Offeshal Lidiya tefera

Offeshal  Lidiya tefera Preach Jesus

05/04/2023

Sola - ብቻ

ሶላ (Sola) የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ብቻ" እንደማለት ነው። በውስጡም "ተጨማሪ የሆኑ ነገሮች አያስፈልጉም" የሚልን መልዕክት አዝሏል።

በፕሮቴስታንት ተሐድሶ ወቅት የተሐድሶ መሪዎች ከመጽሃፍ ቅዱሱ የወንጌል እውነት ፈቀቅ የተባሉባቸውን በርካታ ጉዳዮችን አንስተው ሞግተዋል። "አምስቱ ብቻዎች" | "The five solas" | በመባል የሚታወቁት ሃሳቦችም የተሐድሶውን አጠቃላይ አሳብ በአጭሩ ማንጸባረቅ የቻሉ አንኳር ነጥቦች ነበሩ።

አምስቱ ብቻዎች ("The Five Solas") በመባል የሚታወቁት ነጥቦች አጋዥም ሆነ ጭማሪ የማያስፈልጋቸውን አምስት የክርስትና ዋና ዋና ሃሳቦችን የሚገልጹ ሲሆኑ እንደአንድ አማኝ ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የተገቡ መሰረታዊ የክርስትና እውነቶች ናቸው።

እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡ -

1 -በጸጋ ብቻ | Grace Alone | Sola Gratia.

“በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው።”
ኤፌሶን 2፥5 (አዲሱ መ.ት)

2. በእምነት ብቻ | Faith Alone | Sola Fide

“ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።”
ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት)

3. በእግዚአብሔር ቃል ብቻ/ቃሉ ብቻ| Scripture Alone | Sola Scriptura

“ከሕፃንነትህም ጀምረህ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15 (አዲሱ መ.ት)

4. • በክርስቶስ ብቻ/ክርስቶስ ብቻ | Christ Alone | Solus Christus

“ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
ዮሐንስ 14፥6 (አዲሱ መ.ት)

5. ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ | For the Glory of GOD Alone| Soli Deo Gloria

“ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

• በፀጋ ብቻ
• በእምነት ብቻ
• በክርስቶስ ብቻ
• በእግዚአብሔር ቃል ብቻ
• ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ

ይህንን ሀሳብ ለማውሳት ያህል በጣም በጥቂቱ ይህንን ካልን በእያንዳንዱ ነጥብ ውስጥ ሰፋፊ ዝርዝር ሀሳብ ስላለው ከዚህ በተሻለ የመፅሀፍቅዱስ አስተማሪዎች ብዙ ማለት ስለሚችሉ መማማር እንችላለን!

06/03/2023

በጣም ነው ምወዳዳችሁ ለናን ልዪ ፍቅር አለኝኝኝ ተባረኩ

ለ 40 ደቂቃ ብለው የጀመሩት ፕሮግራም ዛሬ 11ኛ ቀኑን ይዟል።እኛም ናፍቀንሃል 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥በKentucky ግዛት Lexington ከምትባል ከተማ ሃያ ማይል ያህል ርቃ የምትገኝ ትንሽ የመንደ...
19/02/2023

ለ 40 ደቂቃ ብለው የጀመሩት ፕሮግራም ዛሬ 11ኛ ቀኑን ይዟል።
እኛም ናፍቀንሃል 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

በKentucky ግዛት Lexington ከምትባል ከተማ ሃያ ማይል ያህል ርቃ የምትገኝ ትንሽ የመንደር ከተማ ነች Wilmore. ከተማዋን ከተማ ያደረጋት ግዙፍ የክርስቲያን ዩኒቨርሲቲ Asbury University እና Asbury Theological seminary ነው ማለት ይቻላል። የመማሪያ ሕንጻዎች፣ ላይብሬሪዎች፣ ቢሮዎች፣ መሰብሰቢያ አዳራሾች፣ የተማሪ ማደሪያዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች ለዚያች የመንደር ከተማ ውበት ሆነዋል። ለቀጣይ ትምህርቴ ያንን ግቢ ከረገጥኩ ገና ዓመት አልሞላኝም። ለጸሎት የሚሰጡት ትኩረት፣ ለግል የጥሞና ጊዜ፣ ለጋራም አምልኮ ያላቸው ትርጉም ከፍተኛ ነው። ትምህርት ቤቱ የዌስሊ አሻራ ያለበት መሆኑንና አንዳንዶቹ መንፈሳዊ ልምምዶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከመሆናቸው ባሻገር እንደ ዌስሊ ለጋሲ እንደሚታዩ ሰምቻለሁ።

ባለፈው ሳምንት የተለመደው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቻፕል (ሳምንታዊው የማለዳ ጸሎት) በሚደረግበት ወቅት ያልተጠበቀ መለኮታዊ መገኘት በመካከላቸው መከሰቱንና እንግዳ ነገርም ሆኖ እንደነበር በበቀደሙ ልጥፌ ነግሬያችሁ ነበር። የ አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ደክማለች ለዓለማዊነት እጇን ሰጥታለች በሚባልበት፣ ሠይጣን በምድሪቱ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶአል ትውልዱን በልቶታል ተብሎ በሚወራበት፣ ክፋትና ርኩሰት ጣራ ነክቶአል ወንጌልን መስበክ ነውር ሆኗል ግለኝነትና ቁሳዊነት ምድሪቱን ወርሷል፣ ትውልዱም ከሃዲዱ ወጥቶ ወደ ሞት እየተነዳ ነው በሚባልበት በዚህ ጊዜ ተስፋን የሚያጭር ነገር በዩኒቨርሲቲው ቻፕል ውስጥ ተከስቷል።

ዛሬ ዓይኖቼ ያዩትን ከጓደኞቼም ስለሁኔታው የሰማሁትን ልመስክር። “አቤቱ፥ ትመለሳለህ ታድነንማለህ፤ ሕዝቡም በአንተ ደስ ይላቸዋል።” (መዝ. 85:6) ይኼውላችሁ:- እገሌ የሚባል ታዋቂ አገልጋይ ይመጣል ተብሎ አልታወጀም። የማነቃቂያ ኮንፈራንስ አለ ተብሎ ማስታወቂያ አልተለጠፈም፣ አልተለፈፈም። ዕቅድ ተይዞ፣ ስልት ተነድፎ ምንም ዝግጅት አልተደረገም። ጥቂት የአምልኮ መሪዎች ዝማሬያቸውን አቀረቡ… የተለመደው ዓይነት አጭር የቃል መልዕክት ተላለፈ፣ ከመልዕክቱ በኋላ በቃሉ የተወቀሳች ሁ ወደፊት ኑ ጥሪ ቀረበ፣ ጸሎት ተጀመረ ዝማሬው ቀጠለ፣ ንስሓ መግባት ምስክርነት መስጠት ሆነ አልቆም ብሎ ይኼው ዛሬ ድረስ ቀጥሏል። መች እንደሚያቆም የሚያውቅ ሥጋ ለባሽ የለም። እሳቱ እንደ ነደደ ነው።

ይነጋል ይመሻል ያለማቋረጥ ይመለካል፣ ይጸለያል፣ ቃል ይነበባል፣ ንስሓ ይገባል፣ ምስክርነት ይተላለፋል። የሙዚቃ ድምቀት የለም። የመዝሙር ውበት የድምጽ ውህደት ለረጅም ጊዜ ሲያጠኑ የቆዩ መዘምራን የሚዘምሩ ይመስላል። የክብሩ ሙላት አለ። ከተለያዩ ግዛቶች የመጡ ሰዎች በሠልፍ ወደ አዳራሹ ይገባሉ። ዝናብ ብርድ ጨለማ የማይበግረው ረሃብተኛ ሕዝብ በክብሩ ጥማት የተጎዳ ትውልድ በአዳራሾች በራፍ ይንገበገባል። የክብሩ ብርሃን ቤቱን ሞልቶአል። እንደ ወትሮው ፕሮግራም መሪ ተነስቶ “ከዚህ ቀጥሎ ይህና ያ ይሆናል” የሚልበት ዓይነት formal አካሄድ የለም። መንፈስ እንደ መራው አንዱ ተነስቶ የመጣበትን ግዛት ጠቅሶ ከቃሉ አንድ ክፍል አንብቦ ይወርዳል። ሕዝቡ ያንን የቃሉን ክፍል በዘመኑ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሰማ ሰው በመደነቅ ይሰማል። የገንዘብ ማሰባሰብ የሌለበት፣ ታዋቂና ታላላቅ ሰባኪዎችና ዘማሪዎች ያልተጋበዙበት፣ የሙዚቃ ግርግርና የመድረክ ድምቀት የማይስተዋልበት፣ የማስታወቂያ የፖስተርና የካሜራ ግርግር የማይታይበት የተለመደው የፕሮግራም አካሄድ ሥርዓት የማይነበብበት፣ የመንፈሱ የበላይነት ብቻ የክ

06/01/2023

መልካም የልት በአል

Address

Adis Abeba
Istanbul

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Offeshal Lidiya tefera posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share