) የሚጀምር ካለ ዜሮን በማስወገድ በመቁጠሪያ ቁጥር ብቻ ጀምራችሁ እንድትጠቀሙ እንጠይቃለን።

ለምሳሌ 079301 => 79301

=>የማደሪያ ህንፃዎችን ጨምሮ ግቢው ውስጥ ያሉትን ቦታዎች የሚያሳየውን ጠቋሚ ካርታ አሳትማችሁ(PRINT) አድርጋችሁ በመያዝ በቀላሉ እንድትገለገሉ እናሳውቃለን።

መልካም እድል!!!

!


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉 https://t.me/wkusu
ፌስቡክ 👉 www.fb.com/WKUStsU
ድህረ-ገፅ 👉 https://wkusu.com

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉https://t.me/WKUSU_bot

Address

Wolkite
07

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite University Student Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The University

Send a message to Wolkite University Student Union:

Share